ያለፈው ጊዜ፣ አሁን ያለንበት እና የወደፊቱ በተለያየ መንገድ በመዋሃድ የእለት ተእለት የህይወት ተሞክሯችንን ቅርጽ ያስይዛል። ያለፈ ታሪካችን አስተሳሰባችንን በተለያየ መንገድ ለማምለጥ በማይቻል መልኩ ጫና ስለሚያሳድርብን፤ ያለፈ ታሪካችንን በምንም መንገድ ልናስወግደው አንችልም። ግለሰቦች እና የተለያዩ ቡድኖች እራሳቸውን የሚረዱት፣ የፖለቲካዊ እሳቤያቸውን የሚያሰረዱበት እና የማህበረሰብ ባህላቸውን የሚያዋቅሩት ተረቶችን፣ ትርክቶችን፣ እና የጥንት አፈ-ታሪኮችን በመጠቀም ነው።

ነገር ግን ቀደምት የአገዛዝ ስርአቶች ማህበረሰቦች ላይ የፈጠረው ጭቆና እና ሸክም አሁን ያሉ ማህበረሰቦችን ለወቀሳ የሚያነሳሳ ሲሆን ያለፉ የፍትህ መጓደሎችን መካድ እና ህጋዊ የማስመሰል ትርክቶች ሲጋለጡ፤ አሁን ያለንበት ወቅት ባለፈ ታሪክ ትንተናዎች እንዲዋጥና የወደፊት እርምጃን ውጤት አልባ ያደርገዋል። በመሆኑም ይሄ አይነት የታሪክ አረዳድ መፍትሔ አልባ ከመሆኑም በላይ በእንዲህ ከቀጠለ ማብቂያ ወደ ሌለው አዝቅት ውስጥ ሊከተን ይችላል።
ያለፈ ታሪክን እንዴት መረዳት አለብን የሚለው እሳቤ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ መድረክ የተለመደ መከራከሪያ መሆኑ ቀጥሏል። ያለፈ ታሪክ ትርጓሜ አሰጣጥ እጅጉን እየተራራቀ እና ጽንፍ እየያዘ መምጣቱ የመነጨው ከተለያዩ አከራካሪ የታሪክ ትርክቶች ሲሆን የሀገሪቱ ብሔራዊ ስነ-ልቦና ውስጥ ስር እየሰደደ መጥቷል።

ታሪክ እና ትውስታ እጅጉን እየተራራቁ ከመምጣታቸው ባለፈ በልሂቃን እና በማህበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ሚና እንዲኖራቸው ተደርጓል። እየተራራቀ የመጣውን ብሄራዊ ልዩነቶች ለማጥበብ ሲባል የኢትዮጵያ ታሪክን በወል ትምህርትነት (Common course)  ለመጀመሪያ አመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለመስጠት ያልተቻለ ሲሆን፤ ይህም ችግሩ ምን ያህል ስር የሰደደ መሆኑን ማሳያ ነው። ፖለቲካ የታሪክ አለም ውስጥ ጣልቃ እየገባ በመምጣቱ የታሪክ ተመራማሪዎች ራሳቸው የማስተማሪያ ርእሶች ምን መሆን እንዳለባቸው እንኳ መግባባት ላይ ሊደርሱ አልቻሉም። ምንም እንኳ በአሁኑ ወቅት በርካታ የትምህርት ዓይነቶች የመጀመሪያ አመት የዩኒቨርሲቲ ፕሮግራም ውስጥ የተካተቱ ቢሆኑም የኢትዮጵያ ታሪክ ግን እየተሰጠ አይደለም፤ ይህም በመሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ፍኖተ-ካርታው የተሟላ ሳይሆን ቀርቷል።

የ1960ው የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴን ተከትሎ በጥንት ታሪክ ላይ የተመሰረተው የኢትዮጵያ ሀገር ምስል በተለያዩ ክፍልፋይ ምስሎች፣ ማንነቶች እና ታሪካዊ ሐተታዎች ጥያቄ ውስጥ ገባቷል። የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ ገጽታዎች በኤርትራውያን፣ ሶማሌዎች፣ ኦሮሞዎች እና አማራዎች ጽኑ ልዩነቶች ውስጥ የገባ ሲሆን፤ ዳግም አንድ የመሆን እና የክልሎች ራስን ማስተዳደር በአንድ ወገን በመሆን የሃይል የበላይነት በሌላ በመሆን ያለፉት መንግስታት የተለያዩ መገለጫዎች ሆነዋል። ያለፈ ታሪክ ንግርቶች መሃል ትልቅ ልዩነት ያለ ሲሆን፤ አንደኛው ወገን የታሪክ ቀጣይነት፣ አንድነት፣ እና ባህላዊ ማንነት፤ በተቃራኒው ወገን ደግሞ ወረራ፣ ሌሎችን መጫን እና ልዩነት ላይ ማተኮር ይታይበታል።

በተመሳሳይ በ1990ዎቹ የብሔርተኝነት መንሰራፋት እና የታሪክ አረዳድ እና የታሪክ ትንታኔ አለመግባባቶች በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሀተታ ውስጥ የበላይነት እንዲይዝ አድርጎታል። አዲስ የታሪክ ገለጻዎች የብሄር ስብስብ ትዝታዎች ከምንግዜውም በላይ እንደ አዲስ እንዲዋቀሩ አድርገዋል። ከዚህ በተጨማሪም በ2010 ዓ.ም የተከፈተው ፖለቲካዊ ምሕዳር ሌላ ታሪክን የተመለከተ ክርክር እና ሐተታ ማእበል እንዲነሳ አድርጓል።
የኢትዮጵያውያን የታሪክ ትውስታ በተመለከተ ጀዋር መሃመድ የሚያራምደው አቋም፤ ሐገሪቱ የገባችበትን አጣብቂኝ የተሻለ ማሳያ ነው። ይህን በተመለከተ ጀዋር ቃለ-መጠይቅ ከማድረጉ በፊት የአኖሌ ሀውልትን የጎበኘ ሲሆን፤ የዛኑ እለት ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ በዳግማዊ ሚኒሊክ ቤተ መንግስት ውስጥ የሚገኝውን የአንድነት ፓርክ ምርቃት ስነ-ስርአት አካሂዶ ነበር ። ጀዋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ በ ‹‹ፖለቲካ ታሪካዊ ትውስታ›› ላይ የተመሰረተ ተግባር መሆኑን ገልጾ፤ ማንኛውም ሰው ዳግማዊ ምኒልክን፣ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴን ወይም የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስን ለማወደስ ቢሞክር ‹‹ሰይጣናዊ ተግባራቸውን›› አጋልጣለሁ ብሏል። ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ ያለፈ ታሪክ ትንተና ሁለት አማራጮች ብቻ እንዳሉት የተናገረ ሲሆን፤ እነዚህም፡ የታሪክ ምእራፉን መዝጋት አልያም ሁሉም የታሪክ ትንታኔዎች ይፋዊ መገለጫ መንገድ ማግኘት መቻል አለባቸው በማለት ላለፈ በድርድር ላይ ለተመሠረተ የታሪክ እውነታ ምንም አማራጭ አልተወም። በመቀጠልም ‹‹የተጨቆኑ፣ የድሃዎች፣ እና የተጠቂዎች ታሪክ መነገር አለበት›› የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሷል።

ሌሎች ማሳያዎች እንዳሉ ሆነው፣ እስካሁን እንደቀጠለ ያለው አከራካሪው የዳግማዊ ምኒሊክ ፈረሰኛ ሃውልት ጉዳይ በሀገሪቷ ውስጥ ያለውን ያለፈ ታሪክን የተመለከተ ማህበራዊ ክፍፍል ሁነኛ ማሳያ ነው። በ 1984 ዓ.ም የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ብዛት ያላቸው ሰልፈኞችን በመጥራት ዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ አደረገ፤ ሰልፈኞቹም የምኒሊክን ሃውልትንም በጥቁር መጋረጃ በመሸፈን ሃውልቱ በፍጥነት እንዲወገድ ጥያቄ አቀረቡ። ከጥቂት ቀናት በኋላ ብዛት ያለው ህዝብ የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ ጥቁሩ መጋረጃ እንዲወርድ እና ሃውልቱን ማሳደሻ ገቢ አሰባሰቡ። አሁንም ድረስ የህዝቦች አለመግባባት የቀጠለ ሲሆን፤ በ2011 ዓ.ም ሀውልቱ እንዲፈርስ በሚፈልጉ የኦሮሞ ማህበረሰቦች እና ሃውልቱ እንዲጠበቅ በሚፈልጉ ሰዎች መሃል በተነሳ ግጭት የህይወት እልፈት እንደተከሰተ ተዘግቧል።
እንዲህ ያሉት በታሪክ ምክንያት የሚነሱ መሰረታዊ እና ለሞት የሚዳርጉ ጉዳዮች ዋነኛ መንስኤ ተደርገው የሚወሰዱት የሃገሪቱ ብሔረተኛ ልሂቃን የሚጫወቱት ሁነኛ ሚና መሆኑ ይታመናል።

የተለያየ ብሔርተኝነትን የሚያቀነቅኑ ፖለቲከኞች እና ማህበረሰብ አንቂዎች ትኩረታቸውን ብሔራዊ ውርደቶች እና ብሄራዊ ኩራቶች ጫፍ ላይ በማድረግ፤ የታሪክን ምስል በመፍጠር፣ በማዛባት እና ዳግም በማዋቀር፤ እንዲሁም ሆን ብለው ታሪክን በመዘንጋት እና በማስታወስ ለጊዜያው ጥቅማቸው ያውሉታል። ምንም እንኳ እኚህ ታሪክን የተመለከቱ አለመግባባቶች የሚመነጩት ከራሱ ከታሪክ ሳይሆን የፖለቲካ ልሂቃን ብሄራዊ ማንነትን ዳግም ለመፍጠር በማለም ታሪክን እንዳሻቸው በመጠምዘዝ እና በማዛባት ስለሚጠቀሙበት ነው። በመሆኑም፡ ፖለቲከኞች እና የህዝብ እሳቤን የሚመሩ ሰዎች ቀዳሚ የታሪክ ተንታኞች ሆነዋል።

በዚህም መልኩ፣ ያለፈ ታሪክን በማስተካከል የሚችለው አካል የተለያዩ ገጽታዎችን መቆጠጣር እንደሚችል መታያቱ፣ የብሔረተኛ ሊሂቃን፣ መሪዎች እና የማህበረሰብ አንቂዎችን እንቅስቃሴ የሚወስን ይመስላል። እኚህ እርስ በርስ የሚጋጩ የታሪክ ምስሎች ከቡድኖች ማንነት ምስረታ እና ህልውናቸውን ማስቀጠል ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፤ እንደ ታሪካዊ መነሻ፣ ወርቃማ ጊዜ፣ የቦታ ማጣት፣ የድሮን መናፈቅ፣ እና ጊዜ ወዘተ… በመሆኑም ታሪክ ላይ የሚደረግ ትግል የማህበረሰብ ማንነት ላይ የሚደረግ ትግል ሆኗል።
ያለፈን ታሪክ ሰዎች የሆነ ተግባር እንዲፈጽሙ የስሜት ማነሳሳት እና መቀስቀስ፣ ተቀባይነት እንዲኖራቸው ማድረግ፣ እና የማህበረሰብ ባህል ሁነኛ አንቀሳቃሽ መሆን እንዲችሉ በማስቻሉ፤ አሁን ላይ የጋራ ብሄራዊ ምልክቶችን፣ ትርክቶችን፣ እና የተለያዩ ዘር-ብሔር ያላቸው ቡድኖች ብሔራዊ ጀግኖችን መጋራት አስቸጋሪ እንዲሆን አድርጎታል።

እንዲህ ያለው አለምን የመረዳት ግጭት ከዘለቀ፤ ሐገር ከመፍረሷ በተጨማሪ፤ ያለፈ ታሪክ መዘከር የማይችልበት እና የወደፊቱ ባዶ የሚሆንበት ጨለምተኛ የፖለቲካ ዐውድ ሊገነባ ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ ምድራዊ ገነትን ቃል የሚገባ የድሮውን ናፋቂ አክራሪ ቡድን ሊያብብ ይችላል። ነገር ግን ፖለቲካዊ እና መዋቅራዊ ብቻ ሳይሆን ቅድመ-ፖለቲካ ተግባራዊ መሆን ከተቻለ ጨለማውን መሻገር ይቻላል።

ምንጭ – ፀባኦት ወርቅአበባ መላኩ

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *