የኢትዮጵያ መንግስት በሳዑዲ አረቢያ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ያሉ እና የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈፀመባቸው የሚገኙ ዜጎቻችን’ን ወደ ሃገር ለመመለስ በርካታ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በዚህም በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉ ይታወቃል። ጥሰት እየተፈፀምባቸው ለሚገኙ ኢትዮጲያዊያን ድምፅ በመሆን የድርሻቸውን እንዲወጡ እንዲሁም የሳዑዲ አረቢያ መንግስት የስደተኞችን እና እስረኞችን መብቶች፤ የተባበሩት መንግስታትን ቻርተር እና አለም አ+ፍ ህጎችን እንዲያከብር እንዲወተውቱ ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ይሁን እንጅ አሁንም በሳዑዲ አረቢያ እስር ቤቶች ውስጥ የሚTኙ ብዛት ያላቸው ዜጎች ሞት፣ ኢ-ሰብአዊ አያያዝ እንዲሁም ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ለተለያዩ መገናኛ ብዙሀን እየገለፁ ይገኛሉ፡፡ አል አይን አማርኛ ታህሳስ 25 ቀን 2014 ዓ.ም ባዕጣው ዘገባ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች

“የእስር ቤት ሃገር የሚ ክፈትልን ሰው ሲሞት ብቻ ነው” ማለታቸውን እና በኣንድ ክፍል ውስጥ እስከ 500 ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መታሰራቸውን ገልጧል። አል አይን ስደተኞቹን ዋቢ በማድረግ ህፃናት በእስር ቤት እያሉ ዕበሽታ እና በርሃብ መሞታቸውን፤ ዜጎች ያለ ምግብ፣ ልብስ እና ውሃ እንዲሁም በህመም እየተሰቃዩ መሆኑን አስታውቋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከወራት በፊት ሃውማን ራይትስ ዋት የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት ከየመን ወደ ሳዑዲ የ7ኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በጅምላ ለእስር መዳረጋቸውን መግለፁ ኣይተዘነጋም። በተመሳሳይ አዲስ ስታንዳርድ በነሐሴ 21 ቀን 2013 የሳዑዲ መንግስት የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸውና የሌላቸውን እንዲሁም ምንም አይነት ወንጀል ያልፈፀሙ ኢትዮጵያውያንን ማሰሩን የችግሩ ሰለባ የሆኑ ዜጎችን በማነጋገር ዘግቧል።

በሌላ በኩል እንደ ሂውማን ራይትስ ዋች እና የአለም አ*ፍ የስደተኞች ድርጅት ያሉ አለም አቀፍ የመብት ተሟጋች ተጵማት እና ግብረሰናይ ድርጅቶች የእነዚህን ስደተኞች ጉዳይ በሚመለከት ለሳኡዲ መንግስት ጥያቄዎችን ሲያቀርቡ እና ጕዳያቸው በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ትኩረት እንዲያገኝ ሲወተውቱ የነበረ ስሆንም የስደተኞቹ አያያዝ መሻሻል እያሳየ አይደለም፡፡

በመሆኑም መንግስት ከሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ጎን ለጎን ዜጎችን ወደ ሃገራቸው የመመለስ ሂደቱን አስጠናክሮ በመቀጠል ዜጎቹን ከሞትና ከስቃይ መታደግን ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ በተጨማሪም መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር በሀገሪቱ የሚገኙ ዜጎች አያያዝ ሰብአዊነትን የተላበሰ እንዲሆን ማድረግን እና እንዲሁም ተመላሽ ዜጎችን የማቋቋሙን ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል ስንል ለማሳሰብ እንወዳለን። 

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *