ምዕራፍ  ሁለት ፥ ሰተኛ መረጃን ለማጣራት የምንጠቀምባቸው  መገልገያዎች

ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙኃን ሃቅን ለማጣራት እንዲችሉ የሚያግዝ ማጣቀሻ የቀጠለ. . . . . .

በዚህ   ምዕራፍ    የተለያዩ    ሃሰተኛ    መረጃዎችን  ለማጣራት    የሚያገለግሉ  መገልገያዎች   እና   ስልቶች ይዳሰሳሉ።   በአብዛኛው  መገልገያዎች  በይነመረብ ላይ  በነጻ  የሚገኙ   ስለሆነ  ስለአጠቃቀማቸው የተወሰነ የክህሎት ስልጠና የወሰደ  ማንኛውም ሰው በማህበራዊ  ሚዲያና  በድረ-ገጾች የሚለቀቁ  ሃሰተኛ  መረጃዎችን ማጣራት  የሚችልበት እድል በሰፊው እየተፈጠረለት ይገኛል። ነገር  ግን  ስለ መገልገያዎች ከማውራታችን በፊት  በተወሰነ   መጠን   የማህበራዊ  ሚዲያ  መረጃዎችን  ማጣራት   ለምን  ያስፈልጋል የሚለውን   ማየት ተገቢ  ነው።

2.1.  ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ማጣራት የሚያስፈልገው ለምንድን ነው?

ሰዎች  መረጃ  የሚያገኙባቸው ዘዴዎች በጊዜ ሂደት እየተበራከቱ መጥተዋል፡  ከተወሰኑ አስርተ-ዓመታት በፊት  ዋና  የመረጃ  ምንጮች  መደበኛ  የብዙሃን መገናኛዎች  እንደነበሩ ይታወሳል። ምንም እንኳ  የቆዩት ሚዲያዎች   አሁንም   ዜናና    የተለያዩ   ፕሮግራሞችን የማድረስ  ስራ  እየሰሩ   ቢገኙም  የማህበራዊ  ሚዲያ እና   ኦን  ላይን   ሚዲያው   ወደ  መድረኩ  ብቅ  በማለታቸው   የመረጃ   ማግኛ  አማራጮች   ሰፋ  ብለዋል። ከመደበኛ  መገናኛዎች ይልቅ  ማህበራዊ   ሚዲያ  እና  ኦን  ላይን  ሚዲያዎች   መረጃን  በቀላሉና  በፍጥነት ለማግኘት የተሻሉ አማራጮች  በመሆናቸው  በርካታ  ቁጥር  ያለው ህዝብ መረጃዎችን ለማግኘት በእነዚህ ሚዲያዎች   ላይ  ጊዜ  ያሳልፋል። ለዚህ  ማመላከቻ  የሚሆነው እ.ኤ.አ  በ2018 በአሜሪካ  የወጣ  ግምታዊ መረጃ  እንደሚያመላክተው ከሆነ  ወደ  70  በመቶ  አካባቢ  አሜሪካውያን   የሚፈልጉትን ዜና  የሚያገኙት ከማህበራዊ   ሚዲያው  ነው።

የኢንተርኔት  ስርጭት  ከአውሮፓ  ውጭ   ባሉ   በርካታ   ታዳጊ  አገራት   ዝቅተኛ  ቢሆንም   የሚፈልጉትን ዜና   እና   መረጃ   ከማህበራዊ   ሚዲያ   የሚያገኙ  ሰዎች   ቁጥር   በመጨ መር  ላይ   መሆኑን   መረጃዎች ያመላክታሉ።   በመደበኛ  መገናኛ  ብዙሃን ላይ  የሚተገበረውን የይዘት ቁጥጥር (አንድ  ይዘት  ወደ  ህዝብ ከመድረሱ በፊት  ማለፍ  ያለበት  የአ ርትዖትና ሙያዊ  ግምገማ)  በማህበራዊ   ሚዲያዎች   ላይ  መተግበር ስለማይቻል   በፍጥነትና  በብዛት   የሚለቀቁ   መረጃዎችን  ማጣራት   ፋይዳው   የጎላ   ነው።   ሁሉም   ሰው የተለያዩ   መረጃዎችን ያለምንም  ተቆጣጣሪ   በመሰለው   መንገድ እያዘጋጀ   በማህበራዊ   ሚዲያው  የሚለቅ በመሆኑ የመረጃዎችን ትክክለኛነት ማጣራት  ጠቃሚ  ነው።  በሃሰተኛ መረጃዎች  ምክንያት  ህዝቡ ጋዜጠኝነትን ጨምሮ  ሁሉንም  አይነት ይዘቶች ማመን ሊያቆም ይችላል።  ሃሰተኛ  ዜናዎች  ሰዎች ቦታ በሚሰጡት/ጠቃሚ ነው ብለው በሚያስቡት/ ጉዳይ ላይ አጀንዳ በማስያዝ እና መረጃን በመበከል ሰዎች ምክንያታዊ   ሆነው   እንዳያስቡ   በማድረግ  ረገድ   የሚኖረው   ተፅዕኖ  ከፍተኛ   ነው።   ሃሰተኛ   መረጃዎች ጥርጣሬን  የሚጨምሩ በመሆኑ  በተለያዩ   ጉዳዮች  ላይ  የሚኖረውን  አረዳድ  በማዘባት   ረገድ  ሚናቸው ላቅ እያለ  መጥቷል።

በይዘትና ምስሎች ላይ ለውጥ ማድረግ  ወይም መነካካት አዲስ አይደለም።  ከምስሉ በግልጽ መረዳት እንደሚቻለው  ጆሴፍ  ስታሊን  ከጓዶቹ  ጋር  የሚታይ ሲሆን  በጊዜ ሂደት ግን  በስታሊንና በጓዶቹ  መካከል ልዩነቶችና አለመግባባቶች መፈጠራቸውን ተከትሎ  የምስሉን ይዘት  በመቀየር /ጓዶቹን ከምስሎ በማውጣት/ ስታሊን   ብቻውን  እንዲታይ  ተደርጓል።  በመሆኑም  በቡድን   የተነሳ   ምስል   (group   photo)   ተቆርጦ የአንድን ሰው ስብዕና  (personality cult) ለመገንባት በሚያስችል  መንገድ እንደተዘጋጀ መረዳት  ይቻላል።

አስታውሱ!

ሃሰት  ከሆነ   ዜና   አይደለም።    ዝናችሁን  ለመግንባት  አመታት  ፈጅቶባችኋል፤  በግዴለሽነት  ትዊት በማድረግና  ፖስት   በማድረግ  አታበላሹት።  ማህበራዊ   ሚዲያ   ላይ   በምታዩት  የተለጠፈ   ነገር   ወይም ምስል  እውነተኛነት፣  ትክክለኛነት ወይም  ታማኝነት  ጥርጣሬዎች ካሏችሁ  አታጋሩት።

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *