በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጎንደር ከተማ ሸህ ኤሊያስ እየተባለ የሚጠራ የእስልምና እምነት ተከታዮች የቀብር ቦታ የሚገኝ ሲሆን በዚህም ቦታ አዋሳኝ
የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የፀበል ቦታ ይገኛል፡፡ በዚህ አካባቢ ላይ በድንበር እና በመሬት ይገባኛል ምክንያት በተደጋጋሚ
አለመግባባቶች ሲነሱ መቆየታቸውን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው የመረጃ ምንጮች ለመረዳት ችሏል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ለጉዳዩ ዘላቂ መፍትሄ ሳይሰጥ ቆይቶ
ሚያዚያ
18 ቀን 2014 .ም የሸህ ከማል ለጋስ ስርዓተ ቀብር በመስጊዱ ውስጥ በሚፈፀምበት ሰዓት ለቀብሩ የሚያስፈልጉ ድንጋዮችን በቀብር ስነስርዓቱ ላይ
ተገኝተው የነበሩ ሰዎች ለማንሳት ሲንቀሳቀሱ ከቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ጊቢ ነው ድንጋይ የምታነሱት በሚል የተፈጠረው አለመግባባት በአካባቢው ምንም አይነት
የጸጥታ አካል ባለመኖሩ ግጭቱ ወደ ከተማዋ ዘልቆ መግባቱን፣ ይህም ግጭት የተደራጀ መልክ የነበረውና ዱላ፣ ድንጋይ እና ስለት ጥቅም ላይ የዋሉበት እንደነበር፣
ይህንንም ተከተትሎ የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉን እና ብዙዎችም የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ ህክምና
እየተደረገላቸው መሆኑን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡

እንዲሁም ይህንን ግጭት ተከትሎ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ሰዎችንመኖሪያ ቤቶች፣ ንግድ ሱቆች እና ባለሶስት እግር ተሸከርካሪዎች በመለየት ቃጠሎ እና የተደራጀ ዘረፋ የደረሰ መሆኑን፣ በአካባቢው በሚገኙ አራት መስጅዶች ላይጉዳት መድረሱን እና ግጭቱን ተከትሎ በተለምዶ አራዳ የሚባለው አካባቢ የንግድ እንቅስቃሴዎች መቋረጣቸውን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው የመረጃ ምንጮችለመረዳት ችሏል፡፡ በተጨማሪም ይህንን ግጭት ተከትሎ ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች መታሰራቸውን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡ ከዚህ ቀደም የሁለቱም እምነት ተከታዮች በሰላም በአብሮነት መኖራቸው የሚታወቅ ሲሆን ቦታውን በሚመለከት በአንዳንድ አለመግባባቶች ቸግሮች ተፈጥረው የነበረ ሲሆን አነዚህንም አለመግባባቶች ሽማግሌዎች ህጋዊ በሆነ መንገድ እንደከፈሉት እና መስማማት ላይ እንደደረሱ የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ ከሰጡት መግለጫ እና የአማራ ክልል ህዝብ ግንኙነት ጉዳዩን አስመልክቶ ካወጣው መግለጫ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ተያያዥ የህግ ግዴታዎች፡

ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መግለጫ (UDHR) አንቀጽ 3፣ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳንም (ICCPR) በአንቀጽ 6(1) እና 9(1)
ላይ እያንዳንዱ ሰው በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነቱ የመጠበቅ መብት እንዳለው ያረጋግጣል። ይህንኑ መብት በማረጋገጥ፣ መንግሥታት በቃልኪዳኑ
(ICPR) የተረጋገጡትን መብቶች በግዛታቸው የማክበር፣ የማስከበርና የማሟላት ግዴታ እንዳለባቸውም በአንቀጽ 2(1) እና 2(2) ይደነግጋል። የአፍሪካ ቻርተር
በሰዎች እና ህዝቦች መብቶች
(ACHPR) አንቀጽ 4 ማንኛውም ግለሰብ በሕይወት የመኖር መብቱና የአካሉ ደህንነት መብቱ ሊከበርለትና ሊጠበቅለት እንደሚገባና
እነዚህን መብቶቹን በዘፈቀደ ሊነፈግ እንደማይችል ተመላክቷል። የኢ
...ሪ ሕገመንግሥት አንቀጽ 14 “ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና
የማይገሰስ በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነትና የነጻነት መብት አለው
ሲል ይደነግጋል። በተመሳሳይ የኢ...ሪ ሕገመንግስት አንቀፅ 15 ማንኛውም ሰው
በሕይወት የመኖር መብት እንዳለውና በሕግ ከተደነገገው ውጪ ሕይወቱን ሊያጣ እንደማይችል በግልፅ ደንግጓል፡፡ በተመሳሳይ የኢ
...ሪ ሕገመንግስት
በአንቀጽ
16 ላይ ማነም ሰው በአካሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት የመጠበቅ መብት አለው ሲል ያስቀምጣል፡፡

ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መግለጫ (UDHR)ና የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳንም (ICCPR) ሁለቱም ስምምነቶች በአንቀጽ 18
ላይ ማንም ሰው የሀሳብ፣ የኅሊናና የሀይማኖት ነጻነት አለው ሲሉ ደንግገዋል፡፡ በተመሳሳይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገመንግስት በአንቀጽ 27 ላይ ማንም ሰው የማሰብ፣
የህሊና እና የሀይማኖት ነጻነት አለው፡፡ ይህ መብት ማንኛውም ሰው የመረጠውን ሀይማኖት የመያዝ ወይም የመቀበል፣ ሀይማኖቱንና እምነቱን ለብቻ ወይም
ከሌሎች ጋር በመሆን በጋራ ወይም በግል የማምለክ፣ የመከተል፣ የመተግበር፣ የማስተማር ወይም የመግለጽ መብትን ያካትታል ሲል ይደነግጋል፡፡
ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መግለጫ
(UDHR) አንቀጽ 17 ማንኛውም ሰው ብቻውንም ሆነ ከሌሎች ጋር በመተባበር የንብረት ባለቤት የመሆን
መብት እንዳለውና ማንም ሰው በዘፈቀደ ንብረቱን እንዲያጣ እንደማይደረግ ያረጋግጣል፡፡ የአፍሪካ ቻርተር በሰዎች እና ህዝቦች መብቶች
(ACHPR) በአንቀጽ
14 ላይ የንብረት ባለቤትነት መብት እንደሚረጋገጥ እና ሊጣስ የሚችለው ለህዝብ ፍላጎት ወይም ለህብረተሰቡ አጠቃላይ ጥቅም እና አግባብ ባላቸው ህጎች
በተደነገገው መሰረት ብቻ እንደሆነ ይደነግጋል፡፡ ይኸው ቻርተር በአንቀጽ
1 ላይ በዚህ ቻርተር ውስጥ የተካተቱት ሀገሮች በቻርተሩ ውስጥ የተካተቱትን
መብቶች፣ ተግባሮች እና ነፃነቶች ተገንዝበው ተግባራዊ ለማድረግ የሕግ አውጭ ወይም ሌሎች እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡ የኢ
...
ሕገ
መንግሥት በአንቀጽ 40 ሥር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የግል ንብረት ባለቤት መሆኑ እንደሚከበርለት ይደነግጋል፡፡
በተጨማሪም ኢሰመጉ በዚህ ክስተት ዙሪያ ተጨማሪ የምርመራ ስራዎችን በማከናወን ሰፋ ያለ ዘገባን ወደፊት እንደሚያቀርብ ከወዲሁ ይገልጻል፡፡

የኢሰመጉ ጥሪ፡

ኢሰመጉ በጎንደር ከተማ በሀይማኖት ሽፋን የደረሰውን ጥቃት እያወገዘ፤

 • የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለችግሩ የሰጠው ፈጣን ምላሽ አለመኖሩን በመግለጽ እና መንግስት እንደ መንግስት ችግሮች ከቁጥጥር ውጪ ሳይሆኑ፣ የሰው
  ህይወት ሳይጠፋ፣ አካል ሳይጎዳና ንብረት ሳይወድም አሰቀድሞ የመፍታት ሃላፊነት እንዳለበት በመረዳት ይህን ሀላፊነት ለመወጣት በአግባቡ እንዲንቀሳቀስ፣
 • በሀገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አብሮ የመኖር እና የመቻቻል ባህላችንን በመዘንጋት በሀይማኖት ሽፋን እየተነሱ ያሉ ግጭቶች እየተደጋገሙ እየመጡ
  ስለሆነ ይህ ችግር በቂ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ በመሆኑ ችግሮች ሳፈጠሩ እና በአለመግባባቶች ምክንያት የሰዎች ህይወት ሳይጠፋ፣ አካል ሳይጎዳ እና
  ንብረት ሳይወድም በሰላማዊ መንገድ ለአለመግባባቶች ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት አንዲቻል፣
 • በጎንደር ከተማ የተነሳው አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ እና በሰዎች ላይ የተለያዩ የመብት ጥሰቶችን የፈጸሙ አካላት በአፋጣኝ ለህግ ቀርበው
  አስተማሪ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ፣
 • መንግስት፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የማሕበረሰብ አንቂዎች፣ ተጽኖ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦች፣ የፖለተቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማህበራት፣
  ሕብረተሰቡ እንደ አጠቃላይ እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ በሀገራችን ኢትዮጵያ ለዘመናት የኖረውን የመቻቻል የመከባበር እና አብሮ የመኖር
  ባህልን በመዘንጋት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀይማኖት ሽፋን እየተነሱ ያሉ ግጭቶች እና እየደረሱ ያሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በመፍታት ረገድ የበኩላቸውን
  እንዲወጡ እና መሰል ችግሮች ወደፊት እንደዳይፈጠሩ አስቀድሞ በመከላከሉ ላይ ምትክ የሌለውን ሰፊ ድርሻቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ኢሰመጉ ጥሪውን
  ያቀርባል።
selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *