የአገሪቱ ገዢ ፓርቲ ብልጽግና ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ከፓርቲ ኃላፊነታቸው መሰናበታቸው ተገለጸ።

የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ እንዳለው “የአመራር የመተካካት መርኅን እና የአሠራር ሥርዓት በመከተል” አቶ ደመቀን በክብር መሸኘታቸውን ገልጿል።

አቶ ደመቀን በመተካትም የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እና የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባል አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብልጽግና ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል።

አቶ ደመቀ ከፓርቲ አመራርነታቸው መሰናበት በአገሪቱን መንግሥት ውስጥ ይዘው ከሚገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦታን ሊለቁ እንደሚችሉ አመላካች ነው።

አቶ ደመቀ መኮንን ለረጅም ዓመታት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ ነበር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን በመተካት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ቦታን የያዙት።

በቀድሞው ኢህአዴግ እና በአሁኑ ብልጽግና ፓርቲው ውስጥ ቁልፍ ሥልጣንን ይዘው የቆዩት አቶ ደመቀ፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመቀጠል በፓርቲው ካሉት ሁለት ምክትል ፕሬዝዳንቶች መካከል አንዱ ነበሩ።

የብልጽግና ፓርቲ የመጀመሪያውን ጠቅላላ ጉባኤውን መጋቢት ወር 2014 ዓ.ም. ባካሄደበት ጊዜ፣ አቶ ደመቀ መኮንን ከፓርቲው የአመራርነት ቦታ የመልቀቅ ጥያቄ አቅርበው እንደነበር በወቅቱ መገለጹ ይታወሳል።የአገሪቱ ገዢ ፓርቲ ብልጽግና ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ከፓርቲ ኃላፊነታቸው መሰናበታቸው ተገለጸ።

የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ እንዳለው “የአመራር የመተካካት መርኅን እና የአሠራር ሥርዓት በመከተል” አቶ ደመቀን በክብር መሸኘታቸውን ገልጿል።

አቶ ደመቀን በመተካትም የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እና የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባል አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብልጽግና ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል።

አቶ ደመቀ ከፓርቲ አመራርነታቸው መሰናበት በአገሪቱን መንግሥት ውስጥ ይዘው ከሚገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦታን ሊለቁ እንደሚችሉ አመላካች ነው።

አቶ ደመቀ መኮንን ለረጅም ዓመታት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ ነበር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን በመተካት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ቦታን የያዙት።

በቀድሞው ኢህአዴግ እና በአሁኑ ብልጽግና ፓርቲው ውስጥ ቁልፍ ሥልጣንን ይዘው የቆዩት አቶ ደመቀ፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመቀጠል በፓርቲው ካሉት ሁለት ምክትል ፕሬዝዳንቶች መካከል አንዱ ነበሩ።

የብልጽግና ፓርቲ የመጀመሪያውን ጠቅላላ ጉባኤውን መጋቢት ወር 2014 ዓ.ም. ባካሄደበት ጊዜ፣ አቶ ደመቀ መኮንን ከፓርቲው የአመራርነት ቦታ የመልቀቅ ጥያቄ አቅርበው እንደነበር በወቅቱ መገለጹ ይታወሳል።

አቶ ደመቀ መኮንን ማን ናቸው?

በ1980 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በባዮሎጂ ትምህርት ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል። ከዚያም ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በግጭት አፈታት አጠናቀዋል።

በ1980ዎቹ መጀመሪያ ኢህአዴግን የተቀላቀሉት አቶ ደመቀ፤ ከጥቂት ዓመታት በኋላ የአማራ ክልል ምክር ቤት ተመራጭ ሆነው ነበር።

በ1997 የአማራ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው የተመረጡ ሲሆን፤ በቀጣዩም ዓመት የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ተመርጠዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን የብአዴን ሊቀመንበር ሲሆኑ በኀዳር 2005 ዓ.ም የኢህአዴግ ምክትል ሊቀምንበር ሆነው ከተመረጡበት ጊዜ ጀምሮ በምክትል ጠቅላይ ሚንስትርነት እያገለገሉ ይገኛሉ።

የቀድሞው መምህር ወደዚህ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት የትምህርት ሚንስትር ሆነው አገልግለዋል።

በአሁኑ ወቅት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ደመቀ፤ ከብልጽግና ፓርቲ እራሳቸውን ሲያገሉ የአገሪቱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እያገለገሉ ነው።    ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *