ኢትዮጵያ:- ባለፈ ታሪክ የምትዋልል አገር…..

የሚጋጩ የታሪክ ትርክቶችን ለማስታረቅ የተደረጉ ሙከራዎች ቢኖሩም፣ ዛሬ ላይ የሚታየውን የታሪክ እና ብሄር እና ቋንቋ ተኮር ጉዳዮች ውህደትን ለመነጠል የሚደረጉ ጠንካራ ጥረቶች ሲደረጉ ግን አይታይም። በተቃራኒው አንድን የታሪክ ትርክት ከሌላው አስበልጦ በመምረጥ ህጋዊ ለማድረግ የሚደረጉ ጥረቶች የሀገሪቷ ልሂቃን የየእለት ተእለት ተግባር ሆኖ ቀጥሏል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ፤ ከፋፋይ የታሪክ ገጾችን የመዘንጋት እና ታሪካዊ ማንነቶችን የማረም ይፋዊ ፍላጎቶች ማዘንበል እና መታየት ጀምረዋል። እንዲህ ያሉ ከአለፈ ታሪክ ለመራቅ የሚደረጉ ጭፈን እምቢተኝነቶች ለሚቀርቡ ታሪካዊ የኢፍትሃዊነት ጥያቂዎች መልስ ሊሆን አይችልም። ሆን ተብሎ የሚደረግ ታርክን የመዘንጋት ድሮ የተደረጉ ኢፍትሃዊ ተግባራትን እንደ መደገፍ እና እንዲህ ያለውን ጥያቄ የሚያነሱ ቡድኖችን እንደመናቅ ሊቆጠር ይችላል። አሁንም ድረስ ቀድሞ በተፈጸሙ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶች ተጠቂ የሆኑ ፖለቲካዊ ማህበረሰብ አባሎችን ሆን ብሎ የመናቅ ተግባር ተደርጎም ሊታይ ይችላል።

ኢትዮጵያ ልትጠቀም የምትችለው በጋራ መማከር እንጂ በጋራ በማስታወስ ወይም መዘንጋት አይደለም። አንዱ የሌላውን ታሪካዊ ክርክሮችን ህጋዊነት በማክበር ጥቅም እና አቋም በማይነካ በቀጥታ በሚደረግ ድርድር፤ ዛሬ ከሚታየው የታሪክን ከብሄር እና ቋንቋ ጋር መዋሃድ መነጠል ይቻላል። የሁሉንም እውነት ህጋዊ ማድረግ እና ለህዝብ የሚደርስበትን መንገድ ማመቻቸት፤ የተለያዩ ብሔራዊ እንቅስቃሴዎች የያዙትን ብሔራዊ ኩራት እና ውርደት ስሜት መሃል ያለውን ሚዛን መጠበቅ አስፈላጊ ነው። በታሪክ የተደረጉ ኢ-ፍትሃዊነቶችን እና ስኬቶችን ሙሉ እውቅና መስጠት እና ተቀባይት እንዲያገኝ ማድረግ አዲስ ፖለቲካዊ ማህበረሰብን ለመፍጠር የሚያስችል መሰረት ለመገንባት ትልቅ አንቀሳቃሽ መርህን ያካትታል። ይህም ያለፈው ቁስል እንዲሽር እና አሁን ያለውን የእውነታ አረዳድ ለማስተካከል እና የጋራ የወደፊት ራዕይ እንዲኖር ያግዛል።

የጋራ መማከር እና ምልከታ የሌላውን እውነት መፍቀድ ብቻ ያካተተ ሳይሆን፣ የብሔርተኛ እንቅስቃሴዎች እና መሪዎቻቸው ያለፈ ታሪክን ፖለቲካዊ ከማድረግ እንዲቆጠቡ የሚደረጉ ጣልቃ ገብነቶችንም ማካተት አለበት። በማህበረሰብ አንቂዎች የሚደረጉ ታሪክን ዳግም የመተንተን ሁነኛ ሚናዎች ቁጥጥር ሳይደረግባቸው መታለፍ የለባቸውም። እውነተኛ ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነቶችን በየእለት ተእለት ከሚፈበረኩ ሃሰተኛ ታሪኮች የመነጠል ተግባር ላይ የሚደረጉ ጣልቃ ገብነቶች ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል። የእርቅ ሂደቶች በሁሉም ደረጃዎች መደረግ ያለባቸው ሲሆን፤ ትርጉም ያለው የፖለቲካ ውሳኔዎች የተገለሉ ሁሉንም ማህበረሰቦች ያካተተ መሆን አለበት።
ምንም እንኳ በገሃድ ከሚታዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በዘለለ፤ ያልተሳኩ ሃገር የመገንባት ጥረቶች እና ማንነት-ተኮር ብሄርተኝነት ባላፈ የሌሎችን እውነት ከመረዳት የሚያግድ ሌላ ነገር ያለ ይመስላል። ከፖለቲካ በላይ የሆነ ነገር እንደማለት ነው::

ላለፈ ታሪክ ያለን ልዩ ፍቅር፣ በአፈ-ታሪክ እና ተለዋዋጭ ዘይቤ የሚንጸባረቅ ሲሆን፣ በሀገር ውስጥ በሚገኙ ዋነኛ ሃይማኖቶች ጭምር ይሁንታን በማግኘት የጸና ሆኗል። ምናልባትም የጊዜ እና በቅድመ-ፖለቲካዊ የባህል ስዋሰዋችንን ምክንያታዊ መረዳት መመርመር አለብን። አሁን ያለንበት እውነታ ገጽታ ተሞክሮ ወደ የሆነ የምንኖርበትን አለም መዋቅር እና የእኛ በውስጡ መኖርን ያመላክታል። የማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ተሞክሯችን መሰረታዊ እሳቢ የቅድመ–ፖለቲካ መነሻ ክስተት ለውጥን ማስተካከያ ማድረግን የሚሻ ነው። ስነ- ምግባርን፣ መልካምነትን፣ ፍትህን፣ ውበትን፣ ጊዜን እና የመሳሰሉትን የተመለኩቱ ያሉን እሳቤዎች አዲስ ፖለቲካዊ ምናባዊ ፈጠራ እንዲኖረን ያስችላሉ።
በመሆኑም አሁን የያዝነውን እውነታ ቅርጽ የገነቡ በውስጠ ታዋቂ የሆኑ ስነ-ፍጥረታዊ መላምቶቻችንን በመመርመር አሁን የሚታየው የእውኔታዎቻችን ተሞክሮ ያላፈ ታሪካችንን እንዲመስል የሆነበትን ምክንያት በጥልቀት እንድንረዳ እና ለምን እንደዛ እንደሆነ እንድንጠይቅ ያስችለናል።

ፌደሪኮ ካምፓኛ የሚባል ምሁር እንደሚያነሳው “ለምሳሌ አሁን ያለንበት ጊዜ ልዩ የሚያደርገው ዋና መሰረት ከሌሎች ያለፉ ጊዜያት ጋር ምን ይለየዋል? እንዲህ እና እንዲያ ያሉ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ገጽታዎች እንዲፈጠሩ ምን አይነት መሰረታዊ በስነ-ፍጥረት ደረጃ የሚደረጉ ግምቶች ወሳኝ ናቸው? እንዲህ እና እንዲያ ያሉ ማህበራዊ ልማዶችን ለማስተናገድ ወሳኝ የሆኑ ነገሮች መኖር እና አለመኖር የሚያስችሉ ነገሮች የትኞቹ ናቸው? በአሁን ወቅት የሚገኙ ማህበራዊ ተቋማት ስነ-ምግባራዊ አላማዎችን እውነታ ፍትሃዊ ለማድረግ ምን ያስፈልጋል?” የሚሉ እና ሌሎችም ጥየቄዎችን ማንሳት ተገቢ ነው።

አሁን ወደ ኋላ መመለስ የማንችልበት ቦታ ደርሰናል። ያለፈ ታሪክን የተመለከቱ መሰረታዊ አለመግባባቶች ወደ አላስፈላጊ ደም መቃባቶች መርተዋል። በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የውስጥ ጦርነቶች ሃገሪቷን እያፈረሱ ይገኛል፤ እንዲህ ያለውን ብጥብጥ እንዲከሰት ከሚያደርጉ ነገሮች አንዱ ያለፈ ታሪክ ፖለቲካ አንዱ ነው። ከዚህ ማምለጥ የማንችል ከሆነ፤ ቢያንስ ያለፈ ጊዜ ጨለማ ጥላዎች እንዲደበዝዙ ለማድረግ መሞከር ተገቢ ነው። አዲስ ፖለቲካዊ ምናባዊ እሳቤ ለመፈጠር፤ አዲስ ፖለቲካዊ አማራጮችን ማሰብን፣ እና አርቆ ማየትን ይሻል። ህልውናዊ መጥፋትን ለመጋፈጥ ረዘም ያለ የጊዜን ማሰላሰልን ይጠይቃል። ጊዜ ባዶ ነገር አይደለም፡ ወደ ፊት ሊሆን የሚችለውን አማራጭ እና የወደ ፊቱን ማሳያን በውስጡ አካቷል። “በጊዜ ውስጥ” ዕውቁ የሥነ-መለኮት ተመራማሪ ፖል ቲሊች እንደሚለው “የወደፊት ነገራችንን እንወስናለን፣ እኛም በጊዜ እንወሰናለን”። ይህን በተመለከተ፣ ስመ-ጥሩ ባለቅኔ ከበደ ሚካኤል ‹‹ዓለም እና ጊዜ›› የተሰኘው ስራው፣ የህልውናን እውነታ ካለፈ ጊዜ ጋር ያለውን ግንኙነት ማሰብ መታለል እንደሆነ እንደሚከተለው አስፍሮታል፡
አንዱ ስፍራ ሲለቅ፥ አንዱ እየተተካ፣
ሁሉም ርስቴ ነች፥ እያለ ሲመካ፣
ሞኝነት አድሮብን፥ ሳናስበው እኛ፣
ዓለም ሰፈር ሆና፥ ሕዝቡ መንገደኛ፣
ትውልድ ፈሳሽ ውሃ፥ መሬቷም ዥረት፣
መሆኑን ዘንግቶ፥ ይህ ሁሉ ፍጥረት፣
ስትመለከቱት፥ በሰልፍ ተጉዞ፣
ሁሉም በየተራው፥ ያልፋል ተያይዞ።

(ከበደ ሚካኤል፣ የቅኔ አዝመራ)

በታሪካዊ ጊዜ ውስጥ በመኖራችን ምክንያት ብቻ፤ “በምድራዊው ማለፍ” ውስጥ “ዘላለማዊው ሲገለጥ”፤ እና አሁን ካለው ጊዜ በዘለለ የሰዎችን (ፖለቲካዊ) አማራጮች መመልከት እንችላለን። ያለፈ ታሪካችንን ለመደራደር፣ ለማከም፣ እና ዳግም ለማጣመር ማህበረሰባዊ እና መንግስታዊ ተቋማት እና የማህበረሰብ ባህልን የማዳበር ሂደት፣ እውነተኛ ብዝሃ-ባህል፣ ዲሞክራሲያዊነት እና የመሳሰሉትን ብቻ ሳይሆን፤ በፍልስፍና፣ ሥነ-ልቦና፤ ሥነ-መለኮት፣ ስነ-ጥበብ፣ እና ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ለውጥ ማምጣት የሚችሉ ምክንያቶችን ማገናዘብ የሚችሉ ሌሎች መስኮች ላይ የተሰማሩ ባለሞያዎች የተለየ ጥረት እና ራዕይን ይጠይቃል።

ኢትዮጵያ ካለፈ ታሪክ ትውስታ ውጥረት መላቀቅ አለባት። ብሔርተኛ ልሂቃን እንዲሁም ማህበረሰቡ በአጠቃላይ ማለቂያ የሌለው የማህበረሰብ ለውጥ እና እድገት ማምጣት የሚያስችልበትን መንገድ ማሰላሰል አለባቸው። ሆን ተብሎ በሚደረጉ ማሳሳቻዎች እና የታሰበባቸው ውሸቶች ታሪክን ለማወክ የሚደረጉ ሙከራዎችን የሚያካሂዱ የፖለቲካ ሃይሎች ሊወገዙ እና ያለፈ ታሪክ ከፋፋይ ሁነቶች በመዋቅራዊ እና ቅድመ- ፖለቲካዊ ደረጃ ሊመረመሩ ይገባቸዋል።

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *