ትናንት ምሽት ሦሥት ሰአት አካባቢ በኦሮሚያ ክልል  ምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ገንቤል ወረዳ  ቦኔ ቀበሌ ውስጥ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በርካታ ንፁሀንን መግደላቸውን የኦሮሚያ ክልል መንግስት አስታወቀ።የክልሉ የጸጥታ ሃይል ድርጊቱ በተፈጸመበት ቦታ ደርሶ በጥቃት አድራሹ ቡድን ላይ የአጸፋ እርምጃ መውሰዱንም ተናግሯል።

ከለውጥ ሂደቱ በተቃራኒ በመቆም የጥፋት ሓይሎች ከሆኑት መካከል የሕወሓት ተላላኪ ሕገወጥ ቡድንና ኦነግ ሸኔ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ መሆናቸውንም የክልሉ መንግስት ተናግሯል፡፡ ሕገወጥ ቡድኑ የመንግስት መዋቅርን በማፍረስ የአፍራሽና የመተላለቅ ሰንሰለቱን ለማስፋት ሲታትር እንደነበር በግልጽ እንደሚታወቅና  ተላላኪው ኦነግ ሸኔ የጥፋት ሰንሰለቱን በገጠርና በከተማ በማስፋት በመንግስት አመራሮችና በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጭምር ዘግናኝ የሽብር ጥቃቶችን ሲፈፅም ቆይቷል፡፡

በዚህም የብዙ ንፁሃን ዜጎች ህይወት አልፉዋል፡፡ ከቀበሌ እስከ ክልል አመራር ድረስ የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል፡፡አያሌ  የግልና የመንግስት ንብረቶች ወድመዋል፡፡ የኦነግ ሸኔ እኩይ ተግባር ለማስወገድ መንግስት በወሰደው የህግ በላይነትን የማስከበር እርምጃ ሀይሉ እየተዳከመ የሄደ ቢሆንም፣ በሞትና በህይወት መካከልም ሆኖ የጥፋት ሴራውንና እርምጃውን መቀጠሉን ጠቁሟል፡፡ የኦሮሚያ  መንግሰት በምዕራብ ወለጋ ትናንት ምሽት የተፈጸመውን አሰቃቂና ዘግናኝ ጥቃትአውግዟል።

ምንጭ – ሪፖርተር 

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *