የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ አራት ከፍተኛ አመራሮች በመጪው ምርጫ በዕጩነት እንዲመዘገቡ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 2ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ሰጠ።

ችሎቱ ዛሬ ግንቦት 16 ቀን 2013 ዓም ውሳኔ መስጠቱን የባልደራስ የሕግና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሔኖክ አክሊሉ ለሪፖርተር ገልጸዋል ።

እንደ ኃላፊው ገለጻ፣ እነ አቶ እስክንድር ከመከሳሳቸው ባለ ፈ በፍርድ ቤትም ሆነ በሕግ የተጣለባቸው ክልከላ ስለሌለለ ፓርቲው ደረጃውን ጠብቆ እስከ ሰበር ችሎት ባደረገው ክርክር ተከሳሾቹ በእጩነት መመዝገብ እንደሚችሉ መወሰኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም እንዲመዘግብ ትዕዛዝ መሰጠቱን አክለዋል።

ምንጭ – ሪፖርተር

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *