ከፌደራሉ መንግሥት ጋር እየተፋለሙ ያሉት የትግራይ ኃይሎች ዛሬ ለሚጀመረው የሰላም ንግግር ደቡብ አፍሪካ መድረሳቸው ተገለጸ። የህወሓት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት የትግራይ ኃይሎችን የሚወክሉ ተደራዳሪዎች ደቡብ አፍሪካ ደርሰዋል ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ ጽፈዋል። ቀደም ሲል የፌደራሉ መንግሥት ዛሬ በሚደረገው ውይይት ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን አስታውቆ ነበር። ሁለቱ ኃይሎች ልዩነቶቻቸውን በንግግር ለመፍታት በጠረጴዛ ዙሪያ የሚቀመጡት በትግራይ የሚካሄደው ጦርነት ተጠናክሮ በቀጠለበት ወቅት ነው። ባለፉት ቀናት የፌደራሉ መንግሥት ጥምር ኃይሎች በርካታ ከተማዎችን እና የትግራይ አካባቢዎችን ከትግራይ ኃይሎች አስለቅቋል የሚ

ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 14/2015 ዓ. ም. ጀምሮ በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እና በትግራይ አመራሮች መካከል የሰላም ውይይት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። የጠቅላይ ሚንስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን መንግሥታቸው በሰላም ንግግሩ ለመሳተፍ ቁርጠኛ መሆኑን ለአፍሪካ ኅብረት ማረጋገጣቸውን ከቀናት በፊት ገልጸው ነበር። ፕሮፌሰር ክንደያ ደግሞ በትዊተር ገጻቸው ላይ በአፍሪካ ኅብረት በሚመራው የሰላም ንግግር ላይ የሚሳተፈው የትግራይ ልዑክ ቡድን ደቡብ አፍሪካ ደርሷል ሲሉ ትናንት እሁድ ጥቅምት 13 ምሽት ላይ በትዊተር ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።

የንግግር አጀንዳዎች

የአፍሪካ ኅብረት የሚመራው የሰላም ድርድር፤ ተፋላሚ ኃይሎች ግጭት አቁመው ልዩነቶቻቸው በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ተደጋጋሚ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች ሊደራደሩባቸው የሚችሏቸው ጉዳዮች በይፋ ባይገለጽም፤ የአፍሪካ ኅብረት እና ምዕራባውያን ግን ለግጭቱ ፖለቲካዊ መፍትሄ ለመሰጠት ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። ፕሮፌሰር ክንድያ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በሚደረገው ውይይት የትግራይ ኃይሎች የሚያነሷቸው አንገብጋቢ ጉዳዮች ግጭት በአስቸኳይ ማስቆም፣ ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ እና የኤርትራ ኃይሎች ከትግራይ ማስወጣት የሚሉት መሆናቸውን አስታውቀዋል። የፌደራል መንግሥት ግን ከዚህ ቀደም “ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ” ለንግግር ዝግጁ መሆኑን ሲገልጽ ቆይቷል።

ድርድሩ “. . . ለዜጎች መረጋጋትንም ይመልሳል”

ዛሬ በደቡብ አፍሪካ የሚጀመረው የሰላም ንግግር ለሁሉም ዜጎች መረጋጋትን የሚመልስ ነው ስትል አሜሪካ ያላትን ተስፋ ገልጻለች። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ጥቅምት 11፣ 2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ የሰላም ውይይቱን አሜሪካ እንደምትደግፍ ገልጾ፤ ድርድሩ በኢትዮጵያ ያለውን ውጊያ ይገታል ሲል ያለውን ተስፋ ጨምሮ ገልጿል።

“ደቡብ አፍሪካ ይህንን ውይይት ለማስተናገድ በመፍቀዷ እናመሰግናለን። የአፍሪካ ኅብረት ልዩ ልዑክ ኦሉሴጎን ኦባሳንጆን እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት ፓናል አባል የሆኑተን ፑምዚሌ ማልምቦ ንግቹካ እና ኡሁሩ ኬንያታ የሰላም ስምምነት ላይ እንዲደረስ የሚያደርጉትን ጥረት እንደግፋለን” ይላል መግለጫው።

በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ድረ ገጽ ላይ የወጣው መግለጫ “ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን መስከረም ላይ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንዳሉት፣ በአፍሪካ ኅብረት ፓናል አባላቱ አማካይነት የሚደረሰው የሰላም ስምምነት፣ በኢትዮጵያ ያለውን ውጊያ ይገታል። ለሁሉም ዜጎች መረጋጋትንም ይመልሳል” ሲልም አክሏል።

ተደራዳሪዎቹ እነማን ናቸው?

የፌደራሉ መንግሥት ከትግራይ ኃይሎች ጋር የሚነጋገሩ አባላት ከዚህ ቀደም ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ይህ ተደራዳሪ ቡድን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን የሚመራ ሲሆን ሰባት አባላትን ያካተተ ነው።

ከአቶ ደመቀ በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግሥት መንግሥትን የሚወክሉት የፍትሕ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር)፣ ብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ተመስገን ጥሩነህ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንት ጉዳዮች አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የመከላከያ ሠራዊት የመረጃ ደኅንነት ኃላፊ ሌ/ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ጌታቸው ጀምበር (ዶ/ር) እና በብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ማዕከል ዘርፍ ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት እየሰሩ የሚገኙት አምባሳደር ሐሰን አብዱልቃድር ናቸው።

የትግራይ ኃይሎች በበኩላቸው ሁለት ተወካዮቻቸውን ለድርድር እንደሚልኩ ከዚህ ቀደም ገልጸው ነበር። የመጀመሪያው የህወሓት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የፓርቲው ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ የትግራይ ኃይሎችን ከሚመሩት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች መካከል አንዱ የሆኑት ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳይ ናቸው።

ምንጭ – ቢቢሲ

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *