ክልሎች በየፊናቸው በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትምህርትን በፈለጉበት መንገድ ቀርፀው እየሄዱበት ያለው አካሄድ፣ መስተካከል እንዳለበት የታሪክ ምሁራን  ጠየቁ። አስታራቂ ብሔራዊ ትርክት ለመገንባት የትምህርት አሰጣጡ በጥንቃቄ መፈተሽ እንዳለበት ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር ‹‹ብሔራዊ መግባባት ለዘላቂ ሰላምና አገር ግንባታ›› በሚል ርዕስ፣ የታሪክ ምሁራንና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ዓርብ ታኅሳሰ 30 ቀን 2013 ዓ.ም. የፓናል ውይይት አካሂዷል።


በውይይቱ የተገኙትና ‹‹የታሪክ ሚና በብሔራዊ መግባባትና በአገር ግንባታ›› በሚል ርዕስ ጽሑፍ ያቀረቡት የታሪክ ተመራማሪውና የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ምክትል ዳይሬክተር አበባው አያሌው (ረዳት ፕሮፌሰር)፣ ስለብሔራዊ መግባባት ሲናገሩ፣ ታሪክ ትልቅ አገራዊ ሀብት መሆኑን መረዳት እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈ ትውልዱ አሁንም ስለትናንቱ እያወራና እየተራኮተ የዛሬውን እንዳያጣ ጥንቃቄ መደረግ አለበት፤›› ብለዋል።

ለዚህም ሀብት በሥነ ምግባርና በሥነ ልቦና የሚቀረፅበት ዕድሜ ላይ ያሉና የመጀመርያ ደረጃ ላይ የሚገኙ ተማሪዎች የሚሰጠው ትምህርት፣ ከአገራዊ ፋይዳው በመነሳት መሆን አለበት ብለዋል።

አበባው (ረዳት ፕሮፌሰር) እስከ ስምንተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች የሚሰጣቸው ትምህርት በትክክለኛው እውነታ የተመሠረተና የሌላውን ሳያንቋሽሽ፣ ነገር ግን የራሳቸውን በማዳበር እያደጉ ሲሄዱ የጋራ የሆነ አገራዊ ትርክት እንዲይዙ የሚያስችል ሥርዓት መገንባት እንደሚገባ አክለው ገለጸዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ለዘመናት በተገነባ የተዛባ ብሔራዊ የታሪክ አሰናነድ ምክንያት ኅብረተሰቡን ከአንድነት ወደ ልዩነት፣ ከወዳጅነት ወደ ጠላትነት እንዲያመራ የሚያደርጉ ብሔራዊ ትርክቶችን ሊያስተካክል የሚችል፣ ብሔራዊ ትርክት  እንዲኖር ማድረግ ዋነኛ መፍትሔ እንደሚሆን ተገልጿል።

ብሔራዊ መግባባት በአንድ አገር የሚኖሩ ዜጎች ማንኛውም አገሪቱን በሚችሉ ጉዳዮች ላይ መግባባት ሲደረስ እንደሆነ የገለጹት አበባው (ረዳት ፕሮፌሰር)፣ ‹‹ለአገር ግንባታና  ብሔራዊ መግባባት የታሪክ ትርክቶች ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው፤›› ብለዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ የጋራ ብሔራዊ ትርክት እንዳይኖር የሚያደርጉ ጉዳዮች፣ በተለይም የፖለቲካ አስተሳሰቦች መግነንና ታሪክን ከጊዜያዊ ፍላጎት ጋር እንዲጣጣም ብቻ አድርጎ መቅረፅ ዓይነት አካሄዶች መቅረት አለባቸው ሲሉም አክለዋል።

በውይይቱ ‹‹የታሪክና የፖለቲካ ትስስር መስተጋብር በኢትዮጵያ›› በሚል ርዕስ ጽሑፍ ያቀረቡት ሌላው ተመራማሪው አለማው ክፍሌ (ዶ/ር)፣ ታሪክን ለባለታሪኩ በመስጠት ራሳቸውን ችለው የሚቆሙ የታሪክ ምርምር ተቋማት መገንባት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

‹‹ከዚህ ባለፈ ትውልዱ አሁንም ስለትናንቱ እያወራና እየተራኮተ የዛሬውን እንዳያጣ ጥንቃቄ መደረግ አለበት፤›› ብለዋል።

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *