በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀፅ 12 ንዑስ አንቀፅ 2 ረ መሠረት ምክር ቤቱ አብላጫ ድምፅ ያገኘውን የብልፅግና ፓርቲ ተወካይ ዕጩ ተሿሚዎች ያቀረበ ሲሆን፣ በዚህ መሠረት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ  ለምክር ቤቱ ያቀረቧቸው የምክር ቤቱ የመንግሥት ተጠሪ፣ ረዳት ተጠሪና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የተለያዩ ቢሮዎች ኃላፊዎችን ምክር ቤቱ ተቀብሎ አፅድቋል።

tender

ከንቲባዋ ባቀረቡት ዝርዝር መሠረት አቶ መለሰ ዓለሙ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ፣ አቶ ጃንጥራር ዓባይ ምክትል ከንቲባና የሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙ ሲሆን፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ደግሞ አምስት ኃፊዎች ተመርጠዋል፡፡ በዚህም መሠረት ወ/ሮ ነጂባ አክመል የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ጥራቱ በየነ የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ፣ ወ/ሪት ያስሚን ወሃብረቢ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ፣ ወ/ሮ ሒክማ ከይረዲን የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አቶ ዓለማየሁ እጅጉና አቶ ተተካ በቀለ የመንግሥት ረዳት ተጠሪ ሆነው በመሾም ቃለ መኃላ ፈጽመዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ዕጩ የካቢኔ አበላቱን ባስተዋወቁበት ወቅት እንደገለጹት፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የተመረጡትን ዕጩዎች ጨምሮ 24 የሚደርሱ የካቢኔ አባላትን ከብልፅግና ፓርቲ አቀርበዋል፡፡ ምክር ቤቱ በከንቲባነት ሲሾማቸውና በፓርቲያቸው አቋም መሠረት በአዲሱ ምክር ቤት የተለያዩ ድምፆች መሰማት አለበት፣ እንዲሁም የአመራር ስብጥር ሊኖር ይገባል በሚል ከተፎካከሪ ፓርቲዎች ለካቢኔ አባልነት ሁለት አባላት ተመርጠዋል፡፡

በዚህም መሠረት የኢዜማ አመራር የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ የአዲስ አበባ ከተማ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም የአብን ፓርቲ አመራር የሆኑት አቶ የሱፍ ኢብራሂም ደግሞ የመንግሥት ንብረት አስተዳደር ባለሥልጣን ኃላፊና የከተማው ካቢኔ አባላት ሆነው በአዲስ አበባ ምክር ቤት ተሹመዋል፡፡

አዲስ በተመሰረተው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የተለያዩ ቢሮ ኃላፊዎች ሹመት የተከናወነ ሲሆን፣ በዚህም መሠረት፣ በፌዴራል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት  የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት ቀንአ ያደታ(ዶ/ር) የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር የነበሩት  ሒሩት ካሳው (ዶ/ር) ደግሞ የባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሆነው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ወ/ሮ ጽዋዬ ሙሉነህ የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ጀማል አሊዬ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ዳዊት የሺጥላ የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተመረጡ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም በነበረው ካቢኔ የአዲስ አበባ ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አያልነሽ ሀብተማርያም (ኢንጂነር) የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ ኃላፊ፣  ዩሐንስ ጫላ (ዶ/ር) የጤና ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ዘላለም ሙላቱ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ሙሉጌታ ተፈራ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ሆነው በከንቲባዋ ተመርጠዋል፡፡

ሙሉቀን ሀብቱ (ዶ/ር) የአዲስ አበባ የቴክኒክ ሙያ፣ ሥልጠናና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ  ፣አቶ አደም ኑር  የንግድ ቢሮ ኃላፊ፣  ሃና የሺንጉሥ (ዶ/ር) የሴቶች ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ አብርሃም ታደሰ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ እንዲሆኑ በወ/ሮ አዳነች አቤቤ የተመረጡ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪ

አቶ ዮናስ ዘውዴ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ጽጌሬዳ ወርቁ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም ዳዲ ወዳጆ (ዶ/ር) የፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።

ምንጭ – ሪፖርተር

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *