በፈረንጆቹ 2020 ስለኮሮናቫይስ ወረርሽኝ መስማት ስንጀምር የብዙዎች ጥያቄ ያተኮረው ስለበሽታው ምንነት፣ እንዴት ሰዎችን እንደሚያጠቃ እና ራሳችንን ከበሽታው ለመከላከል ምን አይነት መንገዶች መከተል እንደሚኖረበን የሚያጠይቁ ነበር፡፡ እነዚህ ጉዳዮች ቀን በገፋ ቁጥር ይበልጥ እየታወቁና በተለያዩ ሳይንሳዊ ምርምሮች እየተረጋገጡ ቢሄዱም በሌላ መልኩ ደግሞ የሚያወዛግቡ እና ብዙ የተሳሳቱ አመለካከቶች የተነሳባቸው ጉዳዮችም ነበሩ፡፡

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ እጅግ በተስፋፋበት ጊዚያት የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሲያነሱት እንደነበረውም ከወረርሽኙ መሰፋፋት እኩል ስለጉዳዩ የሚነዙት የተሳሳቱ መረጃዎች እና ሳይንሳዊ ማረጋገጫ የሌላቸው ብያ

ኔዎች ለአለማችን ሌላ ራስምታት እንደሚሆን በተደጋጋሚ ሲናገሩ ቆይተዋል፡፡ የተለያየ የማህበረሰብ ክፍል የተሳሳተ አመለካከት የወሰደባቸው አነዚህ የተሳሳቱ መረጃዎች እንደየቦታው የተለያየ መልክ ቢኖራቸውም አብዛኛው ህዝብ የተቀበላቸው የተሳሳቱ አመለካከቶች ግን የሚከተሉት ናቸው፡፡

እድሜያቸው የገፋ ሰዎች ብቻ በኮሮናቫይረሱ ይሞታሉ

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ ሲናገሩ እንደተሰሙት የኮሮናቫይረስ የሚያጠቃው እድሜያቸው የገፋ ሰዎችን ሲሆን ወጣቶችና ከ18 አመት በታቻ የሆኑ ታዳጊዎች ግን በቫይረሱ የመሞት እድላቸው ምንም እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ እንደተናገሩት እድሜያቸው የገፋ ሰዎች ይበልጥ ተጋላጭነታቸው የሚጨምር ቢሆንም ወጣቶችም ግን በቫይረሱ የመጠቃት እና የመሞት እድል ቀላል እንደማይሆን ብዙ ጥናቶች አሳይተዋል፡፡ ለምሳሌ በቅርቡ የአሜሪካው CDC ይፋ ያደረገው ጥናት አንዳሳየው በሰኔ፣ በሃምሌና ነሃሴ ከተመዘገቡ የሞት ምጣኔዎች ሃያ በመቶውን የሚሸፍነው የኮቪድ ኬዝ ከ20 እስከ 29 እድሜ ባላቸው ወጣቶች የተመዘገበ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በሃገሪቱ የብሄራዊ የጤና ስታትስቲክስ ማዕከል የተመዘገበው መረጃ እንደሚያሳየው በኮሮናቫይረስ ከሞቱ 1,800 ሰዎች መካከል 1,200 የሚሆኑት ከ18-25 አመት የሚገመቱ ሲሆኑ ሌላውን ቁጥር የሚይዙት ደግሞ ከ35 በታች የሆኑ ወጣቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሪፖርቶች እድሜያቸው የገፋ ሰዎች ብቻ በኮሮናቫይረሱ ይሞታሉ የሚለውን የተሳሳተ አመለካከት የሚያፈርስ ከመሆኑም ባለፈ በማኝኛውም የእድሜ ክልል የሚገኝ ሰው ተመሳሳይ ስጋት ሊኖርበት እንደሚቸል የሚያሳይ ነው፡፡

የፊት መሸፈኛ ጭምብል ከኮሮናቫይረስ አይታደገንም

ይህ አመለካከት ከመጀመሪያዎች ጊዜያት አንስቶ ብዙ ውዝግቦች የነበሩበትና በከፍተኛ የጤና ባለስልጣነት ጭምር ከፍተኛ ክርክር ሲያስነሳ የቆየ ጉዳይ ነው፡፡ ይሁንና ቀን በገፋ ቁጥር በጉዳዩ ዙሪያ ሲደረጉ የነበሩት ምርምሮች የፊት ማስክ ማድረጋችን እጅግ መሰረታዊ እና አስፈላጊ መሆኑን ያሳየ ነው፡፡ በተለይም ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ሁለት ገዳዮች ይበልጥ እየጠሩ ሲመጡ የማስክ አስፈላጊነት ይበልጥ ጨምሯል፡፡ ይህም ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘው ምልክት የማያሳዩ ቢሆንም እንኳን ቫይረሱን ወደሌሎች ማስተላለፍ መቻላቸው የመጀመሪያው ምክንያት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከሰዎች አፍ የሚወጣው ጥቃቅን ብናኘ በአየር ላይ የሚኖረውን የቫይረሱ ክምችት ስለሚጨምረው ነው፡፡ ታዲያ እነዚህ ወሰኝ የቫይረሱ መዛመቻ መንገዶች በምናጠልቅው የፊት መሸፈኛ ጭምብል መገታታቸው የፊት ማስክ አስፈላጊነትን ቁልጭ አድርጎ ሊያሳየን ይችላል፡፡ እዚህ ላይ ጥንቃቄ ሊደረግበት የሚገባው የማስክ አጠቃቀማችን እና የምንመርጠው የጭምብል አይነት እንጂ፤ የፊት ማስክ ማድረግ ከኮሮናቫይረስ መታደጉ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡

ኮሮናቫይረስ እንደጉንፋን ነው

የኮሮናቫይረስ እና የጉንፋን በሽታ ከመተንፈሻ አካል ጋር ተያይዘው የሚነሱ በሽታዎች በመሆናቻው እና አንዳንድ የሚያሳዩት ምልክቶች ተቀራራቢ በመሆናቸው ሰዎች ተመሳሳይ በሽታዎች አድርገው ይመለከቷቸዋል፡፡ ነገር ግን ሁለቱም በሽታዎች እጀግ የተለያዩ ናቸው፡፡ ዋናው መለያያ ምክንያታቸው ደግሞ የሞት ምጣኔያቸው ነው፡፡ እንደ CDC ዘገባ ከሆነ በጉንፋን በሽታ የተመዘገበው የሞት ምጣኔ 0.1 % ሲሆን በዚህም መሰረት በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኘ ሰው በጉንፋን የመሞት እድሉ ተመሳሳይ ነው፡፡ ይሁንና ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ የተመዘገበው የሞት ምጣኔ ከፍተኛ ብልጫ ያለው ሲሆን ከጉንፋን በተለየ ሁኔታ ደግሞ በየእድሜ ክልሉ ልዩነት ያመጣል፡፡ ለምሳሌ ከ50 በታች ያለ በኮሮናቫይረስ የተጠቃ ሰው ዝቅተኛ የሞት ምጣኔ ያለው ሲሆን 70 እና ከዛ በላይ ለሆኑ ሰዎች ደግሞ ከ5.4% ይሻገራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በዚሁ ተቋም ይፋ የተደረገው በ2020 10 ዋና የሞት ምክንያቶች ተደርገው ከተቀመጡ በሽታዎች ኮሮና ከካንሰር እና ከልብ በሽታ ቀጥሎ በሶስተኝነት መቀመጡ እጅግ የተለየ ያደርገዋል፡፡

እዚህ ላይ ጥንቃቄ ሊደረግበት የሚገባው የማስክ አጠቃቀማችን እና የምንመርጠው የጭምብል አይነት እንጂ፤ የፊት ማስክ ማድረግ ከኮሮናቫይረስ መታደጉ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡

የኮሮናይረስ የሚይዘን ምልክቱን ከሚያሳዩ ሰዎች ጋር የአካል ግንኙነት ካለን ብቻ ነው

የኮሮናቫይረስ በንክኪ ብቻ የሚተላለፍ አለመሆኑን ያሳየው የመጀመሪያ ክስተት በዋሽንግተን የነበረው አንድ ሁነት ነው፡፡ 61 አባላት ያሉት የድምፅ ኳየር ለአምስት ሰዓት በነበራቸው የድምፅ ስልጠና ምንም አይነት ንክኪ ሳያደርጉ በአንድ ሰው አማካኘነት ቫይረሱ ሊተላለፍባቸው ችሏል፡፡ ምንም ምልክት ያልታየበት ይህ ሰው ከሌሎች ጋር ምንም ንክኪ ሳይኖረው በትንፈሽ አማካኘነት ብቻ 57 የሚጠጉት የኳየር አባላት በቫይረሱ ሊያዙ ችሏል፡፡ ይህ እውነት የኮሮናቫይረስ ከአካል ንክኪ ባለፈ በአየር ላይ ለሰዓታት መቆየት መቻሉን የሚያሳይ ሲሆን በዙም የአየር ዝውውር በሌላቸው ቦታዎች ደግሞ የበለጠ ከባድ ይሆናል፡፡

የኮሮናቫረስ ክትባት ከተገኘ ሁላችንም በአንዴ ሊደርሰን ይችላል

ከክትባት ጋር በተያያዘ ብዙ የሚወጡ መረጃዎች የተዛባ እይታ ያላቸው ናቸው፡፡ አብዛኞቹ መረጃዎች የፈረንጆቹ አዲስ አመት ሳይደርስ ከትባቶች ሰዎች ጋር ይደርሳሉ የሚሉ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ገና አመታትን ልንጠብቅ አንችላለን የሚሉ ናቸው፡፡ ይሁንና አለም ጤና ድርጅት የሚያስቀምጠው ማብራሪያ እና ብዙዎቹ የጤና ባለስልጣናት የሚጠቁመት መረጃ የሚያመለክተው ክትባቶች በሚጠናቀቁበት ሰዓት ቀድሚያ የሚሰጣቸው አካለት ወረርሽኙን እየተዋጉ ያሉ የጤና በለሙያዎች እና ለበሽታው እጅግ የተጋለጡ ግለሰቦች ናቸው፡፡ ከዛ ባለፈ ግን ክትባቶች ሰዎች ጋር ይደርሰሉ ተብሎ የሚጠበቀው በአውሮፓውያኑ 2021 ግማሽ አመት ላይ ሊሆን ይችላል፡፡

ምንጭ፡ Medical News Today

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *