ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት ከሕዝብ ከተጠቆሙ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ግለሰቦች መካከል በዕጩነት የተለዩ የ42ቱን የስም ዝርዝር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይፋ አደረገ።

በቀጣይ ሂደትም ከ42ቱ መካከል ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን በኮሚሽነርነት የሚሰየሙትን ለመለየት በቀረቡት ዕጩዎች ላይ ሕዝብ አስተያየት እንዲሰጥ ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል። ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ መሠረታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር በማድረግና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችል ሂደትን የሚመራና የሚያስተባብር አካል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካይነት ለማቋቋም ጥቆማ መካሄዱ ይታወሳል።

ለሕዝብ በቀረበ ጥሪ መሠረት 632 ዕጩዎች በተለያዩ ወገኖች ተጠቁመው ከእነዚህ መካከል ኮሚሽኑን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ በተቀመጡት መስፈርቶች አማካኝነት 42ቱን መለየታቸውን ከሳምንት በፊት የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ አስታውቀው ነበር። ከተጠቆሙት 632 ዕጩዎች ውስጥ የተለዩት 42ቱ ዕጩ ተጠቋሚዎች የትምህርት ሁኔታና የሥራ ልምድ ላይ ከአማካሪዎች ጋር ምክክር ከተደረገበት በኋላ ለሕዝብ ቀርበው አስተያየት እንደሚሰበሰብ ተገልጾ ነበር።

በዚህም መሠረት አብዛኞቹ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በማስተማርና በምርምር ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ ምሁራን የተካተቱበት የ42 ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ የተደረገ ሲሆን ሕዝቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸውም ተጠይቋል። በቀረበው ጥሪ መሠረት ከተለያዩ ወገኖች ከተጠቆሙት ዕጩዎች መካከል የተለዩት 42ቱ ዕጩ ተጠቋሚዎች የሚከተሉት ናቸው፡

1. ሎሬት ፕሮፌሰር ጥሩሰው ተፈራ

2. ፕሮፌሰር አፈወርቅ በቀለ ስመኝ

3. ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ

4. ፕሮፌሰር ባዬ ይማም

5. ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ

6. ፕሮፌሰር ያእቆብ አርሳኖ

7. ፕሮፌሰር ካሳሁን ብርሃኑ ዓለሙ

8. ፕሮፌሰር ህዝቅያስ አሰፋ

9. ፕሮፌሰር በቀለ ጉተማ ጀቤሳ

10. ፕሮፌሰር ዶክተር ዳንኤል ቅጣው

11. ፕሮፌሰር ዘካሪያስ ቀነአ ተስገራ

12. ፕሮፌሰር ክፍሌ ወ/ሚካኤል ሐጀቶ

13. ዶክተር በድሉ ዋቅጅታ

14. ዶክተር ሰሚር የሱፍ

15. ዶክተር አብዲሳ ዘርዓይ በማኖ

16. ዶክተር ሀብታሙ ወንድሙ

17. ዶክተር ታከለ ሰቦቃ

18. ዶክተር ዮናስ አዳዬ

19. ዶክተር ወዳጆ ወ/ጊዮርጊስ

20. ዶክተር ሙሉጌታ አረጋዊ

21. ዶክተር ነጋልኝ ብርሃኑ ባዬ

22. ዶክተር አበራ ዴሬሳ

23. ዶክተር አይሮሪት መ/ድያሲን

24. ዶክተር ተገኘወርቅ ጌጡ መንገሻ

25. ዶክተር ዳዊት ዮሐንስ

26. ዶክተር ተካለ ሰቦቃ

27. ኢንጂኒየር ጌታሁን ሁሴን ሽኩር

28. አምባሳደር ታደለች ኃይለሚካኤል

29. አምባሳደር ምዑዝ ገብረ ሕይወት ወልደ ሥላሴ

30. አምባሳደር ማህሙድ ድሪር

31. አቶ ዘገየ አስፋው አብዲ

32. ወ/ሮ ዘነብወርቅ ታደሰ ማርቆስ

33. አቶ ኢብራሂም ሙሉ ሸዋ እሸቴ

34. አቶ መላኩ ወልደማሪያም

35. አቶ አንዳርጋቸው አሰግድ

36. አቶ ገመቹ ዱቢሶ ጉደና

37. አቶ ሳሙኤል ጣሰው ተፈራ

38. አቶ አህመድ ሁሴን መሐመድ

39. ወ/ሮ ሂሮት ገ/ሥላሴ ኦዳ

40. አቶ ንጉሡ አክሊሉ

41. አቶ ተስፋዬ ሐቢሶ

42. አቶ አባተ ኪሾ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት የተጠቆሙትን 42ቱን ግለሰቦች ዝርዝር ከአጭር የትምህርትና የሥራ መግለጫ ጋር በድረ ገጹ ላይ ይፋ ያደረገ ሲሆን ሕዝቡም አስተያየት እንዲሰጥባቸው ጥያቄ አቅርቧል። ከዚህ ሂደት በኋላም በተጠቋሚ ዕጩዎቹ ላይ ከሕዝብ የሚቀርበው አስተያየት ተገምግሞ የመጨረሻዎቹ 11 ዕጩ ኮሚሽነሮች ተለይተው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሹመት እንደሚቀርቡ ተገልጿል።

ምንጭ – ቢቢሲ