በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ከተባለው ወረዳ በመነጠል << የራሳችን >> ያሉትን ልዩ ወረዳ እንመሰርታለን በሚሉና ጥያቄውን በሚቃወሙ ቡድኖች መካከል በተነሳ ግጭት ዳግም የሰው ህይወት አያለፈ ፣ ንብረትም እየወደመ ይገኛል።

እስከአሁን ሰባት ሰዎች ተገድለዋል፤ ቁጥራቸው ያልታወቁ መኖሪያ ቤቶች በእሳት ጋይተዋል

በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ከተባለው ወረዳ በመነጠል << የራሳችን >> ያሉትን ልዩ ወረዳ እንመሰርታለን በሚሉና ጥያቄውን በሚቃወሙ ቡድኖች መካከል በተነሳ ግጭት ዳግም የሰው ህይወት አያለፈ ፣ ንብረትም እየወደመ ይገኛል።

የአሁኑ ግጭት በዞን ሰገን ዙሪያ በተባለ ሌላ ወረዳ ውስጥ የተቀሰቀሰው ቀደምሲል በመሬት ይገባኛል ሰበብ ለወራት ሲካሄድ የነበረው ግጭት በብሄሮቹ ሽማግሌዎች ጥረት ከረገበ ከሁለት ሳምንት በኋለ ነው።

በዞኑ የሰገን ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከተማ ገለቦ ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በተቀሰቀሰውና አሁን ድረስ በቀጠለው በዚሁ ግጭት እስከአሁን ሰባት ሰዎች መገደላቸውን ፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ መኖሪያ ቤቶች በአሳት መጋየታቸውን ለዶቼ ቬለ (DW) አረጋግጠዋል። የአካባቢው ነዋሪዎችና የአይን እማኖች በበኩላቸው ለዶቼ ቬለ (DW) እንዳሉት በግጭቱ የተደራጁ ቡድኖች ወደ መንደሮች በመዝለቅ ግድያ ፈጽመዋል ፣ መኖሪያ ቤቶችን አውድመዋል ።

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *