አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ለሚጓዙና በአገሪቱ ላሉ ዜጎቿ የጉዞ ማስጠንቀቂያ ስታወጣ፤ ሩሲያ በበኩሏ ዜጎቿ ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ ከማድረግ እንዲቆጠቡ አሳስባለች። የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ የሚገኙ ዜጎቹ በኢትዮጵያ ላሉና ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ ላቀዱ ዜጎቹ የጉዞ ማስጠንቀቂያ አወጣ። ኤምባሲው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የአሜሪካ ዜጎች ከኢትዮጵያ ለመውጣት ዝግጅት እንዲያደርጉ እንዲሁም ወደ ኢትዮጵያ የሚደረግ ጉዞ ያላቸው ዕቅዳቸውን በአንክሮ እንዲያጤኑት አሳስቧል።

ይህ የኤምባሲው ዜና የተሰማው የኢትዮጵያ መንግሥት በመላው አገሪቱ ለስድስት ወራት ተግባራዊ የሚሆን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 23/2014 ዓ.ም መደንገጉን ካሳወቀ በኋላ ነው። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የጣላቸው ክልከላዎችና ግዴታዎች ምንድን ናቸው? በትግራይ ያለው የረሃብ አደጋ እና የመድኃኒት እጥረት አሜሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሦስት አገራትን ከአጎዋ ተጠቃሚነት ማገዷን አስታወቀች በተመሳሳይ ሩሲያ ዜጎቿ አሁን ካለው የኢትዮጵያ ሁኔታ አንፃር ከቻሉ ጉዞ ከማድረግ እንዲቆጠቡ አሳስባለች።

በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ በኦፊሴላዊ የትዊተር ገፁ በለጠፈው መልዕክት አስቸኳይ ካልሆነ በስተቀር ሩሲያዊያን ወደ ኢትዮጵያ እንዳያመሩ ምክር ሰጥቷል። “እየተባባሰ ባለው የማሕበራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ ምክንያት ሩሲያዊያን ዜጎች አስቸኳይ ካልሆነ በቀር ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ እናሳስባለን” ይላል መልዕክቱ። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያወጣው አዋጅ ዋነኛ ዓላማ የአገሪቱ ዜጎች “በሽብር ቡድኑ የሚደርስባቸውን ጥቃት መመከት” መሆኑ የተገለጸ ሲሆን አዋጁም ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።

የአሜሪካ ኤምባሲ ለዜጎቹ ባስላለፈው መልዕክት “የአሜሪካ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ የመጓዝ ውሳኔያቸውን በአንክሮ እንዲያስቡበት እና በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ዜጎች ደግሞ ከአገር ለመውጣት ዝግጅት እንዲያደርጉ አጥብቀን እንመክራለን” ይላል። በአሁኑ ወቅት የኤምባሲው ሠራተኞች ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ መጓዠ እንደማይፈቀድላቸው አስታውሶ፤ ባለፉት በርካታ ቀናት በአማራ፣ በአፋር እና በትግራይ ክልሎች ተባብሶ የቀጠለው ግጭት እና አመጽ በኢትዮጵያ ያለውን የደኅንነት ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ አስጊ አድርጎታል ብሏል።

አንድ ዓመት ሞላው በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ጦርነት እተባባሰ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች የተስፋፋ ሲሆን የፌደራል መንግሥቱና የክልል አስተዳደሮች የአማጺያኑን እንቅስቃሴ ለመመከት ለሕዝቡ ጥሪ አቅርበዋል።አሜሪካ እና ሩሲያ ወደ ኢትዮጵያ ለሚጓዙና በአገሪቱ ላሉ ዜጎቻቸው የጉዞ ማስጠንቀቂያ አወጡ።

ምንጭ – ቢቢሲ

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *