የአሜሪካ መንግሥት የተራድኦና የልማት ድርጅት (USAID)፣ የምግብ ዕርዳታ ለተዋጊ ወታደሮች እንዲደርስ አድርጓል በማለት የሚሰነዘሩ ውንጀላዎችን እንደማይቀበል አስታወቀ። ተቋሙ ሰኞ ነሐሴ 17 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በተለያዩ አካባቢዎች የሚያቀርበውን የምግብ ዕርዳታ ሥርጭት እንደሚከታተልና በዚህም ዕርዳታው ለተቸገሩ ነዋሪዎች እንጂ ለተዋጊ ወታደሮች አለመሰጠቱን እንደሚያረጋግጥ አስታውቋል።

በመሆኑም የምግብ ዕርዳታ ሆነ ተብሎ ለወታደሮች ተሰጥቷል የሚል ውንጀላን ሙሉ በሙሉ እንደማይቀበል ገልጿል። ነገር ግን ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች የሚቀርብ የምግብ ዕርዳታን፣ በግጭቱ የሚሳተፉ ወታደሮች ከተረጂዎች እንደሚሰርቁ (እንደሚነጥቁ) የሚታወቅ እውነታ እንደሆነ ጠቁሟል።

ተቋሙ ይህንን መግለጫ ለማውጣት ምክንያት የሆነው ሰሞኑን በመከላከያ ሠራዊት የተማረከ አንድ የሕወሓት ተዋጊ ጦር አባል፣ ለተረጂዎች የሚቀርብ አልሚ ምግብ በእጁ በመገኘቱ ምክንያት በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ስሙ በመነሳቱ ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሬድዋን ሁሴን ለትግራይ ክልል ተረጂዎች የሚቀርብ የምግብ ዕርዳታ በሕወሓት ወታደሮች እጅ ላይ በተደጋጋሚ መገኘቱን ገልጸው፣ ይህንን ጉዳይ ከድርጅቱ ጋር ማገናኘት ግን ትክክል እንዳልሆነ በትዊተር ገጻቸው ላይ አሳስበዋል።

ነገር ግን የዕርዳታ ምግብ በተማረኩ በሕወሓት ታጣቂዎች እጅ በተደጋጋሚ በመገኘቱ፣ የዕርዳታ ምግቡ እንዴት በታጣቂዎቹ እጅ ሊገባ ቻለ የሚለው ጥያቄ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ሁሉም የተራድኦ ድርጅቶች ሊመልሱት የሚገባ እንደሆነ አስታውቀዋል።

ምንጭ – ቢቢሲ

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *