1.4 አስታራቂ እና አባባሾች
አንድ ግጭት በአራቱ የዕድገት ደረጃዎች አለፈም አላለፍም ግጭቱን በሚያስታርቁ እና በሚያባብሱ በርካታ ሁኔታዎች ይወሰናል። እነዚህ ሁኔታዎች የማስታረቅ ሚና ሊጫወቱ የሚችሉ ከሆነ ግጭት ውስጥ ያሉት አካላት ግጭቱን እንዳይባባስ መከላከል እና መቆጣጠር ይችላሉ። እነዚህ አስታራቂ ሁኔታዎች በማይኖሩበት ሁኔታ የግጭቶች የመባባስ ዕድላቸው በእጅጉ ይጨምራል። እንዲሁም ኃይል የተቀላቀለበት ነውጥ ይከተላል። አንዳንድ ጊዜም ግጭቱ ከቁጥጥር ውጭ ይሆናል። እነዚህን ሁኔታዎች ለይቶ ማወቅ ጋዜጠኞች ግጭቶች እየተባባሱ የሚሔዱ መሆኑን እና አለመሆኑን ለመገመት እንዲችሉ ያስችላቸዋል። በተጨማሪም ግጭቶች እንዲባባሱ መፍቀድ የሚያስከትለውን ውጤት የሚያመላክቱ ጥያቄዎችን እንዲያነሱ ይረዳቸዋል።
ግጭትን ከሚያስታርቁ እና የሚያባብሱ ጉዳዮች የሚላቸው የሚከተሉት ይገኙበታል።
- ታሪክ – ግጭት ውስጥ የገቡ አካላት ቀደም ሲል የነበሩትን ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ የመፍታት የጋራ ታሪክ ያላቸው ከሆነ አለመግባባቶችን ለመቀነስ እና እንዳይባባስም ለመከላከል ይጠቅማቸዋል። በመተማመን ላይ ተመሥርተው ሁኔታዎችን ለማስተካከል ይችላሉ። ብዙ ጊዜ ሰዎች ግጭት ቀስቃሽ ሁኔታዎች በሚገጥሟቸው ወቅት ካሳለፉት ልምድ ተነስተው የቆየ ጭፍን አስተሳሰብ ያንፀባርቃሉ። በዚህም ምክንያት ከፍ ወዳለ የቁጣ ደረጃ ሊያሸጋገር እና ነውጥ የመቀስቀሱን ዕድልን ሊያባብሰው ይችላል።
- የጋራ እሴቶች – ግጭት ውስጥ የገቡ አካላት አንዳቸው የሌላውን ሕጋዊነት እና ሕልውና የሚቀበሉ ከሆነ ሰላማዊ ውይይት ለማካሔድ አስተዋፅዖ ያደርጋል። እነዚህ ወገኖች አንዳቸው የሌላኛቸውን የንብረት፣ የዜግነት እና የፖለቲካ ውክልና መብቶች ለመቀበል ፈቃደኛ ካልሆኑ የድርድር ተስፋዎቻቸው ውስን ይሆናሉ፤ እናም ወደ ግጭት አዙሪት ሊመለሱ ይችላሉ።
- የአማራጮች መኖር – ግጭት ውስጥ የገቡ ወገኖች ለግጭቱ መፍትሔ የሚሆኑ አማራጭ እንዳላቸው ከተረዱ ሁኔታው እንዲባባስ አይፈቅዱም። ሆኖም ግን ጥቅማቸው የተነካ መስሎ ከተሰማቸው ግጭቶችን በፍጥነት እንዲባባሱ ሊያደርግ በሚችል መልኩ ከሙሉ ያነሰ አንቀበልም የሚል አቋም ይይዛሉ። ሌሎቹ ሰዎች አማራጮቻቸውን ማወቃቸው የቱ እንደሚሻላቸው ከግምት ውስጥ ሳያስገቡ ወደ ግጭት እንዳያመሩ ይጠቅማቸዋል።
- ተቀባይነት ያላችግጭትማረቂያመድረኮች-ግጭት ውስጥ ያሉወገኖች የሚጋሯቸው ግጭትን ለመፍታትየተቋቋሙ መድረኮች መኖራቸው ሁከት እንዳይነሳ ይረዳል።ሁሉም ወገኖች በመድረኮቹ ፍትሐዊነት እናውጤታማነት ላይ እምነት ሊኖራቸው ይገባል።ግጭት ውስጥ ያሉትወገኖችከነዚህ መድረኮች ውጪያለውአማራጭኃይል መጠቀም ብቻ እንደሆነ ሊሰማቸው ይችላል።
- የሕግ አመለካከት – ግጭት ውስጥ ያሉ ወገኖች ግቦቻቸው ሕጋዊ ናቸው ብለው ካመኑ፥ ትኩረት በመስጠት ግቦቻቸውን ለማሳካት አቅማቸውን የማደራጀት ዕድላቸው ይጨምራል። ሁለቱም ወገኖች ጥያቄያቸው ሕጋዊ ነው የሚል አቋም ካላቸው ደግሞ ወደ ከፍተኛ ሁኔታ የሚባባስ ግጭት እንደሚያስከትል ግልጽ ነው።
- ተግባቦት – ግጭት ውስጥ ያሉ ወገኖች መካከል የኮሙኒኬሽን መንገድ ካለ ግጭቶች የሚባባሱበት አጋጣሚ ጠባብ ይሆናል። በተቃራኒው በመካከላቸው ውጤታማ የመነጋገሪያ መንገድ ከሌለ አለመግባባት እና የግጭት አዙሪት ይጨምራል።
1.5 ግጭቶች በሚባባሱበት ወቅት ምን ይከሰታል
የበርካታ ጽንሰ ሐሳቦች አቅራቢዎችን ሥራ በመመርመር ግጭት በሚባባስበት ወቅት በተሳታፊ አካላት መሐል የሚከሰቱ ለውጦችን የሚያሳይ ሞዴል አዘጋቷል። ይህ ሞዴል ጋዜጠኞች ግጭት በሚፈጠርበት እና በተደጋጋሚ በሚከሰትበት ጊዜ ሊፈጠር የሚችለውን ነገር መተንበይ እንዲችሉ ይረዳቸዋል። ማንን እና ምን መጠየቅ እንዳለብንም እንረዳበታለን።
ለውጦቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
- ጉዳዮች እና ጥያቄዎች – በግጭቱ መጀመሪያ አካባቢ ግጭት ውስጥ የገቡት አካላት በአንፃራዊ ጥያቄዎቻቸው ውስን ሲሆኑ የሚያነሷቸውም ጉዳዮች በግልጽ የተቀመጡ ናቸው። ሆኖም ግጭቱ እያደገ ሲመጣ ግን እነዚህ ወገኖች ይበልጥ እያተኮሩበት ይመጡና ፍላጎቶቻቸውም ይጨምራሉ፤ የሚያነሷቸውም ጉዳዮች ውስብስብ እየሆኑ ይመጣሉ። ግጭቱ ምንን በተመለከተ እንደሆነ ለማወቅ ከባድ የሚሆንበት ሁኔታ ይከሰትና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ ተፅዕኖ ያመጣል።
- ሀብት – ግጭት በሚነሳበት ጊዜ ግጭት ወገኖች ግባቸውን ለማሳካት ትንሽ ወጪ ብቻ ነው የሚመድቡት። ግጭቱ ቀጥሎ በሚባባስብት ጊዜ ግን የሚጠቀሙት ሀብትም ይጨምራል። ግጭት ውስጥ የገቡ ወገኖች በከፍተኛ ሁኔታ ገንዘብ መድበው የሚንቀሳቀሱ ከሆነ፥ በተጨባጭ ጥቅሞቻቸውን ሳያስጠብቁ ከግጭቱ ራሳቸውን ለማግለል ወይም ለመደራደር ከባድ ይሆንባቸዋል።
- ተሳታፊዎች – አብዛኛው ግጭት እያደገ በሔደ ቁጥር በግጭቱ የሚሳተፉ አካላት ቁጥር ይጨምራል። በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚፈጠር ግጭት፣ ግጭቱን ከእሴቶች እና ከማንነትን አንፃር የሚመለከቱ ከተለየ ጎሳና ሃይማኖት የሆኑ ሰዎች መሐከል ሊዛመት ይችላል።
- ግንዛቤዎች – ግጭቱ እየከፋ ሲሔድ እንዲሁም የተሳሳቱ አመለካከቶች እና ጥላቻዎች ሥር እየሰደዱ ሲመጡ፥ ቡድኖች አንዳቸው ለሌላቸው ያላቸው አመለካከት ሙሉ በሙሉ ይቀየራል። ቡድኖች አንዳቸው ሌላኛቸውን የማሰይጠን ሥራ በመሥራት የራሳቸውን ስጋት በተቀናቃኝዎቻቸው ላይ መለጠፍ ይጀምራሉ። የዚህ ውጤት ቡድኖች ግጭቱን በራሳቸው ለመፍታት ምንም ኃላፊነት የማይወስዱ እንዲሆኑ ያደርጋል።
- ተግባቦት – በቡድኖች መካከል የሚኖር ንግግር በአንፃራዊነት ከግልጽነትና ትክክለኝነት ወደ ጥላቻና እርስ በርስ መወቃቀስ የሚለወጥበት ሁኔታ አለ። ግጭት ውስጥ በገቡ ወገኖች መካከል የሚኖሩ ንግግሮች አንደኛው ስለሌላኛው በሚኖረው አመለካከት ሳቢያ ሊዛባ ይችላል። የተዛባው አስተሳሰብ ግጭትን ለመፍታት የሚደረጉ ኮሚዩኒኬሽኖች ጥቅም ለማግኘት ስልታዊ ማታለያ መንገድ እንደሆኑ በመቁጠር ተቀባይነት እንዳያገኙ ማድረግ ድረስ ይደርሳል።
- የውስጥ ኃይል ተለዋዋጭነት – ቆራጥነት የተሞላበት አመራር ደኅንነታችንን ያረጋግጥልናል ብለው ስለሚያምኑ፣ ቀውስ በሚያጋጥምበት ወቅት ቡድኖች ኃያልነት የሚሰማቸው፣ ዲሞክራት ያልሆኑ ሰዎችን ወደ ኃላፊነት ቦታ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ። ይህ የሚከሰተው ታጣቂ መሪዎች ሰላማዊ በሆኑት ላይ የበላይ በሚሆኑበት ወቅት ነው። የታጣቂው ቡድን በግጭቱ የበላይነትን መቆጣጠር ሁሉንም አካል ሊያስማማ የሚችል ሐሳብ ቢቀርብ ግጭት ውስጥ ያሉ ወገኖች የመቀበል ፍላጎታቸው ይቀንሳል።
እነዚህ ለውጦች በቡድኖቹ መሐከል እና በቡድኖች ውስጥ ሲከሰቱ፥ ቡድኖቹ ግባቸውን ለመምታት ይከተሉት የነበሩት ዘዴ ላይ ተጨባጭ የሆነ ለውጥ ያካሔዳሉ። እነሱምከዚህ ሞዴል እንደምንረዳው፣ ግጭት መቀሰቀስ በሚጀምርበት ወቅት ቡድኖች አንደኛቸው ለሌላኛቸው የሚኖራቸው ስሜት ገለልተኛ ወይንም አዎንታዊ ይሆናል። በዚያ መልኩ በጋራ ሆነው ችግር የመፍታት ሒደት ውስጥ መሳተፍ እንደሚችሉ ይሰማቸዋል። ይሄ ደረጃ በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ አካላት ገንቢ በሆነ መንገድ ችግሮችን መፍታት የሚችሉበት ነው። ሆኖም ግጭቱ እየተባባሰ ሲሔድ የተለያዩ ስሜት ቀስቃሽ ሁኔታዎች ስለሚከሰቱ በወገኖቹ መካከል ያለው አዎንታዊ ግንኙነት ያሽቆልቁላል። እንዲሁም አንዱ ወገን ሌላውን ድርድር ውስጥ እንዲገባ ወይም እጅ እንዲሰጥ ለማሳመን ይሞክራሉ። በዚህ ደረጃ ግጭት ውስጥ የገቡ ወገኖች በቀጥታ ከግጭቱ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ተቀናቃኞቻቸውን እና ሌሎች ቡድኖችን የጥያቄያቸውን ሕጋዊነት ለማሳመን መሞከር የተለመደ ነው።
ግጭት ውስጥ የገቡ ወገኖች ጥያቄያዎቻቸውን ለተቀናቃኝዎቻቸው ማሳመን ካልቻሉ ማስፈራሪያዎችን መጠቀም ይጀምራሉ። እነዚህ ማስፈራሪያዎች ኃይል መጠቀምን እና ጥቅማጥቅሞችን መቀማት ይጨምራሉ። እንዲሁም የማስፈራሪያዎቹን አስከፊነት ለተቀናቃኝ ወገን ለማሳየት ሀብት ማደራጀት መጀመርንም ያካትታል። በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ሲታይ ጉዳት የማድረስ አቅም እንዳላቸው ለማሳየት ለሌላ አገር ድንበር ቅርብ የሆኑ ቦታዎች ላይ የሚደረጉ የጦርነት ልምምዶችን ወይም የሚሳየል ሙከራዎችን ሊያካትት ይችላል። በአንድ አካባቢ ደግሞ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረግን እና ማዕቀቦችን ሊያካትት ይችላል፤ ይህ ሁሉ አንድ ፓርቲ ዓላማውን የሚደግፉ ብዙ ሰዎችን የማሰባሰብ ኃይል እንዳለው ለማሳየት ነው።
ተቀናቃኝዎች ለማስፈራሪያዎቹ ሰግተው ምላሽ ካልሰጡ፥ ግጭት ውስጥ የገቡት ወገኖች ነውጥን ጨምሮ ኃይልን እንደ አማራጭ ይወስዱታል። በዚህ ደረጃ ግጭት ውስጥ የገቡ ወገኖች ኃይላቸውን ለማደራጀት ያላቸውን አቅም ሁሉ ይጠቀማሉ። በተመሳሳይ ወቅት የተቀናቃኞቻቸውን ግብ የመፈለግ አቅም ለማዳከም ጥረት ያደርጋሉ።
ማስታወሻ:
በቡድኖች መካከል ያለው ግንኙነት በሻከረበት ሁኔታ፣ እምቅ ግጭቶች ወደ አፍላ ግጭትነት በሚቀየሩበት ጊዜ ቡድኖቹ በሁሉም ደረጃዎች ውስጥ ላያልፉ የሚችሉበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል። በመከባበር እና በመተማመን ላይ የተመሠረተ ግንኙነት አለመኖር ማለት ወገኖች በግጭት መባባስ ሞዴሉ የከፍተኛውን ደረጃ ባሕሪ እንዲይዙ ያደርጋል ማለት ነው ።
ግጭት ሲባባስ የአንድ ቡድን ዘዴ እንደሚቀየረው ሁሉ ግቦቹም ይቀየራሉ። በግጭት መጀመሪያ ወቅቶች ቡድኖች ዋና ጉዳያቸው ለራሳቸው ያወጧቸው ግቦችን ማሳካት ነው። ለራሳቸው ፍላጎት ትኩረት ይሰጣሉ፣ ስለ ሌሎች አካላት ጉዳይ ግን አያሳስባቸውም። ግጭቶች በሚባባሱበት ጊዜ ግን ሌሎች አካላት ዓላማቸውን ለማሳካት የሚያደርጉትን ጥረት እያደናቀፉ እንደሆነ እየተረዱ ይመጣሉ። ተቀናቃኞቻቸውን ለመጣል ተስፋ በማድረግ ብዙ ሀብታቸውን ግጭቱ ላይ ያውላሉ። ሆኖም ግጭት ውስጥ የገቡት አካላት ግጭቱ ላይ ብዙ ሀብት ባፈሰሱ ቁጥር ማሸነፋቸውም የበለጠ አስፈላጊ እየሆነ ይመጣል። ተቀናቃኝዎቻቸው ሆን ብለው የእነሱን ዓላማ እያደናቀፉ እንደሆነ በተሰማቸው መጠን ሌላውን አካል ለማሸነፍ የበለጠ ይፈልጋሉ። ግባቸውን ማሳካት ሳይሆን ማሸነፍ ግጭቱን የሚገፉበት ምክንያት ይሆናል።1 ግጭቱ ውስጥ የገቡ አካላት አንዳቸው ሌላኛቸው ላይ ጉዳት ማድረስ ደረጃ ከዘለቁ፣ ማሸነፍ በቂ እንደማይሆን የሚሰማቸውና እና ተቀናቃኝዎቻቸው ሊቀጡ ይገባል ብለው የሚያምኑበት ደረጃ ላይ ሊደርሱ ይችላሉ። በዚህ ደረጃ ቡድኖች ሲነሱ የያዙትን ግብ ችላ ይሉና አቅማቸውን አንዱ ሌላኛውን ለመጉዳት እና በቀል ማሰብ ላይ ትኩረት ማድረግ ይጀምራሉ። በብዙ ሁኔታዎች እንደ አሽከርካሪ ላይ ሆኖ ጥይት በመተኮስ እና መኪና ማፈንዳት የመሳሰሉ ስቃይ የተሞላባቸው መግደያ ዘዴዎችን እንዲሁም አደገኛ ነውጥ መጠቀምን ሊያካትት ይችላል።