የተለያዩ ድምፆች – በሁሉም የዜና ሽፋኖች እና ሌሎች ፕሮግራሞች ላይ የተለያዩ ድምፆች መኖራቸውን ማረጋገጥ፡፡ ሥርዓተ ፆታን፣ የተለያዩ ጎሳዎችን እና ቋንቋዎችን እነሱን የሚመለከት ፕሮግራም ሲኖር ወይም ለአንዳንድ ፖለቲካዊ ጥቅሞች ወይም ጎሳዊ ጉዳዮች መዳሰስ አለባቸው ሲባል ብቻ መጠቀስ የለባቸውም፡፡ ነገር ግን ቁልፍ ብሔራዊ ጉዳዮችን (ሥርዓተ ፆታንም ሆነ ጎሳን አካተቱም አላካተቱም )
የሚዳስሱ በሉም ዜናዎች እና ፕሮግራሞች ላይ መዳሰስ ይኖርባቸዋል፡፡
ምስጢራዊነትን ማስወገድ – አንዳንድ ቡድኖችን ማካተት ስላለብን ብቻ አንጥቀሳቸው፡፡ መሰረታዊ የመወከል አቅማቸውን ያዳክመዋልና፡፡ ስለሆነም ተወካይ ቡድኖች እድሉ ስለራሳቸው ለመናገር ወይም ራሳቸውን ለመወከል ጊዜአቸው ሲደርስ ውክልናው ዓላማ ሊኖረው እና ትክክለኛ ሊሆን ይገባ፡፡
ቆም ብሎ ማሰብ – ሪፖርቱ/ፕሮግራሙ ማን ለማን እና ስለማ እየተናገረ ነው በሚል ተዛብቶ ይሆን? ለምን? የባለጉዳዩ ድምፅስ የታለ?
መጠየቅ እና መጋፈጥ – መገናኛ ብዙሃን የላይኛው መደብ ባስቀመጠው ደረጃ ውስጥ መጠቅለል የለበትም ወይም ደግሞ ሰዎ መስማት የሚፈልጉትን ብቻ መቀመም፤ እንዲያውም የላይኛው መደብ ን መደብ ተጋፍጦ እኩልነትን (የሥርዓተ ጾታ ፣ ጎሳ ፣ ቋንቋ እና ወዘተ. ) ፣ ዴሞክራሲን እና ኃሳብን በነጻነት የመግለፅን መብት እንዲያስተዋውቁ መግፋት አለበት፡፡
ወኪልነት ቁልፍ ነው – የመገናኛ ብዙሃን ሰዎች ሁሉም አይነት ማንነቶች በራሳቸው ምሉዕ መሆናቸውን እና የራሳቸው ፍላጎቶች ፣ ጥያቄዎች እና ድምፅ ወኪል ናቸው፡፡ ይህ ወኪልነታቸው አንሶ ሲታይባቸው ነው ድምፆቻቸው የሚታፈኑት እና ወደ አደገኛው “ሌሎች” አናሳ ምድብ ውስጥ የሚገቡት፡፡
የአንድ ጎን ብቻ ታሪኮችን አስወግድ – አንድ የዜና ዘገባ ወይም ማንኛውም ከጾታ ወይም ከተለያዩ ጎሳዎች ጋር የተዛመዱ ፕሮግራሞች በሚዘጋጁበት ጊዜ ሁሉ ታሪኮቹ በአጠቃላይ ተመጣጣኝ እና ክብደት እንደነበራቸው ማረጋገጥ አለበት፡፡ የመገናኛ ብዙሃ ሚና ሁሉንም ዜጎች ፣ አንዱ አንዱን እንደሚበልጥ ለማሳየት ሳይጣደፉ ያለማዳላት መወከል ነው፡፡