Month: March 2021

በመተከል ዞን የተፈጠረው የፀጥታ ችግር ለአምስት ዓመታት ዝግጅት የተደረገበት ነው ተባለ

ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን የወሰዱ ግለሰቦች የጉሙዝ ወጣቶችን በማሠልጠን ለዕኩይ ተልዕኮ ማዘጋጀታቸው ተጠቁሟል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በመተከል ዞን ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር ለአምስት ዓመታት ዝግጅት ሲደረገብት መቆየቱን፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጉዳዩን እንዲከታተል የተቋቋመው ኮሚቴ ገለጸ። በመተከልና ሌሎች አካባቢዎች የተፈጠሩ የፀጥታ ችግሮችን በመገምገም የመፍትሔ አቅጣጫ እንዲያቀርብ ተቋቁሞ የነበረው ኮሚቴ እንደገለጸው፣ በመተከል ዞን ከሦስት ሺሕ በላይ ታጣቂዎችና በእነሱ አማካይነት ጫካ ገብተው የነበሩ ከ68 ሺሕ በላይ የጉምዝ ብሔረሰብ አባላት ወደ ሰላማዊ ሕይወት ተመልሰዋል፡፡ ኮሚቴው ሰባት አባላት ያሉትና በመተከልና ሌሎች አካባቢዎች…