ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም. እንዲከናወን ዕቅድ ለተያዘለት ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ 50 ሺሕ ገደማ የምረጫ ጣቢያዎች እንዲመሠረቱ የታሰበ ቢሆንም በፀጥታና ሌሎች ምክንያቶች ሳቢያ የተቋቋሙና የመራጮች ምዝገባን እያደረጉ ያሉት የምርጫ ጣቢያዎች ቁጥር 25,151 ብቻ እንደሆኑ ቦርዱ አስታወቀ፡፡

ቦርዱ የመራጮች ምዝገባን በተመለከተ ሚያዚያ 6 ቀን 2013 ዓ.ም. ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በሐያት ሪጀንሲ ሆቴል የመራጮች ምዝገባን አስመልክቶ ባካሔደው የምክክር መድረክ ላይ የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ እንዳስታወቁት፣ ምርጫ ጣቢያዎቹ ሥራ ያልጀመሩባቸው በዋናነት የፀጥታና የቁሳቁስ ማጓጓዝ ችግሮች ሳቢያ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

በተለይ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በአማራና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ያሉ የምርጫ ጣቢያዎችን ለማቋቋም በክልሎቹ የተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የፀጥታ ችግሮች ፈተና እንደሆኑ ተነግሯል። በአፋርና በሶማሌ ክልሎች የፀጥታና የዕቃ ማጓጓዝ ችግሮች በመታየታቸው ሳቢያ ምንም የምርጫ ጣቢያዎች አለመቋቋማቸውና የመራጮች ምዝገባም እንዳልተጀመረ ተነግሯል፡፡

ምንጭ – ሪፖርተር

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *