1.4. የሃሰተኛ መረጃዎች መዘዝ

ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙኃን ሃቅን ለማጣራት እንዲችሉ የሚያግዝ ማጣቀሻ የቀጠለ. . . . . .

ሃሰተኛ   መረጃዎች  የሚያስከትሉት ጉዳት  እጅግ  ከፍተኛ  ነው።  በተለያየ  ጊዜ  አመጽ  በመቀስቀስ  በርካታ ንብረት   እንዲወደም፣  ከምንም  በላይ   እጅግ   ክቡር   የሆነው  የሰው   ልጅ   ህይዎት  በከንቱ   እንዲያልፍ ምክንያት  ሲሆኑ ይስተዋላል። በተለይ  ደግሞ  ብሄርን መሰረት  ያደረገ ፖለቲካ  ስር በሰደደበት፣ የመቻቻልና የማስተዋል  ጥበብ     በሂደት  እየተሸረሸረ   በሄደበት፣    ልዩ   ፍላጎታቸውን  ለማራመድ  ተግተው  በድብቅ ሴራ   የሚጎነጉኑ  ግፈኞች   በተበራከቱበት ሁኔታ፣  በስራ  አጥነትና  በተለያዩ   የኑሮ  ጫናዎች  የተማረረ በሚሊዎኖች  የሚቆጠር   ወጣት   ባለበት   ሁኔታ፣   አስቸጋሪ አዝማሚያዎችን ቀድሞ   በመገንዘብ   በከፋ መልኩ  ከመከሰታቸው በፊት  የመቀልበስ ስራ  ለመስራት አቅምና  ዝግጁነት   ጠንካራ  ባልሆነበት ሁኔታ፣ ተገቢውን   መረጃ    ከመንግስት አካላት  በአጭር ጊዜ  ማግኘት  አዳጋች    ሆኖ  በቆየበት፣ የዳበረና  ጠንካራ የሚዲያ  አሰራር  በሌለበት፣ ሚዲያዎች  የመንግስትን ፊትና  ይሁንታ አይተው  ለመንቀሳቀስ  በሚዳዱበት እንዲሁም   በተለያዩ  ውስጣዊና   ውጫዊ  ጫናዎች ተወጥረው በሚፍጨረጨሩበት፣  ሃሰተኛ   መረጃዎቸን በተደራጀ  መልክ የማጣራት ስራና  ልምድ  ገና  በእንጭጩ የሚገኝ  በመሆኑ የሃሰተኛ መረጃዎችን መጠነ- ሰፊ  ጉዳት  መረዳት  ይህን   ያክል   የተወሳሰብ  ፍልስፍና  አይሆንም።

በመሆኑም ሃሰተኛ  መረጃዎች  የህዝብን  አብሮ  የመኖር እሴት  የሚሸረሽሩ፣ ተከባብሮ  እና  ተዋዶ  ለመኖር የሚረዱ  አስተሳሳሪ  ድሮች  መንምነው  እንዲቆረጡ  የሚያደርጉ፣ የህዝብን  ሰላምና ደህንነት በማወክ   ወደ ተስፋ  መቁረጥና ባስ  ሲልም  መረር   ወዳለ  ሁኔታ የሚገፋፉ   ሁኔታዎችን እንዲፈጠሩ   በማድረግ ረግድ አሉታዊ ተጽዕኗቸው   ከፍተኛ  ነው።

የሃሰተኛ  መረጃዎችን መዘዝ   እንደሚከተለው በተጨባጭ  ምሳሌ  ማስረዳት  ተገቢ  ነው።  በ2011  ዓ/ም ጥቅምት   ወር  ላይ  የተፈጸመው  አሳዛኝ  ክስተት   ሃሰተኛ   መረጃዎች   የሚያስከትሉትን  ጉዳት  ለመረዳት አይነተኛ   ማሳያ  ነው።  ነገሩ   እንዲህ   ነው፡   አንድ   የሶስተኛ   ዲግሪ   ተማሪ  ለሚሰራው   ምርምር  ግብዓት የሚሆን መረጃ  ለመሰብሰብ  ወደ  በአማራ  ክልል ምዕራብ  ጎጃም ዞን  ጎንጂ  ቆለላ ወረዳ  ወደ  አዲስ  አለም ከተማ ያመራል። ይህ  ተመራማሪ ብቻውን አልነበረም፤ ይልቁንም መረጃውን  ለመሰብሰብ ከሚያግዘው ጓደኛውና  ለዚሁ  ስራ  ከወረዳው  ከተመደበ የላብራቶሪ  ቴክኒሻን  ጋር  እንጂ።  የሚሰበሰበው መረጃ  በአዲስ አለም  ከተማ  የአንደኛ   ደረጃ  ት/ቤት   ተማሪዎች  ምራቅና  አይነምድር  መውሰድ  ነበር።   እነዚህ   ሰዎች ከተማሪዎች  አስፈላጊውን   ናሙና  እየወሰዱ    በነበረበት    ወቅት   ግን   አንድ   ያልታሰበ  ነገረ   ተፈጠረ። ባለሙያዎቹ   ለተማሪዎች  ክትባትና   በመርፌ   እየወጉ    መድሃኒት   እየሰጧቸው  ስለሆነ    ተማሪዎች እየታመሙና እየሙቱ እንደሆነ ተደርጎ  በተወሰኑ የከተማ  ወጣቶች  ዘንድ  ሃሰተኛ  ወሬ  ተናፈሰ።  ይህንን ሃሰተኛ   ወሬ  ተከትሎ   በመቶዎች የሚቆጠር   የከተማው  ህዝብ  ወደ  ት/ቤቱ  በመሄድ መረጃ  ከተማሪዎች እየሰበሰቡ   የነበሩትን  ሁለት   ባለሙያዎች በድንጋይ  በመውገር   የገደላቸው   ሲሆን   ከወረዳው  የተላከው የላብራቶሪ  ቴክኒሻን   ክፉኛ  ተጎድቶ   ሆስፒታል ገብቶ  እንደነበር  የሚታወስ  ነው።  በዚህ  ሃሰተኛ   መረጃ ምክንያት  ብዙ  ተስፋ  የሰነቁት  ተመራማሪዎች በአጭሩ ተቀጩ።  ሃሰተኛ   መረጃዎች  ለተቋማት  ንብረት ውድመትም መንስኤ  የሚሆኑባቸው  አጋጣሚዎችም በርካታ   ናቸው።

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *