የአለም የጤና ድርጅት ኮቪድ-19 (ኖቬል ኮሮና ቫይረስ) አለም አቀፍ ወረርሽኝ መሆኑን መጋቢት 2፣ 2012 ዓ.ም አስታውቋል፡፡ እንደ ድርጅቱ መግለጫ፣ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥርም በአለም አቀፍ ደረጃ እየጨመረ መጥቷል፡፡፡፡
ህዝብ ስለቫይረሱ ሊኖረው የሚገባውን ግንዛቤ በማስጨበጥና መንግስታት ቫይረሱን ለመዋጋት የሚደረጉትን ጥረቶች በማሳወቅ ረገድ፣ በመላው ዓለም የሚገኙ ጋዜጠኞች ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ ነው፡፡በሲ.ፒ. ጄ እነደተዘገበው፣ ጋዜጠኞች ይህንን የሚያደርጉት፣ በብዙ ሀገራት ያሉ መንግስታት፣ በነፃነት የመዘገብንና መረጃ የማግኘትን ሂደት በሚያሰናክሉበት ሁኔታ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር፣ የሚዲያው አካላት፣ ከፍተኛ ጫናና ችግር እየገጠማቸው ነው፡፡ በዚህም የተነሳ፣ ከጋዜጠኞች ጋር በሲ.ፒ. ጄ በተደረጉ ቃለ ምልልሶች እንደታየው፣ የመገናኛ ብዙኃን አባላት፣ ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀሱ፣ ቃለ መጠይቅ ሲያደርጉና ስራቸውን በሚሰሩበት ቦታ ራሳቸውን በከፍተኛ ደረጃ ለቫይረሱ ተጋላጭ እየሆኑ ነው::
ሁኔታው እየተባባሰ በሄደ መጠንና አዳዲስ መረጃዎች በመጡ ቁጥር፣ ወቅታዊ የጤና ምክሮችና ስለቫይረሱ ስርጭት አዳዲስ ዜናዎች በሚመለከታቸው ባለስልጣኖች ይሰጣሉ፡፡ በየወቅቱ ስለሚሰጡ ምክሮችና መደረግ ስለሌባቸው ነገሮች ወቅታዊ ግንዛቤ ለማግኘት፣ የቫይረሱን ስርጭት የሚዘግቡ ጋዜጠኞች በአለም የጤና ድርጅትና በየሃገሩ የጤና ድርጅቶች የሚሰጡ መረጃዎችን ሳያሳልሱ መከታተል ይገባቸዋል፡፡
የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ የመረጃ ማዕከል፣ ስለ አሁናዊ የቫይረሱ ስርጭት ለማወቅ አስተማማኝ ምንጭ ነው፡፡
በመስክ ስራ ላይ እራስን ከአደጋ ጠብቆ ስለመቆየት
በአሁን ጊዜ አለም አቀፋዊ ጉዞዎች በስፋት በመከልከላቸው፣ ቢያንስ ለተወሰነ ጊዜ አብዛኛዎቹ የመገናኛ ብዙኃን ስራ የሚያከናወኑት በሃገር ውስጥ ነው፡፡ ያለበቂ ወይም ያለምንም ማሳሰቢያ፣ የዘገባ ስራዎች ሊለወጡ ወይም ሙሉ በሙሉ ሊሰረዙ ይችላሉ፡፡ ይህም የሚሆነው በመላው አለም በፍጥነት በሚከሰቱና በሚቀያየሩ ሁኔታዎች ነው፡፡
ስለዚህ፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመዘገብ የሚሹ ባለሙያዎች የሚከተሉትን የጥንቃቄ መረጃዎች ልብ ሊሉ ይገባል፤ ከስራ ሥምሪት በፊት
- ለቫይረሱ ያለንን ተጋላጭነት ለመቀነስ፣ በተቻለው አጋጣሚ ሁሉ ቃለ መጠይቆችን በአካል ከማድረግ ይልቅ በኢንተርኔት ወይንም በስልክ ማካሄድ ይገባል፡፡
- የአሜሪካው በሽታን የመቆጣጠሪያና የመከላከያ ማዕከል(ሲ.ዲ.ሲ) እንደሚለው፣ በዕደሜ የገፉ ሰዎችና ቀደም ሲል የጤና ዕክል ያለባቸው ግለስቦች ለቫይረሱ በከፍተኛ ደረጃ የተጋለጡ ወገኖች ናቸው፡፡ ከእንዲህ ዓይነት ሰዎች ጋር ቀጥተኛ ንክኪ የነበረን የመገናኛ ብዙኃን ሰራተኞች፣ ከተቀረው የሕብረተሰብ ክፍል ጋር በቀጥታ ሊያገናኘን የሚችል የዘገባ ሥራን ልናስወግድ ይገባል፡፡ ለነፍሰ ጡር ሰራተኞችም ተመሳሳይ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል፡፡
- የመገናኛ ብዙኃን አመራሮች የኮቪድ-19 ወረርሽኝን የሚዘግቡ ጋዜጠኞችን ሲመድቡ የዘረኝነት ጥቃት እንዳይካሄድባቸው ልብ ሊሉ ይገባል፡፡ ይህን መሰል ጥቃት በዝፊድ (BuzzFeed) ይፋ አድርጓል፡፡ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲም ኢትዮጵያ ውስጥ በሚኖሩ የውጭ ዜጎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች እንዳሉ የሚያሳይ ማስጠንቀቂያ መጋቢት ወር ላይ አውጥቷል ፡፡ ቫይረሱ ስርጭት እየጨመረ በሄደ ቁጥር፣ እነዚህ ሁነቶች በተደጋጋሚ ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡
- ጋዜጠኞች በመስክ ስራ ላይ እያሉ በቫይረሱ ሊለከፉ ስለሚችሉ፣ ስለሁኔታው ከአለቆቻቸው ጋር በመመካከር ሊያገኙት ስለሚገባ እርዳታና እገዛ አስቀድመው ማቀድ አለባቸው፡፡ የሚያወጡት እቅድ ደግሞ፣ እራስን አግልሎ ማቆየትንና ለረጅም ጊዜ በማግለያ ቦታ መቆየትን ሊያካትት ይገባል፡፡
ስነልቦናዊ ደህንነት
- ከፍተኛ ልምድ ያለቸው ጋዜጠኞች ሳይቀሩ፣ ስለ ኮቬድ 19 ሲዘግቡ፣ በስነልቦና ረገድ ሊቸገሩ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ፣ የስራ ሃላፊዎች፣ ጋዘጠኞቻቸው እንዴት እየዘገቡ እነደሆነና እስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም መመሪያና ድጋፍ ሊሰጧቸው ይገባል፡፡
- እኛ ጋ ዜጠኞች የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመዘገብ ስንቀሳቀስ፣ የቤተሰቦቻችን መጨነቅና መስጋት የሚጠበቅ ነው፡፡ በመሆኑም፣ እነዚህን ስጋቶችና ጭንቀቶች ከቤተሰቦቻችን አባላት ጋር በግልጽ ልንነጋገር ይገባል፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም፣ ይህንን
ከቤተሰብ ጋር የሚደረግ ውይይት የድርጅታችን የህክምና አማካሪዎች ባሉበት ብናደርገው መልካም ነው፡፡
- ጋዜጠኞች ለሲ.ፒ.ጄ እነዳስታወቁት፣ ቤተ ዘመድና ወዳጆች ሳየቀሩ ስለ ኮቪድ 19 ስለሚሰሩ ዘገባዎች ብዙ ጊዜ አሉታዊ አስተያየት በመስጠት አደገኝነቱን እስከመጠራጠር ደርሰዋል፡፡ ይህ ደግሞ ስሜትን የሚጎዳ ሊሆን ይችላል፡፡
- በኮቪድ-19 ከተጠቃ ቦታ ወይም አካባቢ፣ በተለይም ከህክምና ተቋም ወይም ከማግለያ ቦታዎች ሆነን የዘገባ ስራ ስንሰራ ሊፈጠር የሚችለውን የስነልቦና ጫና ልብ እንበል። የኮቪድ-19 ስርጭት ዘገባ የሚሰራው ቫይረሱ በስፋት ከተንሰራፋበት፡፡ የዲ.ኤ.አር.ቲ ማዕከል ስለ ጋዜጠኝነት እና ጭንቀት (the DART Center for Journalism and Trauma) የተባለው የመረጃ ምንጭ፣ አስጨናቂ ሁኔታዎችን ለምንዘግብ ጋዜጠኞች ጠቃሚ ማዕከል ነወ፡፡የአእምሮ ጤናን ጨምሮ፣ ለጥንቃቄ የሚበጁ ምንጮችን ለማግኘት፣ የሲ.ፒ.ጄን የአደጋ ጊዜ ገጽ እንጎብኝ/እንምልከት
በቫይረሱ መለከፍን እና ቫይረሱን ወደሌሎች ማስተላለፍን መከላከል
በአሁኑ ጊዜ ብዙ ሀገሮች ማህበራዊ/ አካላዊ ርቀትን ተግባራዊ እያደረጉነው፡፡ባደጋ ጊዜ አገልግሎት ወደሚሰጥባቸው ወይም ከዚህ በታች ወደ ተገለጹ ቦታዎች ስለ ቫይረሱ ለመዘገብ ስናስብ፣ በቦታዎቹ ስለሚደረጉ የንጽህና አጠባበቆች በቅድሚያ በቂ ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል፡፡ ስለሁኔታው የምንጠራጠር ከሆነ፣ ወደ እነዚህ ቦታዎች መሄድ የለብንም፤
- ወደ ማንኛውም የጤና አጠባበቅ ተቋም፣
- አረጋውያንን የመንከባከቢያ ማዕከል፣
- የታመመ፣ የጤና እክል ያለበት ወይም ነፍሰ ጡር ቤት፣
- የታመሙና በበሽታው የተጠረጠሩ የሚቆዩባቸው፣ ማግለያ ቦታዎች ወይም አንቅሰቃሴ የታገደባቸው ከልሎች፣
- ያስከሬን ማቋያ፣ ያስከሬን መገነዣ ወይም ሰርዓት ቀብር የሚፈጸምባቸው ቦታዎች፣
- ህዝብ በብዛት የሚኖርባቸው የከተማ ስፍራዎች (ማለትም የተፋፈጉና ንጽህና የጎደላቸው)፣
- የስደተኞች ማቆያ ጣቢያ፡፡
- ኮቪድ 19 የተከሰተበት እሰር ቤት ወይም ፖሊስ ጣቢያ።
ራሳችንን ከቫይረሱ ለመከላከል የሚያስችሉን መደበኛ ምክረ ሃሳቦች ደግሞ የሚከተሉትን ያካትታሉ፤
- ከማንኛውም ሰው ቢያንስ በ2 ሜትር እራሳችንን ማራቅ፤ የመተንፈሻ አካላት ህመም ምልክቶች(ማስነጠስ ወይም ማሳል) የታዩባቸው ሰዎች ዘንድ ስንሆን ደግሞ የበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ፡፡እጅ መጨባበጥን፣ መተቃቀፍንና መሳሳምን እናስወግድ፡፡
- ቃለ መጠይቅ በምናደርግበት ጊዜ፣ በተጠያቂዎቹ ፊት ለፊት ከመሆን ይልቅ፣ በሰያፍ በመቆም ቢያንስ ሁለት ሜትር እራሳችንን በማራቅ ስራችንን እንስራ፡፡ በተለይ ቃለ መጠይቅ የምናደርግላቸው ሰዎች እንደ ማስነጠስና ማሳል ያሉ ያተነፋፈስ የህመም ምልክቶች ሲታይባቸው የተለየ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል፡፡
እኛ ጋዜጠኞች ቀደም ሲል የጤና ችግር ካለባቸው ሰዎች፣ የቫይረሱ ምልክት ከሚታይባቸው ጋር ንክኪ ካላቸው ሰዎች፣ የኮቪድ-19 ህሙማን ወይም ለቫይረሱ ተጋላጭ በሆኑ ቦታዎች ከሚሰሩ ሰራተኞች ጋር ቃለ መጠይቅ ስናካሂድ በቂ ርቀታችንን መጠበቃቻን ልናስተውል ይገባል፡፡
- እጆቻችንን ለ20 ሴኮንዶች በሳሙናና በሞቀ ውኃ አዘውትረን በደንብ መታጠብና እጆቻችንን በሚገባ ማድረቃችንንም ማረጋገጥ፡፡ እጅን በደንብ ስለመታጠብና ማድረቅ የሚያስረዳ መመሪያ በዓለም የጤና ድርጅት ድህረ-ገጽላይይገኛል፡፡
- ሙቅ ውኃና ሳሙና በአካባቢው ከሌለ፣ ሳኒታይዘር ወይም ለዚሁ የተዘጋጁ መጥረጊያዎችን መጠቀም ይቻላል፡፡ ይሁንና፣ በተገኘው አጋጣሚ፣ ወዲያውኑ በሞቀ ውኃና ሳሙና መታጠብ ግድ ይላል፡፡ (በዚህ ረገድ፣ ከ60% በላይ ኢታኖል ወይም ከ70% አይዞፕሮፓይል የተዘጋጁ ሳኒታይዘሮች ውጤታማ እንደሆኑ ሲ.ዲ.ሲ ይመክራል፡፡ሳኒታይዘርን መጠቀም በምንም አይነት አዘውትሮ እጅን መታጠብን ሊተካ እንደማይችል ላፍታ እንኳ መዘንጋት የለብንም፡፡
- ስናስል ወይም ስናስነጥስ ሁሌም አፋችንን መሸፈን አስፈላጊ ነው፡፡ ስናስል ወይም ስናስነጥስ ሶፍት ከተጠቀምን፣ ሶፍቱን ወዲያውኑ በጥንቃቄና በተገቢ ሁኔታ ማስወገድ አለብን፡፡ ይህንን ካደረግን በኋላም እጃችንን በሚገባ መታጠብ ይኖርብናል፡፡
- በቢ.ቢ.ሲ እንደ ተገለጸው፣ፊትን፣ አፍንጫን፣ አይን ናጆሮን ወ.ዘ.ተ አለመንካት፡፡
- ሌሎች ሰዎች በተጠቀሙበት መጠጫ ወይም የምግብ መመገቢያ እቃዎች አለመጠቀም፡፡
- ሌሎች ሰዎች በተጠቀሙበት መጠጫ ወይም የምግብ መመገቢ ያእቃዎች አለመጠቀም፡፡
- መላ ጸጉራችን መሸፈን አለበት።ጸጉራችን እረጅም ከሆነ ደግሞ በደንብ መታሰርና መጠቅለል ይኖርበታል።
- የኮቪድ-19ን ስርጭት መዘገብ ከመጀመራችን በፊት ጌጣ ጌጦችንና የእጅ ሰዓቶችን አወላልቀን ማስቀመጥ፡፡ ይህን ማድረግም የሚያስፈልገን፣ የኮቪድ-19 ቫይረስ፣በተለያዩ እቃዎች ላይ ለሰዓታት በሕይወት መቆየት ስለሚችል ነው፡፡
- መነጽር የምናደርግ ከሆነም፣ አዘውትረን በውኃና በሳሙና ማጽዳት፡፡
- ከተቻለ፣ሥራ ላይ ስንሆን ዓይን ዉስጥ የሚሰኩ ሌንሶችን (contact lenses) ከማድረግ እንቆጠብ፤ ሳናስበው ዓይኖቻችንን ስንነካካ ሌንሶቹን መነካካታችን ስለማይቀር በቫይረሱ የመያዛችን ዕድል ከፍ ይላል፡፡
- የምንለብሳቸውን የልብስ አይነቶች ስንመርጥ የትኞቹ የልብስ ዓይነቶች በቀላሉ ሊፀዱ እንደሚችሉ ከግምት ውስጥ ማስገባት አለብን፡፡ ስራችንን ከጨረስንም በኋላ፣ የተጠቀምንባቸውን ልብሶች በሙቅ ውኃና በሳሙና በደንብ መታጠባቸውን ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡
- ከተቻለ፣ ወደ ስራ ስንሰማራ ጥሬ ገንዘብ ከመያዝ እንቆጠብ፤ በተጨማሪም፣ ክሬዲት/ዴቢት ካርዶቻችንን፣ የብር መያዣ ወይንም ሌሎች ቦርሳዎቻችንን በየጊዜው በደንብ እናፅዳ፡፡
- ሁሌም ለሰዎች ቃለ መጠይቅ ስናደርግ ከቤት ውጭ እናካሂድ፡፡ ቃለ መጠይቁን ስናደርግ እቤት ውስጥ ማካሄድ ካለብን፣ አየር በድንብ የሚዘወዋርበትን ቦታ (ለምሳሌ፣ መስኮቶቹን በመከፋፈት) እንምረጥ፡፡
- ወደተሰማራንበት ስራ ለመሄድ ወይም ከዚያ ለመመለስ የምንጠቀምበትን የመጓጓዣ ዓይነት ከግምት ውስጥ ማስገባት አለብን፡፡ የብዙኃን መጓጓዣዎች በሚጨናነቁበት ሰዓት መጓጓዝን ማስወገድ ይኖርብናል፡፡ ጉዟችንን እንደጨረስን፣
በሳኒታይዘር እጆቻችንን መጠራረግ ተገቢ ነው፡፡ የራሳችንን መኪና የምንጠቀም ከሆነ ደግሞ፣ ባጋጣሚ በቫይረሱ የተያዘ ሰው ከጫንን፣ ቫይረሱ በመኪናው ውስጥ ወዳሉ ሰዎች እንደሚተላለፍ መዘንጋት የለብንም፡፡
- በየስራችን ጣልቃ እረፍት መውሰድ እንዳለብን ለአፍታም መዘንጋት የለብንም፡፡ በስራ የተዳከሙ ሰዎች ንጽህናቸውን በአግባቡ መጠበቅ እንዳለባቸው ሊረሱ ይችላሉ፡፡ ለስራ ወደ ተስማራንበት ቦታ ስንሄድ ወይም ስንመለስ ለረጅም ሰዓት ማሽከርከር ሲኖርብን ደግሞ፣ ሁኔታው ከዚህ የከፋ ሊሆን ይችላል፡፡
- በቫይረሱ ወደ ተጋለጠ ቦታ ከመሄዳችን በፊት፣ በቆይታችን ወይም የነበርንበትን ቦታ ስንለቅ፣ ምንጊዜም እጆቻችንን በሙቅ ውኃና በሳሙና በደንብ መታጠብ አለብን፡፡
- በቫይረሱ መያዛችንን የሚያመለክቱ ምልክቶች (በተለይም ትኩሳት ወይም የትንፋሽ ማጠር) ከታዩብን፣ የህክምና አገልግሎት የምናገኝበትን መንገድ ማሰብ አለብን፡፡ በአሁኑ ሰዓት፣ ብዙ የመንግስት የጤና አካላት ቫይረሱን ወደ ሌላ እንዳናስተላልፍ እራሳችንን እንድናገል ይመክራሉ፡፡ ለቫይረሱ በከፍተኛ ደረጃ የተጋለጠ ቦታ የተገኘን ከሆነ፣ በኮቪድ-19 በተያዙ ብዙ ሰዎች ጋር የመገናኘት እድላችን ከፍ ይላል፡፡ ይህ ደግሞ በቫይረሱ የመጋለጣችንን ዕድል ከፍ የደርገዋል፡፡
- ስጋና እንቁላልን አብስለን እንመገብ፡፡
መሳሪያዎችን በጥንቃቄ ስለመያዝ
ኮቪድ 19 በቫይረሱ በተበከሉ መሳሪያዎች አማካኝነት እንደሚዛመት የተረጋገጠ ነገር ነው፡፡ ስለሆነም፣ መሳሪያዎቻችንን ማጽዳትና ከጀርሞች ነጻ የማድረግ ልምድ የምንጊዜም ተግባራችን መሆን አለበት፡፡
- ከሚሰኩ ማይኮች ይልቅ፣ አቅጣጫ አመልካች(directional ‘fishpoles’)ማይኮችን በበቂ ርቀት መጠቀም፡፡
- ሁሌም ከሥራ በኋላ ፣ የማይክ ሽፋኖች፣ ከጀርም መጽዳትና በፈላ ውሃና በፈሳሽ ሳሙና መታጠብ አለባቸው፡፡
- ሽፋኖችን በጥንቃቄ በማውለቅ ካንዱ ወደሌላው ሊተላለፍ የሚችልን ብክለት ለመከላከል የሚያስችለንን ስልጠና/ መመሪያ ከሚመለከተው አካል ጠይቀን ማግኘት አለብን፡፡ በተቻለ መጠን፣ እንደ ዊንድ መፍ (‘wind muff’) ያሉ የማይክ መሸፈኛዎችን ከመጠቀም እንቆጠብ፡፡
- በተቻለ መጠን፣ ዋጋቸው ረከስ ያሉ የጆሮ ማዳመጫዎችን ተጠቅመን እንደምንጥላቸው (በተለይም እንግዶቻችን የተጠቀሙባቸውን ) እናስብ፡፡ ሁሌም የጆሮ ማዳመጫዎችን ከመጠቀማችን በፊትና ከተጠቀምንባቸው በኋላ መጠራረግና ከጀርም ማጽዳታቸንን አንዘንጋ፡፡
- ርቀታችንን ጠብቀን ያለስጋት ስራችንን መስራት የሚያስችሉንን ረጃጅም ሌንሶች እንጠቀም፡
- በተቻለ መጠን፣ ገመድ አልባ የሆኑ ተንቀሳቃሽ መሳሪያዎችን እንጠቀም፡፡
- ስራችንን ስናጠናቅቅ የተጠቀምንባቸውን መሳሪያዎች በምን እግባብ ማስቀመጥ እንዳለብን እናሰተውል፡፡
- የምንችል ከሆነ እየተጠቀምንበት ያለውን መሳሪያ ከፕላሰቲክ በተሰራ መሸፈኛ ዙሪያዉን እንጠቅልለው፡፡ ይህን በማድረጋችን፣ የመሳሪያችንን የውጭ አካል በቫይረሱ ከመበከል እናድነዋለን፡፡ በተጨማሪም፣ መሳሪያውን በቀላሉ ለማጽዳትና ከጀርም ነጻ ለማድረግ ያስችለናል፡፡
- በደንብ ቻርጅ የተደረጉ ተጨማሪ ባትሪዎችን በመያዝ ስራ ላይ እያለን ባትሪን ቻርጅ ከማድረግ እንቆጠብ፤ ይህንን ስናደርግ መሳሪያችንን በቫይረሱ ከመበክል እናድነዋለን፡፡
- ፈጣን ምላሽ የሚሰጡ፣ እንደ ሜሊስፕቶል ያሉ ጸረ-ጀርም መጥረጊያዎችን በመጠቀም መሳሪያዎችን በሚገባ እናጽዳ፤ አስከትሎም፣ የእጅ ስልኮችን፣ታብሌቶችን፣መሰኪያዎችን፣ላፕቶፖችን፣ ሃርድ ድራይቮችን፣ካሜራዎችን፣ የይለፍ ካርዶችንና ገመዶችን በሳኒታይዘር እናጽዳ፡፡
- የተጠቀምንባቸውን መሳሪያዎች ወደ ቦታቸው ከመመለሳችን በፊት፣ ከብክለት ነጻ መሆናቸውን ማረጋገጥ፤ እነዚህን መሳሪያዎች የሚጠቀሙ ሌሎች ባለሙያዎችም መሳሪያዎቹን እንዴት በንጽህና የመያዝና ከብክለት ነጻ የማድረግ እውቀትና ስልጠና ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፤ ምንም ዓይነት መሳሪያ እንዲያው ዝም ብሎ ያልተተወ እና ለተገቢው ሰው በአግባቡ የተመለሰ መሆኑን ማረጋገጥ፡፡
- አንድን ተሽከርካሪ ለስራ ተጠቀመን ካበቃን በኋላ፣ የተሽከርካሪው የውስጥ አካል ተገቢው ስልጠና ባላቸው ባለሙያዎች አማከኝነት ሙልጭ ተደርጎ በደንብ መጸዳቱን ማረጋገጥ፤ ጽዳቱ ሲከናወን የተሽከርካሪው የበር እጀታዎች፣ የማርሽ መቀየሪያን፣ የእጅ ፍሬንን፣ መሪው፣ጎን መስታዎቶች፣የአንገት መደገፊዎች፣ የተሸከርካረ ቀበቶዎች፣ ዳሽቦርዶችና ሌሎች የሚነካኩ ቁልፎች ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡
የኤሌትሪክ መሳሪያዎችን ስለማጽዳት
የኤሌትሪክ መሳሪያዎችን ለማጽዳት የሚከተሉት ነጥቦች እንደ መመሪያ ሊያገለግሉን ይችላሉ። የምንጠቀምበትን አንድን መሳሪያ ለማጽዳት ክመሞከራችን በፊት፣ ሁሌም መሳሪያውን ያመረተው ድርጅት ያዘጋጀውን መመሪያ በሚገባ ማንበብ ይኖርብናል።
- ሁሌም የኤሌትሪክ መሳሪያዎችንና የኤሌትሪክ ገመዶችን ከሶኬቶች መንቀል/ማላቀቅ አለብን።
- ፈሳሸ ንገሮችን ከመሳሪያዎቻችን እናርቅ፤ መሳሪያዎቻችንን ለማጽዳት ብሊቾችን፣ የሚረጩ መርዞችን አንጥቀም። እንደዚያ ካደርግን፣ መሳሪያዎቻችን እንጎዳቸዋለን።
- መሳሪያዎቻችን ላይ ምንም ነገር አንርጭ።
- መሳሪያዎቻችን ለማጽዳት ለስላሳ አና ሸካራነት የሌላችው ጨርቆችን አንጠቀም።
- ለማጽዳት የምንጠቀምበትን ጨርቅ ትንሽ ውሀ አናስንካው አንጅ አንንከረው።
- መሳሪያዎችንን ደግመን ድጋግመን በደንብ አንጠራርገቸወ::
- ክፍተት ያላቸው የኤሌትሪክ መሳሪያዎች (ለምሳሌ ቻርጅ የማድረጊያ ሶኬቶች፣ የጆሮ ማዳመጫ ሶኬቶቸ፤ኪቦርዶችን) እርጠበት እንዳያገኛቸው እንጠንቀቅ።
- መሳሪያዎችንን በንጹህ፤ በደረቅና በለስላሳ ጨርቅ እናጽዳ።
- አንዳንድ ፋብሪካዎች ምንም ክፍተት የሌለባችውን መሳሪያዎችን ለማጽዳት የምንጠቀምበት አልኮል ክ70% በላይ የሆነ አልኮልነት (isopropyl alcohol) ሊኖረው አንደሚገባ ይምክራሉ።
- ሁሌም መሳሪያችንን ጸረ-ጀርም ተጠቅመን ከማጽዳታችን በፊት፣ የአምራቹ ድርጅት የሚለውን ማረጋገጥ አለብን፤ አለበለዚያ፣ ጸረ-ጀርሙ መሳሪያችንን ሊጎዳብን ይችላል።
ተጨማሪ ዝርዝር መመሪያዎችን ደግሞ እዚህ መጣጥፍ ዘንድ ማግኘት ይቻላል።
እራስን ለመከላከል የሚያገለግሉ የህክምና መሳሪያዎች
እራስን ለመከላከል የሚያገለግሉ የህክምና መሳሪያዎችን (ተጠቅመን የምንጥላቸው ጓንቶች፣ የፊት ጭንብሎች፣ የመከላከያ ሽርጦች፣ ቱታዎች/በመላ አከላችን የሚጠለቁ ልብሶች ተጠቅመን የምንጥላቸው የጫማ መሸፈኛዎች) በጥንቃቄ ማጥለቀና ማውለቅ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ እነዚህን ቁሳቁሶች በአግበቡ ለመጠቀም ደግሞ መልካም የጥንቃቄ ተሞክሮዎችና የአጠቃቀም መመሪያዎችን በትክክል መከተልን ይጠይቃል፡፡ በሲ.ዲ.ሲ የተዘጋጀውን አጠቃላይ መመሪያ ለመመልከት ይህንን እንጫን፡፡ ብክለትን ከአንዱ ወደ ሌላው የማስተላለፍ አደጋ ከፍተኛ ስለሆነ፣ እነዚህን መመሪያዎች ከመተግበር ልንዘናጋ አይገባም፡፡ ከተጠራጠርን፣ ወደ ስራ ከመሰማራታችን በፊት የባለሙያ መመሪያ እና ስልጠና እንጠይቅ።
በብዙ ሀገሮች፣ እራሰን ለመከላክል የሚያግለግሉ የህክምና መሳሪያዎች ከፍተኛ የአቅርቦት እጥረት አለ፤ በምሆኑም፣ እነዚሀን መሳሪያዎች መጠቀማችን እጥረቱን ሊያባብስው እንድሚችል ልብ እንብል።
ሁሌም እውቅና ባላቸው ድርጅቶች የተመረቱ እና የጥራት ደረጃቸው የጠበቁ ራሰን ለመከላከል የሚያገለግሉ የህክምና መሳሪያዎችን እንጠቀም፤ ይህንንም ስናደርግ፣ ለጥንቃቄ የተቀመጡ መስፈርቶች መሟላት አለመሟላታቸውን እናረጋግጥ፡፡ አልጄዚራ እንዳመላከተው፣ ጥራታቸውን ያለጠበቁ መሳረያዎች እንዳሉ ልብ እንበል፤ ኢንተርፖልም እንደዘገበው፣ ተመሳስለው የተሰሩ የማይረቡ ምርቶች ገበያውን ተቀላቅለዋል፡፡ ገበያውን አየመሩ ካሉና ከፍተኛ እውቅና ካገኙ እራስን ለመከላከል ከሚያገልግሉ ቁሳቁሶች መካከል ከፊሎቹን እዚህ ማየት ይቻላል፡፡
- በቫይረሱ በተበከሉ እንደ ህከምና መስጫ ባሉ ተቋማት መስራት ወይም መሄድ ሲኖርብን፣ የመከላከያ ጓንቶችን ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ከላቴክስ (latex) ጓንቶች ይልቅ፣ የኒትሪል (nitrile) ጓንቶች የተሻለ የመከላከል አቅም እንዳላቸው እንገንዘብ።
- በጣም አስጊ በሆኑ እንደ ህከምና መስጫ ባሉ ተቋማት የዘገባ ስራ መስራት ሲኖርብን፣ እራስን ለመከላከል የሚያገለግሉ እንደ የፊት ጭንብሎችና በመላ አካል የሚጠለቁ ልብሶች ያሉ ተጨማሪ ቁሳቁሶችን መያዝ የግድ ይላል፡፡
- እንደ የስራ ጠባይችን ፣ተጠቅመን የምናስወግዳቸው ጫማዎች ወይም ከጫማ በላይ የሚጠለቁ ውኃ የማያበላሻቸው ነገሮች ማድረግ ሊኖርብን ይችላል፡፡ ቦታዎችን ስንለቅ፣ ሁሉንም በደንብ መጥረግ/ማለቅለቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ውኃ የማያበላሻቸውን ከጫማ በላይ የሚጠለቁ ነገሮችን ከተጠቀምን በኋላ፣ ቦታውን ከመልቀቃችን በፊት በጥንቃቄ ልናስወግዳቸው ይገባል፡፡
- እራስን ለመከላከል የሚያገለግሉ የህክምና ቁሳቁሶችን ስናደርግ/ስንለብስ፤ የሰለጠነ የባላሙያ ድጋፍ እንዲኖረን ይመከራል። ይህንን የምናደርገው፣ ከጥንቀቄ ጉድለት ሊከሰት የሚችለውን ለቫይረሱ የመጋለጥ አደጋ ለመቀነስ ነው፡፡ በዚህ ረገድ፣
በኢራን የጤና አገልግሎት የተዘጋጀውን ይህንን ቪዲዮ መመልከት ይበጃል፡፡ ይሁንና፣ ቪዲዮው ስልጠናን/የባለሙያ ድጋፍን
ሊተካ እንደማይችል ልብ ይሏል፡፡
-
በምንም ዓይነት፣ የተጠቀምንባቸውን ጓንቶች፣ በመላ አካል የሚጠለቁ ልብሶች እና ሽርጦችን መልስን መጠቀም የለብንም፡፡ በቫይረሱ የተጠቃውን ቦታ ከመልቀቃችን በፊትም፣ እራስችንን ለመከላከል የተገለገልንባቸውን የተበከሉ የህክምና ቁሳቁሶች ባግባቡ ማስወገዳችንን እናረጋግጥ፡፡
የፊት ጭንብሎች
አስከ አሁን ድረስ፣ የኮቪድ 19 ምልክት ያልታየባቸው የህብረተስብ ክፍሎች የፊት መሸፈኛ ጭንብልን መልበስ እንዳለባቸው ወይም እንደሌለባቸው ስምምነት ላይ አልተደረስም፡፡ የአሜሪካው የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል፣ የቫይረሱ ምልክት ያልታየባቸው ሰዎች በህብረተሰቡ መሀል ሲዘዋወሩ ከጨርቅ የተሰሩ የፊት መሸፈኛዎችን አንዲያደርጉ ይመክራል፡፡ ይሁንና፣ ከፍተኛ ዕጥረት የሚታይባቸውን ለህክምና አገልግሎት የተሰሩ የፊት ጭንብሎች እንዳይደረጉ ያሳስባል፡፡ በሌላ በኩል፣ የአለም የጤና ድርጅት፣ የፊት ጭንብል እንድናደርግ በአካባቢ ባለስልጣናት አስከአልተነገርን ድረስ፣ ለአደጋ በተጋለጡ እንደ ሆስፒታል ባሉ ቦታዎች እስከአልስራን ድረስ ወይንም በቫይረሱ ለተጠረጠረ ሰው እንክብካቤ እምናደርግ ካልሆነ በሰተቀር፣ የፊት ጭንብል መልበስ አስፈላጊ አይደለም ይላል፡፡
ባግባቡ ካልተጠቀምንባቸው ፣ የፊት ጭንብሎች በቫይረሱ ለመለከፍ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ የሚሉ ስጋቶች አሉ፡፡ ላንሴት( Lancet)
ያደረገው የቅርብ ጊዜ ጥናት እንደሚያሳየው፣ በቫይረሱ በተጋለጠ አካባቢ የተደረገ የህክምና የፊት ጭንብል፣ ቫይረሱን ለሰባት ቀናት ይዞ ሊቆይ ይችላል፡፡ ይህ ጥናት እንደሚያሳየው፣ ጭንብልን ማድረግ፣ መልሶ መጠቀም ወይንም ጭንብሉን እንዳደረጉ ፊትን መነካካት እራስን ለቫይረሱ በከፈትኛ ደረጃ ማጋለጥ ማለት ሊሆን ይችላል።
የፊት ጭንብልን የግድ ማድረግ ካለብን ደግሞ፣ የሚከተሉትን ምከሮች መተግበር የግድ ይላል፤
- አስፈላጊ ከሆነ፣ ከህክምና ጭንብል ይልቅ፣ ኤን 95ን (ወይም ኤፍ.ኤፍ.ፒ2ን/ ኤፍ.ኤፍ. ፒ3ን) መጠቀም ይመከራል፡፡ የምናደርገው ጭንብል፣ የአፍንጫችንን የላይኛውን ጫፍና የአገጫችንን ጠርዝ መሸፈኑን ማረጋገጥ አለብን፡፡ ይህም፣ የምናደርጋቸው ጭንብሎች ፊታችን ላይ በደንብ ልክክ እንዲሉ ያግዘናል፡፡
- በተጨማሪም ጭንብሉ በደንብ መወጠሩንና በመሃል ክፍተት አለመኖሩን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ፊታችን ላይ ያሉ ፀጉሮችም በየጊዜው መላጨት ይኖርባቸዋል፡፡
- ካደረግነው በኋላ፣ ጭንብሉን መንካት የለብንም፡፡ ጭንብሉን ልናስወግድ ስንፈልግም ማሰሪያውን ብቻ በመጠቀም መሆን አለበት፡፡ ፊት ለፊት ያለውን የጭንብሉን አካል በጭራሽ መንካት የለብንም፡፡
- የፊት ጭንብሉን ካስወገድን በኋላ፣ እጆቻችንን በሳሙናና በሙቅ ውኃ መታጠብ አለብን፡፡ ወይም ደግሞ፣ የአልኮል ሳኒታይዘር(60% በላይ ኢታኖል ወይም 70% አይዞፕሮፓይል) ተጠቅመን እጆቻችንን ልናፀዳ ይገባል፡፡
- ጭንብሉ እርጥበት ሲያገኝው፣ በአዲስ፣ በንፁህና በደረቅ ጭንብል መተካት ተገቢ ነው፡፡
- የተጠቀምንበትን ጭንብል በጭራሽ በድጋሚ መጠቀም የለብንም፡፡ የተጠቀምንበት ጭንብልም ወዲያውኑ ክዳን ባለው የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ መጣል አለብን፡፡
- ጭንብልን መጠቀም፣ራሳችንን ከምንከላከልባቸው መንገዶች አንዱ ብቻ መሆኑን ማስተዋል ተገቢ ነው፡፡ ከጭንብሉ በተጓዳኝ፣ እጆቻችንን አዘውትረን በሙቅ ውኃና በሳሙና መታጠብና ፊታችንን፣ ማለትም ዓይኖቻችንን፣አፋችንን፣ ጆሮዎቻችንን እና አፍንጫችንን ከመነካካት መቆጠብ አለብን፡፡
- እንደ አካባቢው ሁኔታ፣ የፊት ጭንብል እጥረት ወይም የዋጋ ማሻቀብ ሊያጋጥም እንደሚችል ልንገነዘብ ይገባል፡፡
የዲጂታል ደህንነት
- ስለ ኮቪድ-19 ቫይረስ ስርጭት የሚዘግቡ ጋዜጠኞች የኢንተርኔት ጥቃት ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡ እራሳቸውን ለመከላከል በሲ.ፒ.ጄ የተሰነደውን መልካም ተሞክሮ በጥንቃቄ በመመርመር ራሳችንን ከጥቃት እንታደግ፡፡
- የኮቪድ-19ን ስርጭት ለመከታተል፣ መንግስታትና የቴክኖሎጂ ድርጅቶች በየጊዜው ቅኝቶችን ያደርጋሉ፡፡ የዜጎች ቤተ ሙከራ(Citizen Lab)እንደሚለው፣ ይህ ቅኝት በፒጋሰስ (Peagasus) የተሰራውን ኤን.ኤስ.ኦ ቡድን (NSO Group) ይጨምራል። ስራውም ጋዜጠኞችን ኢላማ ባደረጉ የስለላ መረቦችን(Spyware) መከታተል ነው፡፡ አለም አቀፋዊ ግልጽነት (Tranasparency Internantional)) የተስኘው ተቋም እነዚህን ሂደቶች እየተከታተለ በድህረ ገፁ ያሰፍራል፡፡
- ከኮቪድ-19 ጋር የተያያዙ መረጃዎችን የያዙ ሊንኮችን ከመጫናችን ወይም ከማውረዳችን በፊት፣ ቆም ብለን በአንከሮ ማስብ ይኖርብናል፡፡የኤሌክትሪክ ድንበር ማህበር (Electronic Frontier Foundation) ጥናት እንደሚያሳየው፣ ወንጀለኞች ወቅታዊውን የጤና ቀውስና መደናገጥ ተጠቅመው ግለሰቦችና ድርጅቶችን ኢላማ እያደረጉ ነው፡፡ የጥቃታቸው ደረጃም የተወሳሰቡ የኢንተርኔት የማጥቂያ ዘዴዎችን በመጠቀም የእኛን የጋዜጠኞችን መሳሪዎች እስከ ማኮላሸት ደርሷል፡፡
- ኮቪድ-19ን በተመለከተ መረጃ የሚሰጡ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ወይንም መልክት መላላኪያ መተግበሪያዎችን (messaging apps) ከመጫናችን በፊት፣ ኮምፒውተሮቻችንን ሊያጠቁ ወደሚችሉ አደገኛ ቫይረሶች (malware) ሊያገናኙን እንደሚችሉ አውቀን ጥንቃቄ አናድርግ፡፡
- በግለሰቦች ላይ በማነጣጠር የግል ፋይልን ከመነተፉ በኋላ፣ ፋይላችንን ለማስመለስ ገንዘብ የሚያሰከፍሉ እንደ ኮቪድ-19 መከታተያ((Tracker)) ያሉ መተግበሪያዎች እንዳሉ ልብ አንበል፡፡
- ስለኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ የሚያሳዩ እንደ አለም የጤና ድርጅት ካሉ ከታወቁ የመረጃ ምንጮች ያሉ ካርታዎችን በማሳየት የይለፍ ቃላትን የሚመነትፉ ጎጂ የኮምፒውተር ቫይረሶች (Malware)እንዳሉ ተረጋግጧል፡፡
- በጋርዲያን (The Guardian) እንደተዘገበው፣ በመንግስት የታገዘ የሀሰት መረጃ እንዳለ ልንገነዘብ ይገባል፡፡ እንደዚህ ያለውን አጠቃላይ የሀሰት መረጃ በተመለከተ፣ የአለም ጤና ድርጅት ጥንቃቄ እንዲደረግበት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡፡ ቢ.ቢ.ሲም በቂ ማስገንዘቢያ አለው፡፡ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ድባቅ መምቻ (myth buster)) መመሪያም በአለም ጤና ድርጅት ድህረ-ገጽ ላይ ይገኛል፡፡
- በመልክት መላላኪያ መተግበሪያዎች አማካኝነት የሚተላለፉ ሀሰተኛ ዜኛዎችና አሳሳች መረጃዎችም እንዳሉ ልናውቅ ይገባል፡፡
- ፌስቡክ ላይ የሚገኙ አንዳንድ የኮቪድ መልክቶች፣በሰዎች ፋንታ፣ በአርቴፊሻል ኢንተሌጀንስ አማካኝነት እየተቀነባበሩ እንደሚሰራጩ ተደርሶበታል፤ እንዲያውም፣ ተገቢነት ያላቸው መልክቶች ስህተት (error )ተብለው እሰከ መፈረጅ ደርሰዋል፡፡
- በኢንተርኔት ኮንፈርንሶች እና በግል ኑሮ ጉዳዮች (privacy issues) ዙሪያ የተጻፉ ፅሁፎችን እናብብ፤ ይህንን ስናደርግ ፣ እነዚህ አገልግሎቶች መረጃዎቻችን ላይ ምን እንደሚፈጽሙ፣ የትኞችን መረጃዎች ማግኘት እንደሚችሉ፣ ከአደጋ ነጻ የሆኑ መረጃዎች የትኞቹ እንደሆኑ ለማወቅ የሚያስችል ግንዛቤ ይኖረናል፡፡ ባሁኑ ጊዜ በርካታ ሰዎች ስራቸውን እቤታቸው ሆነው በማከናወን ላይ ይገኛሉ፤ ይህንንም ተከትሎ፣ ብዙዎቹ የኢንተርኔት መንታፊዎች ኢላማ እየሆኑ እንደመጡ ልብ ልንል ይገባል፡፡
- በአምባገነን መንግስታት በሚመሩ አገሮች ስለኮቪድ-19 ስርጭት መዘገብ አደጋ እንዳለው መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ እነዚህ መንግስታት አዘጋገቡን በአንክሮ ይከታተሉታል፡፡ በሲ.ፒ.ጄ እንደተለገጸው፣ አንዳንድ መንግስታት፣የቫይረሱን ስርጭት መጠን ለመሸሸግ በሚያደርጉት ጥረት፣ ሚዲያውን ሳንሱር እስከ ማድረግ ይደርሳሉ፡፡
ወንጀል እና በስራ ላይ ስለሚደረግ አካላዊ ጥንቃቄ
የአለም አቀፉ የኢኮኖሚ ሁኔታ እያሽቆለቆለ መቀጠሉን ተከትሎ፣ በርካታ ሰዎች ወደ ድህነት እየተዘፈቁ ሲመጡ፣ የወንጀል ተግበራት እየጨመሩ የመሄድ ሁኔታ እሙን ነው፡፡
- በአሁኑ ጊዜ፣ ብዙ የከተማ አከባቢዎች ወና እየሆኑ በመምጣታቸው፣ የፖሊስ አቅምም በዚያው መጠን አየሳሳ ነው፡፡ ወንጀለኞችም ይህንን አጋጣሚ ከመጠቀም አይመለሱም፡፡ አንዳንድ ጋዜጠኞች፣ የወንጀለኞች ኢላማ እየሆኑ አየመጡና እሰከ መደብደብ ድረስም እንደደረሱ ተዝግቧል።
- በተለይ ከገጠራማ ቦታዎች ስንዘግብ ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡’ ኮቪድ 19ን ወደ መኖረያችን ስፍራ ይዘውብን ሊመጡ ይችላሉ በሚል ስጋት፣ እ‘መጤዎች’ ላይ ጥርጣሬ ሊያድርባቸው ወይንም አንሱን ሲያዩ ደማቻው ሊፈላ ይችላል፡፡
- ከእስር ቤት ወይም ከእስረኞች የማቆያ ማዕከላት የምንዘገብ ጋዜጠኞች፣ ከኮቪድ-19 ስርጭት ጋር በተያያዘ፣ አመፅ ወይም ተቃውሞ የሚያስነሱ ታራሚዎች እንደሚኖሩ በንቃት ልንከታተል ይገባል፡፡ ይህ ደግሞ በቅርቡ በጣልያን፣ በናየጀሪያ፣ በኮሎምቢያ አና በህንድ ተከስቷል፡፡
- ከኮቬድ 19 በተያያዘ፣ ከቤት ያለመውጣት ድንጋጌዎችን ተከተሎ፣ በተለያዩ ሀገራት በፖለስ በኩል፣ እንደ አካለዊ ድብደባ፤ አስለቀሽ ጋዘ መጠቀም አና በጎማ ጥይት መደብደብ ያሉ ጠንካራ እረምጃወች እየተወሰዱ እንዳሉ ልብ ልንል ይገባል፡፡
- በታራሚው ህብረተሰብ ሊከሰት የሚችለውን የኮቪድ-19 ስርጭት ለመግታት በማሰብ፣ እንደ አሜሪካ፣ አየርላንድ፣ ኢንዶኔዢያ፣ ፍልስጤም፣ ኢቲዮጲያ፣ እና ሶማሊላንድ፣ ኢራን ያሉ ሃገራት ታራሚዎችን ፈትተዋል፡፡ ይህን ተከትሎ፣ የወንጀል መጠን ሊጨምር እንደሚችል መገንዘብ ይገባል፡፡
- የአንዳንድ ቁሳቁሶችን እጥረት ተከትሎም፣ ዝርፊያ እና ቅሚያ እንደሚኖርም ማስተዋል ተገቢ ነው፡፡
- በሲ.ፒ.ጄ እንደ ተገለጸው በአምባገነን ሥርዓት በሚተዳደሩ ሀገሮች የሚሰሩ ጋዜጠኞች ስለኮቪድ-19 ስርጭት በሚዘግቡበት ጊዜ የመታሰር አደጋ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል በንቃት ሊከታተሉ ይገባል፡፡እኛ ጋዜጠኞች አለም ዓቀፋዊ የዘገባ ስራ ሲኖርብን (ከታች እንደታየው) ስለምንሄድበት ቦታ የፀጥታ ሁኔታ አስቀድመን ጥናት ማካሄድ ይኖርብናል፡፡ እስከ አሁን ድረስ፣ በአንዳንድ የሩሲያ ክፍሎች፣ በፈረንሳይ፤ በብራዚል፣ በአሜሪካ፣ በኒጀር፣ በቦሊቪያ፣ በእስራኤል፣ በብራዚል፣ በፓኪስታን በቆጵሮስ እና በዩክሬን እዚያም ኃይል የተቀላቀለባቸው ሁነቶችና ተቃውሞዎች ተከስተዋል፡፡በኢራቅና ሆንግኮንግ ደግሞ ሲካሄዱ የነበሩ ተቃውሞዎች በኮቪድ-19 ምክንያት አልፎ አልፎ ተባብሰው የቀጠሉበት ሁኔታ አለ፡፡
የውጭ ጉዞን ያካተቱ ስራዎች
በመላው አለም በተደነገጉ የጉዞ እቀባዎች የተነሳ፣ በአሁኑ ሰዓት የውጭ ጉዞዎች እጅግ እየቀነሱና በጣም አዳጋች እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ከአገር ውጭ ወጥተን የዘገባ ስራ የምንሰራ ከሆነ የሚከተሉትን ከግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርብናል፤
- ለዘገባ ስራ በተሰማራንበት ቦታ የሚገኙትን የህከምና መስጫ ተቋማት ሁሉ ለይተን ማወቅ አለብን፡፡ አንደ ሕንድ፣ ዚምባብዌ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ፓፑዋ ኒው ጊኒ ባሉ ሃገራት እንደታየው፣ የጤና ባለሙያዎች በትንሸ ወይም ያለምንም ማስጠንቀቂያ የስራ መቆም አድማ ሊመቱ አንደሚችሉ ልብ ልንል ይገባል፡፡ አንዲህ ባሉ ሁኔታዎች፣ እራስን ለመከላከል የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች በቀላሉ ላይገኙ ወይንም ከናካቴው ላይኖሩ ይችላሉ፡፡
- ወደ የምንሄድበት ሀገር በደህናው ጊዜ ልንጠየቃቸው የሚችሉ አስፈላጊ የክትባት አይነቶችን አሟልትን መያዛችንን ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡ የኢንፍሉዌንዛ ክትባትን በመውሰድ ከወቅቱ የቫይረሱ ምልክቶች ጋር በተያያዘ ሊከሰቱ የሚችሉ ውዥንብሮችን ማስወገድ አንችላለን፡፡
- ስለጉዟችን የጉዞ የመድን ዋስትና መግዛት ይኖርብናል፡፡ ብዙ መንግስታት፣ የውጭ ጉዞን በተመለከተ የተለያዩ የጉዞ ምክሮችንና ማስጠንቀቂያዎችን አውጥተዋል፡፡ ከነዚህ መካከል፣ የብሪታንያ የውጭ ጉዳይየ ኮመንዌልዝ ቢሮ፣የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እና የፈርንሳይ የውጭጉ ዳይመስሪያ ቤቶችይ ይገኙበታል፡፡ ስለኮቪድ-19 ለመዘገብ የሚያስችል የጉዞ ፈቃድ ላይሰጥ እንደሚችል ልንገነዘብ ይገባል፡፡
- ልንዘግበው ስለአሰብነውን ሁነት ስናቅድ፣ ብዙ ሃገራት ስለአሰተላለፏቸው ህዝባዊ ስብሰባን ሰለሚከልክሉ ድንጋጌዎች መከታተል አለብን፤ እስከ ምን የህል ቁጥር አንድ ላይ መሆን እንደተፈቀድም እንደዚሁ ማወቅ ተገቢ ነው፡፡
- ልንሄድባቸው ወዳሰብንባቸው ቦታወች ባሁኑ ወቅት ስላሉ ወይም ወደፊት ሰለሚኖሩ የጉዞ እገዳዎች ተከታተልን ማወቅ አለብን፡፡ የውጭ ሀገር ዜጎችን አስመልክቶ ተጨማሪ የጉዞ እቀባዎች ወይም ክልከላዎች እየጨመሩ ሊሄዱ እንደሚችሉም ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል፡፡
- በምንሄድበት ቦታ ሁሉ የድንገተኛ ጊዜ አማራጭ እቅድ ቢኖረን ጥሩ ነው፡፡ ምክንያቱም፣ ያለበቂ ወይንም ያለምንም ማሳሰቢያ፣ ከተሞች፣ ክልሎች ወይንም ሃገራት ቤት የመዋል ወይንም ሙሉ ለሙሉ ያለመንቀሳቀስ ትዕዛዝ ሊያስተላልፉ ይችላሉ፡፡
- በብዙ የዓለማችን ክፍል፣ የየብስ ድንበሮች ተዘግተዋል፡፡ ተጨማሪ የድንበር መዘጋቶች በየቦታው ሊቀጥሉ ስለሚችሉ የድንገተኛ ጊዜ አማራጭ እቅዶች ይህንኑ ታሳቢ ሊያደርጉ ይገባል፡፡
- ከታመምን አንጓዝ፡፡ ብዙዎች የአለም ዓቀፍና አየር ማረፊያዎች፣ ታላላቅ የመጓጓዣ ቀጠናዎችን ጨምሮ፣ ጠንካራ የጉዞ የምርመራ ሥርዓቶችን በስራ ላይ አውለዋል፡፡ በርካታ ተመርማሪ መንገደኞች በእርግጠኝነት ወደ ማግለያ ቦታ ሊወሰዱ ወይም እራሳቸውን አግልለው እንዲቆዩ ሊደረጉ ይችላሉ፡፡
- ብዙ የአየር መንገዶች ከመነሻና ከመድረሻ ቦታዎች ያሉ በረራዎችን በመሰረዛቸው፣ አለም ዓቀፍ የጉዞ አማራጮች በእጅጉ ተመናምነዋል፡፡
- የጉዞ ትኬቶች ስንገዛ፣ ጉዟችን ቢሰረዝ፣ ገንዘባችን ሙሉ በሙሉ ተመላሽ እንደሚሆን ማረጋገጥ አለብን፡፡ አዳዲስ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት፣ ኮቪድ-19፣ በብዙ አየር መንገዶች ታላቅ የገንዘብ ኪሳራ አድርሷል፡፡
- አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ይዘን መሄድ እንዳለብን አንዘንጋ፡፡በፍርሃት በገፍ መግዛት(panic buying) የተነሳ፣ በብዙ ቦታዎች ከፍተኛ የቁሳቁስ እጥረቶች ታይተዋል፡፡ በዋናነት እጥረት ከታየባቸው እቃዎች የፊት ጭንብሎች፣ የእጅ ሳኒታይዘሮች፣ ሳሙናዎች፣ የታሸጉ ምግቦችና የሽንት ቤት ወረቀቶች ይጠቀሳሉ፡፡ የስራ ማቆም አድማ ወይም በቫይረሱ ምክንያት ምርቱን የሚያመርቱ ሰራተኞች እጥረት የተነሳ ሁኔታው ሊባባስ እንደሚችል ማወቅ ተገቢ ነው፡፡
- እንደ ዮርዳኖስ ባሉ የውኃ ዕጥረት ባለባቸው ሀገራት፣ የውኃ ፍላጎቱና እጥረቱ በከፍተኛ ደረጃ ሊያሻቅብ እንደሚችል ልብ ይሏል፡፡
- በጣም ብዙ ሀግሮች ቪዛ መስጠት አቁመዋል፣ የሰጡትንም ቪዛ ስራ ላይ እንዳይውል ያደረጉ አሉ፡፡ ስለሆነም፣ የምንሄድበትን ሀገር የቪዛ ሁኔታ አስቀድሞ ማጣራት ያስፈልጋል፡፡
- የምንሄድበት ሀገር ከኮቪድ-19 ነጻ መሆናችንን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወረቀት መቅረብ እንደሚያስፈልገን ወይም እንደማያስፈልገን አስቀድመን ማረጋገጥ አለብን፡፡ እዚህ ላይ ለዚህ ምሳሌ ማግኘት እንችላለን፡፡
- በብዙ የአየር መንገድ ኬላዎች፣ የጤና ምርመራ እርምጃዎች እና የሙቀት መለኪያዎች ይከናወናሉ፡፡ በመሆኑም፣ የበረራ ፕሮግራማችን እነዚህን ነገሮች ከግምት ውስጥ ማስገባት አለበት፤ የበረራ ዕቅዳችን ተለማጭ (Flexible) ማድረግ ይኖርብናል፡፡ በባቡር፣ በመርከብ ወይንም በአገር አቋራጭ አውቶብሶች ስንጓጓዝም፣ ተመሳሳይ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልገናል፡፡
- አንዳንድ ሀገሮች፣ ለውጭ ሀገር ተጓዦች ብቻ የሚያገለግሉ የአየር ማረፊያዎችና ኬላዎች ስላዘጋጁ፣ ከዚህ ጋር በተያያዘ ስለምንሄድባቸው ሀገሮች ሁኔታ በየጊዜው ማጣራት ተገቢ ነው፡፡
- የምንሄድበት ሀገር ውስጥ ያሉ የዜና ማሰራጫዎች በሃገሪቱ ውስጥ ስላሉ የከተማው እንቅስቃሴዎች የሚዘግቡትን አዘውትሮ መከታተል ጠቃሚ ነው፡፡
ስራችንን ከጨረስን በኋላ
- ሊከሰቱ የሚችሉ የህመም ምልክቶችን ልብ ማለት እና የጤንነታችንን ሁኔታ አዘውትሮ መከታተል፡፡
- ለአደጋ በከፍትኛ ደረጃ ከተጋለጠ የዘገባ ስራ መልስ፣ እራሳችንን አግልለን ማቆየት የግድ ይላል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት የሚሰጡትንም ምክር ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡
- ስለ ኮቪድ-19 የሚወጡ አዳዲስ መረጃዎችን መከታተል አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ደግሞ፣ ስለነበርንበትና ስለመጣንበት ሀገር እየተተገበሩ ስላሉ ሙሉ በሙሉ የማግለል ስርዓቶችን ይጨምራል፡፡
- ያለንበት ሀገር የቫይረሱ የወረርሽኝ ሁኔታን መሰረት በማድረግ፣ ከነበርንበት ቦታ ከተመለስን በኋላ ላለፉት 14 ቀናት ከእነማን ጋርና ከምን ያህል ሰው ጋር እንደተገናኝን ማስታወሻ መያዝ አለብን፡፡ ይህን ማድረግ ምናልባት የቫይረሱ ምልክት ከታየብን፣ የአገኘናቸውን ሰዎች በቀላሉ አፈላልጎ ለማግኝት ይረዳል፡፡
ምልክቶች ሲታዩብን፡
- የኮቪድ-19 ምልክቶችከታዩብን፣ ምልክቶቹ አነስተኛ ቢሆኑም እንኳ ፣ ክአለቆቻችን ጋር ስለሁኔታው በመንጋገር፣ ስራችንን ካጠናቀቅንበት ቦታ በተገቢው የመጓጓዣ ዘዴ ወደ ቤታችን መመልስ አለብን ፡፡ እንደ አገኘን ታክሲ መጠቀም የለብንም፡፡
- ራሳችንና ማህበረሰባችን ለመጠበቅ፣ በአለምጤናድርጅት፣ በሲ.ዲ. ሲእና በየአካባቢው የጤና ባለስልጣናት የሚሰጡ ምክሮችን እንከታተል፡፡
- ምልክት ከታየብን ጊዜ ጀምሮ ቢያንስ ለ7 ቀናት ቤታችንን ለቀን አንውጣ፡፡ እንደዚያ በማድረጋችን ቫይረሱን ወደ ሌላ ሰው ባለማስተላለፍ ማህበረሰባችንን እንጠብቃለን፡፡
- አስቀድመን በማቀድ ከሌሎች እርዳታ እንጠይቅ፡፡ ምን ምን አቅርቦቶች እንደሚያስፈልጉን ለቀጣሪያችን፣ ለጓደኞቻችን እና ለቤተሰቦቻችን ነግረን፣ በራፋችን ላይ እንዲያስቀምጡልን እናድርግ፡፡
- በተቻለ መጠን ቤታችን ውስጥ ካሉ ሰዎች እራሳችንን በ2 ሜትር እናርቅ፡፡
- ከተቻለ ለብቻችን እንተኛ፡፡
- የምንኖርበትን ቤት ከሌሎች ሰዎች ጋር መጋራት ግድ ከሆነ፣ የተጋሩን ሰዎች ራሳቸውን ለ14 ቀናት ማግለል አለባቸው፡፡ ይህንን በተመለከተ ጠቃሚ መመሪያ እዚህ ይገኛል፡፡ቫይረሱን ከአንዱ ወደ ሌላው ላለማስተላለፍ፣ በመታጠቢያ ቤት፣ በመፀዳጃ ቤት፣ በወጥ ቤት እቃዎች አጠቃቀም ዙሪያ የተለየ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡
- በሙቅ ውሃና በሳሙና እጆቻችንን ቢያንስ ለ20 ሴኮንዶች አዘውትረን በደንብ መታጠብ አለብን፡፡
- ለቫይረሱ ተጋላጭ ከሆኑ ቀደም ሲል የጤና ችግር ካለባቸው ሰዎች በተቻለ መጠን እራሳችንን ማራቅ አለብን፡፡
- እራሳችንን አግልለን በቆየንበት ሁኔታ የቫይረሱን ምልክቶች ካልባሱብን በስተቀር፣ ሀገር ውስጥ ወደ የሚገኙ የጤና ባለስልጣናት ስልክ መደወል አይገባንም፡፡
በሲ.ፒ.ጄ ድህረ-ገጽ የሚገኘው የጥንቃቄ “ኪት”” ለጋዜጠኞችና ለዜና ሰዎች ስለ አካላዊ፣ ዲጂታላዊ ስነ-ልቦናዊ ጥንቃቄዎች መረጃዎችና ጠቃሚ ምክሮችን ይሰጣል፡፡ ይህ ደግሞ ስለምርጫና ሊከሰቱ ስለሚችሉህዝባዊአመጾች ተፈላጊ መረጃን ይጨምራል፡፡
በመጨረሻም፡ ጋዜጠኞች በተደጋጋሚ ለስራ የሚጠቀሙባቸውን የኤሌክትሮንክስ መሳሪያዎች በሚገባ ማፅዳት ይኖርባቸዋል፡፡