የሚከተሉት አራት ስልቶች ክፍል አንድ ላይ ባየናቸው ፅንሰ ሐሳቦች ላይ በመመርኮዝ ጋዜጠኞች ለተደራሾቻቸው ስለ ግጭቱ የተሟላ ግንዛቤ እንዴት መስጠት እንደሚችሉ ያስረዳሉ። እነዚህ ስልቶች ወይም መመሪያዎች ክስተቶችን ከመዘገብ ባለፈ ለማውጣጣት የሚጠቅሙ ጥያቄዎችን እንድናነሳ ያስችለናል።

በግጭት አፈታት እና በሰላም ግንባታ ውስጥ የተሳተፉ ሰዎች የዜና ተቋማትን በተመለከተ ከሚያቀርቡት በጣም ከተለመዱት ቅሬታዎች መካከል አንዱ፣ ጋዜጠኞች በግጭት ተሳታፊ ቡድኖች ባሕሪ ላይ ብቻ ተመርኩዘው ሰዎች ድርጊቱን ለመፈፀም ያነሳሳቸውን ምክንያት ያለመመልከታቸው ጉዳይ ነው። በክፍል አንድ ላይ እንዳየነው የግጭቱን ዐውድ የማያሳይ ዘገባ የተዛባ ምሥል እንደሚያሳይ ግልጽ ነው።

በቅድሚያ በግጭት ተሳታፊ ወገኖች ለሚያከናውኑት ተግባር ትኩረት መስጠት ተደራሾች ለድርጊቱ መነሾ የሆነውን ጉዳይ በተመለከተ እርግጠኛ እንዳይሆኑ ያደርጋል። እንደነዚህ ዓይነት ዘገባዎች ቡድኖች በግዴለሽነት የነውጥ ወይም የተቃውሞ እርምጃ ውስጥ የተሳተፉ እንደሆኑ ሊያሳዩ ይችላሉ። ሰዎች የጉዳዩን ውስብስብነት መረዳት የሚጀምሩት ሁኔታውን ባገናዘበ መልኩ ክስተቱን መግለጽ ስንችል ነው።

ዮሃን ጋልቱንግ  ግጭትን ለመረዳት ለጋዜጠኞች ጠቃሚ መሆኑ የተረጋገጠ ሞዴል አቅርበዋል፦የግጭት ሦስቱ ማዕዘናት (ጋልቱንግ 1996፡)

የጋልቱንግ የግጭት ሦስት ማዕዘናት ግጭትን በትክክል ለመረዳት፣ ግጭቱን የሚፈጥሩ በማኅበረሰቡ ውስጥ ያሉ ተቃርኖዎችን (ዐውድ) መመልከት እንደሚያስፈልግ ያስረዳል። እንዲሁም ቡድኖቹ አንዳቸው ለሌላኛው ያላቸው አመለካከት በጠባያቸው ወይም ባሕሪያቸው ላይ እንዴት እንደሚገለጽ መረዳት አለብን። እነዚህ ሁኔታዎች አንዳቸው ሌላኛው ላይ ተፅዕኖ ያሳድራሉ። ቁጡ ባሕሪ ያላቸው አመለካከቶች የጠነከሩ እንዲሆን በማድረግ ቡድኑ ከሌሎች ጋር እንዳይቀራረብ ተፅዕኖ ያሳድራል።

ይህ ሞዴል የግጭት ዘገባ ለሚሰሩ ጋዜጠኞች ጠቃሚ ጥቆማዎች አሉት። ምክንያቱም ሪፖርቶች የተሟሉ የሚሆኑት ታዳሚዎች ባህሪን ሊረዱ እንዲችሉ የሁኔታውን አውድ የሚገልፁ ሲሆኑ እንደሆነ ስለሚያሳይ ነው። ቡድኖች አንዳቸው ለሌላቸው ያላቸውን አመለካከት ማወቅ አለብን። እንዲሁም እርስ በእርስ ለየሚተያዩበት መንገድ መነሻ የሆናቸው የኋላ ታሪካቸውንም መመርመር ይኖርብናል።

ምናልባት ለግጭቱን መንስኤ የሆነውን ነገር ሙሉ በሙሉ ላንረዳው እንችላለን። ነገር ግን በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉንም ወገኖች ማናገር እና በነሱ በኩል ስለ ክስተቱ እንዲያስረዱ እድሉን መስጠጥ በጣም አስፈላጊ ነው።

4.2 ከመነባንብ ባሻገር ማግኘት

ቡድኖች ግጭትን ከተፎካካሪነት አንፃር ሲመለከቱ ምን እንደሚፈልጉ እና ተቀናቃኝዎቻቸው ምን ዓይነት ጠባይ ሊኖራቸው እንደሚገባ የሚሰማቸውን የተለያዩ ፍላጎቶች የመግለጽ ዝንባሌ ይኖራቸዋል። ሆኖም እነዚህ ፍላጎቶች በአጠቃላይ የቡድኑን እውነተኛ ፍላጎቶች የሚወክሉ መሠረታዊ ፍላጎቶችን የሚደብቁ አቋሞች ብቻ ናቸው። በብዛት ቡድኖች እንፈልጋለን ብለው በሚያወሩት (አቋም) እና የእውነት በሚፈልጉት (ጥቅም) መሐል ትልቅ ክፍተት አለ። እነዚህ ጥቅሞች ቡድኖቹ መሠረታዊ ችግሮቻቸው እንዲፈቱ በሚመርጧቸው መንገዶች ተካተዋል።

በግጭት ውስጥ ያሉ ቡድኖች ምንም እንኳን ትክክለኛው ፍላጎታቸው እና ጥቅማቸው በሌሎች መንገዶች ሊስተካከሉ ቢችሉም ከአቋማቸው ነቅነቅ ማለት አይፈልጉም። በዚህም ቡድኖች እርስ በርስ ግትር እና ሥምምነት የማይፈልጉ እንደሆኑ አድርገው በመመልከት ለተቀናቃኞቻቸው አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ሳያውቁ ይቀራሉ። ይህም ቡድኖች ለግጭቶች ፈጠራ የታከለበት መፍትሔዎችን የማግኘት ዕድል እንዳይኖራቸው ያደርጋል። ወይም የግጭቱን በጎ ለውጥ በከፍተኛ ሁኔታ ሊያዘገ

ጋዜጠኞች  ነገሩን  ከጅማሬው  አንስቶ  ለማወቅ  ሲፈልጉ  የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው፦:

 ግልጽ የሆነ ጥያቄ አቅርባችኋል፤ ለዚህ ጉዳይ መልስ የፈለጋችሁት ለምንድን ነው?

ጥያቄዎ የሚመለስበት ሌሎች መንገዶች አሉ?

ቡድኖቹ እነዚህ ጥያቄዎች በመጀመሪያ እንደተጠየቁ በግልጽ የመመለስ ዕድላቸው አነስተኛ ነው። ነገር ግን አጥብቀው መጠየቅ ሲጀምሩ ሊከታተሉት የሚችሉትን እውነተኛ ፍላጎታቸውን እና ጥቅማቸውን የሚያረዱበት ዕይታ ያገኛሉ። በአንዳንድ ሁኔታዎች ይህ ማለት ከቡድኖች ጋር ጊዜ በማሳለፍ ስለነሱ በደንብ ማወቅ እና እምነትን ማትረፍ ማለት ነው። በሌሎች ሁኔታዎች ሐሳባቸውን ማጋራት ከሚፈልጉ የተለያዩ ሰዎች ጋር መነጋገር ማለት ነው። በቡድኖቹ ውስጥ ላሉ የተለያዩ ሰዎች እነዚህን ጥያቄዎች ማቅረብም አስፈላጊ ነው። ይህን በማድረግ ፍላጎቶቹን የምር የቡድኖቹ አባላት ይጋሩታል ወይስ የመሪዎቹን አቋም ብቻ ነው የሚያንፀባርቀው የሚለውን መለየት ያስችለናል።

4.3 ጊዜ እና ቦታ ጥያቄ

ብዙ ጊዜ ግጭቶች ሲከሰቱ ተቀዳሚ ዜና መሆናቸው ሰዎች ግራ እንዲጋቡ ሊያደርግ ይችላል።

ስለ ድንገተኛ ነውጥ የሚሠሩ ዘገባዎች ተሳታፊ ቡድኖቹ ኢ-ምክንያታዊ እና ዓላማ ቢስ እንደሆኑ ያስቆጥራቸዋል። ጋዜጠኞች ግጭቱ የተከሰተበትን አካባቢ ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ማየት አለባቸው። ብዙ ጊዜ ግጭት ረጅም ታሪክ እንዳለው፤ እንዲሁም ግጭት በሁለት ቡድኖች መካከል የሚከሰት ቢሆንም ቅሉ ግጭቱን የተቀሰቀሰው ዋና መንስዔ በሌላ ቡድን አማካኝነት ሊሆን እንደሚችል ማሳየት በጣም አስፈላጊ ነው። ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን በሁለት ጎሳዎች መሐል በመሬት ይገባኛል የሚፈጠር ግጭት ነው። ግጭቱ የሚጀምረው ከዘመናት በፊት ቅኝ ገዢዎች ዘመን ጀምሮ ሊሆን ይችላል።

በአንድ አጋጣሚ ምን እንደተከሰተ ማለትም ፊት ለፊት የምናየውን መግለጽ አለብን። ነገር ግን ለዚህ ክስተት መነሻ የሆነ ያለፈ ታሪክ ካለም መጠየቅ ይኖርብናል። ግጭት ውስጥ የገቡ አካላት ግጭቱን ያባባሱ፣ አንዳቸው ለሌላቸው ያላቸውን አመለካከቶች እና ዕሳቤዎች እንዲይዙ ያደረጋቸው ምንድን ነው? በተጨማሪም ግጭት ውስጥ የገቡ ወገኖች በመካከላቸው ያለውን ውጥረት ለማርገብ ምን ማድረግ እንዳለባቸው መጠየቅ አለብን።

ግጭት በአንድ ጊዜ የሚቆም ክስተት ሳይሆን ቀጣይ ሒደት መሆኑን ማሳየት አለብን። ክሪስ ቺናካ ጋዜጠኞች ቡድኖቹ አቋማቸውን አለመቀየራቸውን ዘወትር ማረጋገጥ አለባቸው ሲል የሚከተለውን ቁልፍ ነጥብ አስቀምጧል።

ጋዜጠኞች ወጥነትን ማረጋገጥ አለባቸው። አንዳንድ ጊዜ ሰዎችን ብዙ ጊዜ ታናግራላችሁ እናም ተመሳሳይ ነገር የሚያወሩ ይመስላችኋል። ነገር ግን በመጨረሻ ከተናገሩት አቋማቸውን በትንሹ ቀይረውታል። (ጋዜጠኛው የቡድኑ ወቅታዊ አቋም ነው ብሎ በሚያምነው እና በቡድኑ ትክክለኛ አቋም መካከል) ወጥ አለመሆን ወይም ተቃርኖ ሊኖር ስለሚችል ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው ።አንድ ቡድን በተወሰነ ጉዳይ ላይ ብቻ (በጥቂቱም ቢሆን) አቋሙ መቀየሩ፥ አቋሙን ምንም ካለመቀየሩ እኩል አስፈላጊ ታሪክ ነው።

4.4 ጋዜጠኞች ማንሳት የሚችሏቸው ጥያቄዎች

ከላይ ለተነሱት ጉዳዮች ምላሽ የሚሆኑ ጋዜጠኞች ሊጠይቋቸው የሚችሉ የተወሰኑ ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው:

  • ግጭቱ ምንን በተመለከተ ነው? ተሳታፊ አካላት እነማን ናቸው? አላማቸውስ ምንድነው? ነውጡ ከሚደርስበት አካባቢ ውጪ ያሉ ሌሎች ተሳታፊ አካላት አሉ?
  • የግጭቱ ትክክለኛ  መነሻ  ምንድነው?  ምላሽ  የሚያስፈልገው  መዋቅራዊ አለመመጣጠን አለ? ከግጭቱ ጀርባ ያለው ታሪክ ምንድን ነው?
  • አንዱ ቡድን በሌላኛው ላይ ከሚያስፈራራው ውጪ ግጭቱ ስለሚኖረው ውጤት ምን ዓይነት ሐሳቦች አሉ?
  • ግጭቱ ሊፈታ የሚችልባቸው ፈጠራ የታከለባቸው መፍትሔዎች ወይም አዳዲስ ሐሳቦች አሉ? እነዚህ ሐሳቦች ነውጥን ለመከላከል በቂ ጫና ማሳደር ይችላሉ?
  • ነውጥ ቢቀሰቀስ የማይስተዋሉ ውጤቶች (እንደ ጥላቻ፣ የበቀል ምኞት፣ ራስን ከፍ ከፍ ማድረግ የመሳሰሉ) ወደፊት ሰላም የመምጣቱ ዕድል ላይ ምን ዓይነት ተፅዕኖ ያሳድራሉ?
  • ነውጥን ለመከላከል እየሠራ ያለው ማነው? ስለ ግጭቱ ውጤት ያላቸው ራዕይ ምንድን ነው?
  • ምን ዓይነት ዘዴዎች እየተጠቀሙ ናቸው? እና እንዴት መደገፍ ይችላሉ?
selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *