የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽርነት የቀረቡትን 11 ዕጩዎችን ሹመት በአምስት ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ፡፡ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዕጩ ኮሚሽነሮችን ጥቆማ አቀባበል አማካሪው ቡድን አቋቁሞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሥራውን አጠናቋል፡፡ የምክር ቤቱ የዕጩ አቀባበል አማካሪ ቡድን አባላቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት፣ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ተወካይና የሲቪል ማኅበራት ጥምረት ተወካይ ናቸው፡፡

ከቀረቡት በርካታ ዕጩዎች ላይ የሕዝብ አስተያየት ተሰጥቶ፣ መሥፈርቱን ማሟላታቸው ተረጋግጦና ፈቃደኛነታቸው ተጠይቆ 11ዕጩዎች ዛሬ የካቲት 14 ቀን 2014 ዓ.ም. ሹመት እንዲፀድቅ ዛሬ ጠዋት ቀርቦ አስተያየት ከተሰጠና ውይይት ከተደረገበት በኋላ

1. መስፍን አርዓያ ወልደ ተንሳይ (ፕሮፌሰር)
2. ወ/ሮ ሒሩት ገብረ ሥላሴ ኦዳ
3. ተገኘ ወርቅ ጌቱ (ዶ/ር)
4. አይዶሪት መሐመድ ያሲን (ዶ/ር)
5. ወ/ሮ ብሌን ገብረ መድኅን ዮሴፍ
6. ዮናስ አዳዬ አደቶ (ዶ/ር)
7. አቶ ዘገየ አስፋው አብዲ
8. አቶ መላኩ ወልደ ማርያም በላይ
9. መሐመድ ድሪር ገሃዲ (አምባሳደር)
10. አቶ ሙሉጌታ አጎ ወልደ ሚካኤል
11. አምባዬ ኦጋቶ አናታ (ዶ/ር)  የአገራዊ ምክክሩ ኮሚሽነር ሆነው ቃለመሃላ ፈጽመዋል።

ምንጭ – ሪፖርተር

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *