ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2013 ዓም ድረስ ምስክሮችን ለመስማት ተቀጥሮ የነበረው የእነ አቶ
እስክንድር ነጋ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ተሰብሮ እንዲታይ ለመወሰን ለጥር 5 ቀን 2013 ዓም ተቀጠረ።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የህገመንግስትና የሽብርተኝነት ወንጀል ችሎት ዛሬ ታህሣሥ 28 ቀን 2013 ዓም የተከሳሾቹን ጠበቆች አስጠርቶ እንዳስታወቀው ፣ ተከሳሾች ጥር 5 ቀን 2013 ዓም ችሎት ቀርበው የዓቃቤ ሕግ ምስክሮችን የመስሚያ ቀናትና ጊዜ ለመወሰን ቀጠሮ መሰጠቱን የእነ አቶ እስክንድር ጠበቃ አቶ ሔኖክ አክሊሉ ለሪፖርተር ተናግረዋል።