የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቀጣዩ አገራዊ ምርጫ እስከ 50 ሚሊዮን የሚደርሱ መራጮች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታወቀ።

ቦርዱ ይህን ያለው ዛሬ 6ኛውን አገር አቀፍ ምርጫን አስመልክቶ እያደረጋቸው ያሉ ለምርጫው የሚያስፈልጉ ዝግጅቶች ሥራን ባስታወቀበት ወቅት ነው።

ቦርዱ እድሜያቸው ለመምረጥ ደርሶ በምርጫው ይሳተፋሉ ያላቸው ዜጎች ከአገሪቱ ሕብ ቁጥር ወደ ግማሽ የሚተጉ ሲሆኑ፤ በመላው አገሪቱ በምርጫው ድምጽ የሚሰጡባቸው 50 ሺህ 900 የምርጫ ጣቢያዎች እንደሚኖሩም አስታውቋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር የቤት ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የቀረበለትን በአገሪቱ ያለውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ግምገማና ምክረ ሐሳብ ተመልክቶ ከባለፈው ዓመት የተሸጋገረውን አገራዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ዝግጅት እንዲካሄድ መወሰኑ ይታወሳል።

በዚህም መሠረት ከድምጽ መስጫ ጣቢያዎች በተጨማሪ የመራጮች ምዝገባን የሚያከናውኑ 152 ሺህ 700 ሰዎችን እንዲሁም ለድምጽ መስጫ ቀን 254 ሺህ 500 ምርጫ አስፈጻሚዎችን እንደሚያሰማራም አስታውቋል።

በዚህ ዓመት ሊካሄድ እንደሚችል ለተጠቆመው አገራዊ ምርጫ በአምስት ቋንቋዎች የተዘጋጁ የመራጮች መዝገቦች መዘጋጀታቸውም ተገልጿል አስታውቋል።

የምርጫውን ተአማኒነት ለማረጋገጥም መራጮችም የሚወስዱት ለማባዛት እና አስመስሎ ለማተም የማይቻል የደኅንነት መጠበቂያ ያለው የመራጮች መታወቂያ ካርድ መዘጋጀቱንም አስታውቋል።

ቦርዱ እንደ ድምጽ መስጫ ሳጥኖች፣ የሚስጥር ድምጽ መስጫ መከለያዎች፣ ማስፈጸሚያ ቁሳቁሶች የያዙ ቦርሳዎች፣ የጠረጴዛ ባትሪ የመሳሰሉ ለምርጫ ቀን የሚውሉ ቁሳቁሶችን ማዘጋጀቱን አስታውቋል።

ቦርዱ ከወዲሁ የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶችን እያከናወነ መሆኑን ገልጿል። ስድስተኛው አገራዊና ክልላዊ መርጫ ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ይካሄዳል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ ሲሆን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ወደዚህ ዓመት እንዲተላለፍ መወሰኑ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባላት ሚና ምንድነው?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ካሉት አምስት የቦርድ አባላት መካከል አንዱ የሆኑት ጌታሁን ካሳ (ዶ/ር) ሰኞ ዕለት [መስከረም 18] በገዛ ፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስገባታቸው ይታወሳል።

ብርቱካን ሚደቅሳ (ወ/ሪት) የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሲሆኑ ቦርዱ ተጨማሪ አራት አባላት አሉ። ጌታሁን ካሳ (ዶ/ር)፣ አቶ ውብሽት አየለ፣ ብዙወርቅ ከተተ (ወ/ሪት) እና አበራ ደገፉ (ዶ/ር) የምርጫ ቦርድ አባላት በመሆኑ ሰኔ 2011 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሾማቸው ይታወሳል።

የቦርዱ አባላት ሚናቸው ምንድነው?

አምስት አባላት ያለው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ምርጫ እና ሕዝበ ውሳኔን በተመለከተ ከፍተኛውን የመወሰን ኃላፊነት የያዘ አካል ነው። በዚህም ቁልፍ ውሳኔን የማሳለፍ ስልጣን እንዳለው ይነገራል።

በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ 1133/2011 መሠረት ቦርዱ በሕገ መንግሥቱ እና በምርጫ ሕግ መሠረት የሚካሄድን ማንኛውንም ምርጫ እና ሕዝበ ውሳኔ በገለልተኝነት ያስፈጽማል።

የምርጫ ቦርድ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ደግሞ በምርጫ ሂደት የምርጫ ውጤትን የሚያዛንፍ የሕግ ጥሰት ተከስቷል ብለው ሲያምኑ ውጤቱን መሰረዝና ድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ የመወሰን ስልጣን አላቸው።

የሥራ አመራር ቦርዱ የምርጫ ቦርድ የመጨረሻው ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አካል ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን የምርጫ ውጤቶች ይፋ ከመደረጋቸው በፊት የምርጫ ውጤቶችን ያጸድቃል።

የምርጫ ሕጎችን ማስፈጸም፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን መቆጣጠር፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ድጎማ ማከፋፈል፣ ለምርጫ ታዛቢዎች ፈቃድ መስጠት እና መቆጣጠር፣ የምርጫ ቁሳቁሶችን ማሰናዳት እንዲሁም በጀት አዘጋጅቶ ሥራ ላይ ማዋል የሚሉት ከቦርዱ ስልጣን እና ተግባር መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

የቦርዱ አባላት እንዴት ይመረጣሉ?

የቦርድ አባላት የሚመረጡት ዝርዝር ሥነ-ሥርዓቶችን ተከትሎ ነው።

በቅድሚያ ጠቅላይ ሚንስትሩ እጩ የቦርድ አባላትን የሚመለምል ኮሚቴ ያቋቁሟሉ።

የዚህ ኮሚቴ አባላት ደግሞ ከተለያዩ የሕብረተሰቡ ክፍል የሚወጣጡ እና ገለልተኛ የሆኑ ግለሰቦችን ያቀፈ መሆን ይኖርበታል።

ከሐይማኖት ተቋማት፣ ከሳይንስ አካዳሚ፣ ከሠራተኞች ኮንፌዴሬሽን፣ ከንግድና ማኅበራት፣ ከሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እንዲሁም ከሲቪል ማኅበራት እና ከአገር ሽማግሌዎች የሚመረጡ ሰዎች የኮሚቴው አባላት ይሆናሉ።

ከዚያም ይህ ኮሚቴ የምርጫ ቦርድ አባል ሊሆኑ የሚችሉ እጩዎችን ጥቆማ ከሕዝብ፣ ከፖለቲካ ድርጅቶች እና ከሲቪል ማኅበራት ይቀበላል።

ኮሚቴው ከተጠቆሙት ሰዎች ውስጥ የቦርድ አባላት ሊሆኑ የሚችሉ እጩዎችን በመለየትና ፍቃደኝነታቸውን በማረጋገጥ የእጩዎቹን ዝርዝር ለሕዝብ ይፋ በማድረግ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ያቀርባል።

ጠቅላይ ሚንስትሩም የእጩዎቹ ስም ዝርዝር ከኮሚቴው ከደረሰባቸው በኋላ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር በቀረቡት እጩዎች ላይ ምክክር ያደርጋሉ።

ከምክክሩ በኋላ ጠቅላይ ሚንስትሩ እጩዎቹን ለሹመት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባሉ። ምክር ቤቱም የቀረቡት እጩዎችን በአብላጫ ድምጽ ሲያጸድቅ እጩዎቹ የቦርዱ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ሆነው ይሾማሉ።

የምርጫ ቦርድ አባላት እነ ማን ናቸው?

ብርቱካን ሚደቅሳ (ወ/ት) የቦርዱ ሰብሳቢ ሲሆኑ ቦርዱ ተጨማሪ አራት አባላት አሉ። ጌታሁን ካሳ (ዶ/ር)፣ አቶ ውብሽት አየለ፣ ብዙወርቅ ከተተ (ወ/ሪት) እና አበራ ደገፉ (ዶ/ር) የምርጫ ቦርድ አባላት በመሆኑ ሰኔ 2011 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሾማቸው ይታወሳል።

ብርቱካን ሚደቅሳ- የቦርድ ሰብሳቢ

ከሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በሕዝብ አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የሰሩት ብርቱካን ሚደቅሳ ቀደም ሲል የፌዴራል ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው አገልግለዋል። ብርቱካን ወደ ስደት ከመሄዳቸው በፊት በተቃዋሚ ፓርቲ አባልነት በፖለቲካው ውስጥ ይንቀሳቃሱ እንደነበረ ይታወቃሉ።

ብዙ የተባለለትን የ1997 ዓ.ም ምርጫን ተከትሎም ከተነሳው ውዝግብ ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ለእስር የተዳረጉ ሲሆን የዕድሜ ልክ እስራትም ተፈርዶባቸው ነበር። ከእስር ከወጡ በኋላ ወደ አሜሪካ ተጉዘው ጥናቶችን አድርገዋል።

ከሰባት ዓመታት ስደት በኋላም በ2011 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን እንዲመሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተሹመው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን በሊቀ መንበርነት እየመሩ ይገኛሉ።

አቶ ውብሸት አየለ – የቦርድ ምክትል ሰብሳቢ

አቶ ውብሸት አየለ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ምሩቅ ናቸው። በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በዳኝነት አገልግለዋል። ከዳኝነት ሥራቸው ለቀው የራሳቸውን ቢሮ በመክፈት የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ ሆነው ሠርተዋል።

አቶ ውብሸት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን በማማከር፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ውይይት በማስተባበር እንዲሁም በሌሎች የቦርዱ እንቅስቃሴዎች ላይ በሙያቸው ተሳትፎ ሲያደርጉ መቆየታቸው ተጠቅሷል።

አቶ ውብሸት በሲቪክ ማኅበራት እና ማኅበረሰባዊ እንቅስቃሴዎች ከፍተኛ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ ተጠቁሟል።

አበራ ደገፋ (ዶ/ር) – የቦርድ አባል

አበራ ደገፋ (ዶ/ር ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው። የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በሶሻል ወርክ እና ሶሻል ዴቨሎፕመንት ከአ.አ.ዩ አግኝተዋል። በተጨማሪም፣ በኔዘርላንድስ ከሚገኘው ኢንስቲትዩት ፎር ሶሻል ስተዲስ፣ በዓለም አቀፍ ሕግ እና ልማት የድኅረ ምረቃ ዲፕሎማ አላቸው።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመደበኛው የመምህርነት ሥራቸው ባሻገር በልዩ ልዩ ከፍተኛ ኃላፊነቶች በሙያቸው እንዳገለገሉ የሚነገርላቸው አበራ (ዶ/ር)፤ በዘመን ባንክ፣ በፍትሕ ሚኒስቴር የጠበቆች አስተዳደር ጉባኤ እና በኦሮሚያ የሕግ ጆርናል የቦርድ አባል በመሆን መስራታቸው ይጠቀሳል።

የምርጫ ቦርድ አባል ሆነው ከመሾማቸው በፊት በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕግ እና የፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባኤ እንዲሁም የአስተዳደር ወሰንና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባል ሆነዋል።

ብዙወርቅ ከተተ (ወ/ሪት– የቦርድ አባል

ብዙርቅ ከተተ(ወ/ሪት) የከፍተኛ ትምህርታቸውን ከኩባ ሐቫና ዩኒቨርሲቲ የውጪ ቋንቋዎች ትምህርት ክፍል በሥነ ቋንቋ የሁለተኛ ደረጃ ዲግሪ አግኝተዋል።

ብዙወርቅ (ወ/ሪት) በልዩ ልዩ ተቋማት አገልግለዋል። ከእነርሱም መካከል የቀድሞው የአደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፣ አክሽን ኤይድ ኢንተርናሽናል ይገኙበታል።

በግጭት አፈታት እና መከላከል ላይ በሚሠራው የጀርመን አማካሪ ድርጅት ውስጥም፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፕሮጄክት አስተባባሪ ሆነው ሠርተዋል።

ብዙወርቅ (ወ/ሪት) በመልካም አስተዳደር፣ በአቅም ግንባታ እና ሲቪክ ተሳትፎን በማበረታታት ላይ የሚሠራ፤ ‘ዜጋ ለዕድገት’ የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት መሥራች እና የቦርድ ሊቀ መንበር ሆነው አገልግለዋል።

ጌታሁን ካሳ (ዶ/ር) – የቦርድ አባል

ከቦርዱ ይፋዊ ድረ-ገጽ ላይ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ጌታሁን ካሳ (ዶ/ር) የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ያገኙት በ2010 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነው።

ጌታሁን ካሳ (ዶ/ር) በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ አገልግለዋል። በትግራይ ክልል የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ፣ በአዲስ አበባ እና በመቀለ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት መምህር እና ዲን፣ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኤግዚኪዩቲቭ ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል።

ጌታሁን (ዶ/ር) የተለያዩ የምርምር ጽሑፎችን በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ የኅትመት ውጤቶች ላይ ማሳተማቸውም ተጠቅሷል።

ጌታሁን ካሳ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አባል ሆነው ከተሾሙ በኋላ በኃላፊነታቸው ላይ ከአንድ ዓመት ብዙም ባልበለጠ ጊዜ ከቆዩ በኋላ ነው በፈቃዳቸው ሥራቸውን ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸው የተነገረው።

በዚህ አንድ ዓመት ውስጥ የቦርዱ ዋነኛ ሥራ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ስድስተኛ አገራዊና ክልላዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት በኋላ ወደዚህኛው ዓመት መሸጋገሩ ይታወሳል።

ከሳምንት በፊት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አገራዊው ምርጫ በዚህ ዓመት እንዲካሄድ ለማድረግ አስፈላጊው ዝግጅት እንዲደረግ ከወሰነ በኋላ፤ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚጠበቅበትን ለመወጣት ዝግጅት በሚጀመርበት ወቅት ከቦርድ አባላቱ አንዱ የሆኑት ጌታሁን ካሳ (ዶ/ር) ኃላፊነታቸውን ለመልቀቅ መወሰናቸው ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆኗል።

ጌታሁን ካሳ (ዶ/ር) ከቦርድ አባልነታቸው ለመልቀቅ መወሰናቸውን በመግለጽ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ ከማቅረባቸው ውጪ ምክንያታቸው ምን እንደሆነ የገለጹት ነገር የለም።

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *