Month: June 2021

ከትግራይ ክልል ግጭትና ሰብዓዊ ቀውስ ወጣ ያለው የአሜሪካ መንግሥት መግለጫና የፀጥታው ምክር ቤት ውይይት

ፖለቲካዊ መነሻን ይዞ በትግራይ ክልል በተቀሰቀሰው ውጊያና ውጊያውን በተከተለው ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስና ኢሰብዓዊ ጥሰቶች ምክንያት ሥጋቱን ሲገልጽና ግጭቱ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲያገኝ ሲወተውት የነበረው የአሜሪካ መንግሥት፣ ባለፈው ሳምንት ውሳኔው ሥልጣን ላይ የሚገኙና የቀድሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት፣ የመከላለከያና የደኅንነት ዘርፍ ኃላፊዎች ላይ የጉዞ ማዕቀብ መጣሉ ይታወሳል። ከጉዞ ማዕቀቡ በተጨማሪም ከዓመት በፊት የተቋረጠው የኢኮኖሚና የመከላከያ ግንባታ ድጋፍም እንዳይለቀቅ ወስኗል። ይህንን የአሜሪካ መንግሥት ውሳኔ ኢትዮጵያ ተገቢ ያልሆነና ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ፣ በአንድ ነፃ አገር ላይ የሚደረግ ያልተገባ ጣልቃ ገብነት በማለት ማጣጣሏ ይታወቃል። ከዚህም እልፍ በማለት አሜሪካ በዚህ መንገድ የምትቀጥል ከሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት ከአሜሪካ ጋር ያለውን የውጭ ግንኙነት መልሶ ለማየት እንደሚገደድ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ የኢኮኖሚ፣ በባለሥልጣናት ላይ የጉዞ ማዕቀብ መጣሉ በተጠናቀቀው ሳምንት ውስጥ የነበረና አሁንም የቀጠለ ዓብይ መነጋገሪያ…