ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት አስፈላጊነት
- ግለሰቦች ምሉዕነት እንዲሰማቸው ያደርጋል (personal fulfillment)
- እውነቱን ለመረዳት እንዲሁም ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ ተሳትፎ ለማድረግ
- የግለሰቦችን ውሳኔ ሰጪነት አቅም ያጠናክራል7ቱ የተዛቡ መረጃ ዓይነቶች
1ኛ – ስላቅ ወይም ቀልድ (Satire or Parody) – እነዚህኞቹ አንባቢውን ለመጉዳት ወይም ለማሳሳት የተፈጠሩ ሳይሆን ለማስገረም፣ ለማዝናናት ወይም ባለታሪኩ ላይ ለማላገጥ የተዘጋጁ መረጃዎች ናቸው፤ ነገር ግን በተደራሲዎቹ እንደ እውነት ሊቆጠሩ ይችላሉ።
2ኛ – አሳሳች ይዘት (misleading content) – እነዚህኞቹ መረጃዎቹ ስህተት ባይሆኑም የቀረቡበት መንገድ ግን ተደራሲያኑን በማሳሳት ሌላ ነገር እንዲገምቱ ወይም እንዲያምኑ የሚያደርግ ነው።
3ኛ – የተፈበረከ ይዘት (fabricated content) – ጉዳት ለማስከተል በማሰብ ሙሉ ለሙሉ የተፈጠረ የሐሰት መረጃ።
4ኛ – ለምድ ለባሽ ይዘት (Imposter content) – መረጃው ከታማኝ ምንጭ ወይም ቢሮ የተገኘ ለማስመሰል የተደረገ ነገር ግን የተፈበረከ የሐሰት መረጃ።
5ኛ – የውሸት ግንኙነት (False connection) – ሁለት የማይገናኙ ነገሮችን (ፎቶ እና ታሪኩ፣ ርዕሱና ዝርዝሩ…) እንደሚገናኙ አስመስሎ ማቅረብ።
6ኛ – የውሸት ዐውድ (False context) – እውነተኛ ታሪኮችን እና ምስሎችን እየተጠቀሙ ነገር ግን ከአገባቡ ውጪ በመጥቀስ መረጃ ማዛባት።
7ኛ – አላግባብ የተተረጎመ ይዘት (manipulated content) – መረጃው ብዙ ተመልካች እንዲያገኝ ሲባል ብቻ አዛብቶ ማቅረብ።
ዐሥርቱ የሐሰተኛ መረጃዎችን መለያ ጥያቄዎች
- የዜና አውታሩ የሚታወቅ እና ተዓማኒ ነው?
- የዜና ጸሐፊው የሚታወቁ እና ተዓማኒ ናቸው?
- ዜናው ትኩስ ነው ወይስ እንደአዲስ የተከሸነ?
- የዜናው ምንጭ ተብለው የተጠቀሱት ይታመናሉ?
- የዜናው ይዘት አስተያየት ወይስ ጥሬ ሐቅ?
- ዜናው በሌላ ምንጭ የተረጋጠ/የሚረጋገጥ ነው?
- ከዜናው ጋር የቀረበው ፎቶ አዲስና እውነተኛ ነው?
- የዜናው ርዕስ እና ዝርዝሩ የሚዛመዱ ናቸው?
- ዜናው በወቅታዊ ክስተት ላይ የተጻፈ ስላቅ ይሆን?
- በጉዳዩ ታማኝ ባለሙያዎች ስለዜናው ምን ይላሉ?ሐሰተኛ መረጃ መለያዎች
የምሥል ማሰሻዎች (Reverse Image Search) – የተቀየሩ ምስሎች/ፎቶዎች፣ የቆዩ ነገር ግን እንደአዲስ አገልግሎት ላይ የዋሉ ምሥሎች፣ ወዘተ. መለያዎች
- images.google.com
- tineye.com
- RevEye (an add on)
- http://regex.info/exif.html (image meta data)
ቦታ ማወቂያዎች
- Google Earth Pro: google.com/earth
- Google Maps: maps.google.com
- Google Street View: google.com/streetview
ሐሰተኛ መረጃ መለያዎች (የቀጠለ)
- የዩቱዩብ መረጃ ተመልካች (YouTube Data Viewer) ተንቀሳቃሽ ምሥሉ መቼ እና በማን እንደተለጠፈ ያሳያል
- citizenevidence.amnestyusa.org
- invid-project.eu
የመረጃ መዛባትን እንዴት እንከላከል?
- ኀላፊነት የሚሰማው የበይነመረብ ተጠቃሚ በመሆን
- ጥራት ያለውን ዜና ከሚታመን ምንጭ በማግኘት
- ሐሰተኛ መረጃ ሲገጥም በማጋለጥ ወይም ሪፖርት በማድረግ
እነዚህ መብቶች ገደብ ሊጣልባቸው የሚችለው የሐሳብና መረጃ የማግኘት ነጻነት በአስተሳሰባዊ ይዘቱና ሊያስከትል በሚችለው አስተሳሰባዊ ውጤት ሊገታ አይገባውም በሚል መርሕ ላይ ተመሥርተው በሚወጡ ሕጎች ብቻ ይሆናል።
- የዜና አውታሩ የሚታወቅ እና ተዓማኒ ነው?
- ሦስቱ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት መሠረቶች
- የፈለጉትን አመለካከት ያለማንም ጣልቃ ገብነት የመያዝ መብት
- መረጃ የመፈለግ እና የማግኘት መብት
- ያለ አመለካከት ገደብ ሐሳብን በተቻለው ሚዲያ ሁሉ የማሰራጨት መብት ናቸው።
ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት
አንቀጽ 29/2
“ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሐሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው። ይህ ነጻነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ወሰን ሳይደረግበት፣ በቃልም ሆነ በጽሑፍ ወይም በኅትመት፣ በሥነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው መረጃና ሐሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበል እና የማሰራጨት ነጻነቶችን ያካትታል።”
ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት እና ብዝኀነት
በአፍሪካ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት መርሖች ድንጋጌ (Declaration of Principles of Freedom of Expression In Africa) መርሕ 3 የሚከተሉትን የግድ አስፈላጊ መመሪያዎች ለመንግሥታት ያስቀምጣል
- የተለያዩ ሐሳቦችን የሚያንፀባርቁ መረጃዎች ለሕዝቡ እንዲደርሱ
- ብዝኀነትን የሚያገናዝቡ ሚዲያዎች እና የመረጃ መለዋወጫ አማራጮች እንዲያብቡ (እነዚህም የሚገለሉ ቡድኖችን ማለትም ሴቶችን፣ ሕፃናትን፣ ስደተኞችን፣ የቋንቋ እና የባሕል ቡድኖችን ይጨምራል)
- አገር በቀል ቋንቋዎችን መጠበቅ እና ማበረታታት
- የአካባቢ ቋንቋዎችን በመንግሥት የሥራ ቋንቋነት መጠቀም
ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት እና ብዝኀነት
የዩኔስኮ ባሕላዊ ብዝኀ መገለጫዎችን የመጠበቅና የማበረታታት ሥምምነት (UNESCO Convention on the Protection and Promotion of Cultural Diversity Expression) “ባሕላዊ ብዝኀነት” ማለት “የሰብኣዊነት መገለጫ ነው” ይላል። ስለዚህ መንግሥታት የመጠበቅ እና የማበረታታት ግዴታ አለባቸው።
ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ገደቦች
ICCPR 19/3 (ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ሊገደብ የሚችለው)
- የሌሎችን መብቶች እና መልካም ሥም ለመጠበቅ ሲባል
- የአገር ደኅንነትን ለመጠበቅ፣ ሕዝባዊ ስርዓትን (public order) ለማስከበር፣ የብዙኀኑን ጤና እና ሞራል
ለመጠበቅ ሲባል
9 የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት ስለ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ገደቦች
አንቀጽ 29/6፡
- የወጣቶችን ደኅንነት፣ የሰውን ክብርና መልካም ሥም፣ ለመጠበቅ ሲባል ሕጋዊ ገደቦች በነዚህ መብቶች ላይ ሊደነገጉ ይችላሉ።
- የጦርነት ቅስቀሳዎችም እንዲሁ ሰብዊ ክብርን የሚነኩ የአደባባይ መገለጫዎች በሕግ የሚከለከሉ ይሆናሉ።
10 ሦስት እርከን ሙከራ (Three part test)
ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ለመገደብ ሦስቱ ሁኔታዎች መኖር አለባቸው፣
- በሕግ በተደነገገ አግባብ መሆን አለበት
- ቅቡልነት ያለው ዓላማ (legitimate goal)ሊኖረው ይገባል
- ቅቡልነት ላለው ዓላማ የግድ አስፈላጊ መሆን አለበት
11 ዓለም ዐቀፍ ክልከላዎች
International Convention on the Elimination of All Forms of Racial Discrimination (ሁሉንም ዓይነት የዘር መድልዖዎች ለማስወገድ የዓለም ዐቀፉ ሥምምነት) አንቀጽ 4/a ላይ በሕግ መቀጣት ያለባቸው ስድስት ድርጊቶችን ይዘረዝራል፣
- የዘር የበላይነትን የሚሰብኩ ሐሳቦችን ማሰራጨት
- የዘር ጥላቻ የሚሰብኩ ሐሳቦችን ማሰራጨት
- የዘር መድልዖን ማነሳሳት/መቀስቀስ
- በዘር የነሳሳ የጥቃት ተግባር
- በዘር ለተነሳሳ የጥቃት ተግባር ማነሳሳት
- ለዘረኝነት ድርጊት የገንዘብን ጨምሮ ማንኛውንም ዓይነት ድጋፍ መስጠት
12 የተከለከሉ ንግግሮች
- ICCPR አንቀጽ 20 የሚከተሉት ንግግሮች በሕግ መከልከል አለባቸው ይላል
- የጦርነት ፕሮፓጋንዳ
- የብሔር፣ የዘር እና የሃይማኖት መድልዖን የሚሰብኩ፣ ለጥቃት እና ለነውጥ የሚያነሳሱ መልዕክቶች
13 የጥላቻ ንግግርን ማወቂያ ስድስት መንገዶች (UNOHCHR)
1) ዐውድ (context)
መልዕክቱ የተነገረበት አገባብ (ዐውድ) ማግለልን ወይም ጥቃትን ለማነሳሳት ነው ወይስ…
2) ተናጋሪው
ተናጋሪው/ዋ በማኅበረሰቡ ውስጥ ያለው ቦታ እና ሲናገር/ስትናገር የነበሩት አድማጮች
3) ዓላማ (intent)
ንግግሩ የተነገረው ሆን ተብሎ ጥላቻውን ለማነሳሳት ነው ወይስ ባለማወቅ ወይም በቸልተኝነት…?
4) ይዘቱ ወይም ቅርፁ (Content or form)
የንግግሩ ይዘት ቀስቃሽ እና ቀጥተኛ ነው ወይስ በተዘዋዋሪ…?
5) የንግግሩ ተዳራሽነት
ንግግሩ ለማን ነው የተነገረው? ተዳራሽነቱ ምን ያህል ነው? የት ነው የተነገረው?
6) የጎጂነት ዕድሉ
ንግግሩ ጉዳት ሊያደርስ የሚችልበት ዕድል አለ ወይስ የለም…?
የጥላቻ ንግግር መለያ ቀመር