ለከፍተኛ ሙቀት ተጋልጠው ስራ የሚሰሩ ነፍሰጡሮች በሆዳቸው ያለው ጽንስ ለሞት የመዳረጉ ወይም የመጨናገፍ ዕድሉ በሁለት እጥፍ እንደሚጨምር በህንድ የተደረገ ጥናት አመላከተ።

ጥናቱ ከፍተኛ ሙቀት እናቶች ላይ የሚያመጣው ተጽዕኖ ከዚህ ቀደም ከታሰበው እጅግ ከፍ ያለ እንደሆነ አሳይቷል።

አጥኚዎቹ ከፍተኛ ሙቀት የሚመዘገብበት የበጋ ወቅትም ሴቶች ላይ ተጽዕኖ እንዳለው ይገልጻሉ።

በጥናታቸውም ነፍሰጡር እናቶች ላይ ብቻ የሚያተኩር አማካሪ እንዲቋቋምም ምክረ ሀሳበ አቅርበዋል።

በህንድ በሚገኘው ራማቻንድራ የከፍተኛ ትምህርት እና ምርምር ተቋም አማካኝነት የተሰራው ጥናት ከአውሮፓውያኑ 2017 ጀምሮ 800 ሴቶችን አሳታፊ አድርጓል።

ከተሳታፊዎች ግማሽ የሚሆኑት ለከፍተኛ ሙቀት ተጋልጠው እንደ ግብርና፣ ጡብ ምርት እና የጨው ማውጣት ስራ ላይ የተሰማሩ ናቸው።

የተቀሩት ደግሞ ቀዝቀዝ ባለ አየር ውስጥ የሚሰሩ ናቸው። ይህም ትምህርት ቤት እና ሆስፒታልን የሚያካትት ሲሆን ክነዚህ ውስጥ ለከፍተኛ ሙቀት የተጋለጡም ይገኙበታል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ምን ያህል የሙቀት መጠን የሰው ልጅ ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ ቁርጥ ያለ ቁጥር የለም።

በጥናቱ ላይ የተሳተፉት ፕሮፌሰር ጃን ሂረሰት ሙቀት የሰው ልጅ ሰውነት ላይ ጉዳት የሚያደርስበትን መጠን የሚወስነው የምንጠቀመው ነገር ነው ይላሉ።

በጥናቱ ተሰታፊ የነበረቸው ስማዚ በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ልጇን አጥታለች።

“ነፍሰጡር እያለሁ በከፍተኛ ሙቀት እና ድካም ውስጥ እስራ ነበር” የምትለው ስማዚ አንድ ቀን ከፍተኛ የጤና መታወክ እንዳጋጠማት ትናገራለች።

በዚያ ምሽት ወደ ሆስፒታል ከባለቤቷ ጋር ሲያመሩ ጽንሱ መውረዱ እንደተነገራት ትገልጻለች።

ስማዚ ከፍተኛ ሙቀት ጽንስ ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ ምንም መረጃ አልነበረኝም ትላለች።

ጥናቱ ግን በከፍተኛ ሙቀት የሚሰሩ እናቶች በቀዝቃዛ አየር ውስጥ ስራቸውን ከሚያከናውኑት ጋር ሲነጻጸር በሆዳቸው ያለው ጽንስ የመጨናገፍ እድሉ በሁለት እጥፍ ከፍ እንደሚል ይገልጻል።.

ታዲያ ይህንን ስጋት ለማስወገድ ፕሮፌሰር ሂረስት ለረዥም ሰዓት ለሙቀት ተጋልጦ መስራትን ማስወገድ፣ በሞቃታማ ቀናት ጥላ ወዳለው ስፍራ በመሄድ በመደበኛ ሁኔታ ማረፍ፣ ከፍተኛ ሙቀት በሚመዘገብባቸው ቀናት ስራን መቀነስ እንዲሁም ውሃን መጠጣትን ልማድ ማድረግ እንደሚረዳ ጠቅሰዋል።     ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *