‹‹ተማሪዎችን ከታች የዴሞክራሲ ሥርዓት እሴቶችን ማስተማር ብንጀምር በኢትዮጵያ የተንሰራፋውን ችግር መቅረፍ እንችላለን›› አቶ ስምኦን ከበደ ተሰማ፣ የቮት ለኢትዮጵያዬ በጎ አድራጎት ድርጅት መሥራች

በኢትዮጵያ የሚታየው የዴሞክራሲ ዕጦት መነሻው ከታችኛው የትምህርት ደረጃ ጀምሮ  የሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር ትምህርት በተግባር አለመሰጠቱ ነው የሚል ሐሳብ አላቸው፡፡ ለዚህም ተማሪዎችን በማሳተፍ ለውጥ ለማምጣት ያስችላል ያሉትን  ‹‹አዲስ ተማሪ አዲስ አፍሪካ አዲስ ዓለም›› ፕሮጀክት ነድፈው መንቀሳቀስ ከጀመሩ ዓመት ሆኗቸዋል፡፡ አቶ ስምኦን ከበደ ተሰማ የቮት ለኢትዮጵያዬ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ ከምሕረት ሞገስ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡ ሪፖርተር፡– ቮት ለኢትዮጵያዬ የተሰኘውን ድርጅት በ2011 ዓ.ም. የመሠረቱት በልጅዎ አማካይነት ነው ይባላል፡፡ ቢያብራሩልን? አቶ ስምኦን፡- ልጄ ወደፊት ምን መሆን ትፈልጊያለሽ ስላት ጠቅላይ ሚኒስትር አለችኝ፡፡ ምላሽዋ አስደነገጠኝ፡፡ በወቅቱ የኬጂ 3…