ስሪላንካ በጊዜያዊነት ፌስቡክን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊ ትስስር ድረ ገጾችን እና እንደ ዋትስአፕ ያሉ የመልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያዎችን ማገዷ ተሰማ።
በሀገሪቱ የሚገኝ ሞባይል ኦፕሬተር ዲያሎግ የተባለ አገልግሎት ሰጪም ቫይበር፣ ኢሞ፣ ስናፕቻት፣ ኢንስታግራም እና ዩትዩብን እንዲዘጋ መታዘዙን ትዊተር ላይ አስፍሯል።
ሀገሪቷ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው በፋሲካ በዓል ወቅት በሀገሪቱ በታጣቂዎች የደረሰው የቦምብ አደጋ ተከትሎ የሃይማኖት ግጭት በመቀስቀሱ መሆኑን አስታውቃለች።

ግጭቱን ተከትለው የሚነዙ ሐሰተኛ ዜናዎችንና መነሻቸው የማይታወቁ ወሬዎችንም ለመከላከል በማሰብ በጊዜያዊነት ማህበራዊ ሚዲያዎቹ ሊዘጉ መብቃታቸውን ባለስልጣናት ተናግረዋል።
የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንደገለጹት የሃይማኖት ተከታዮች ባስነሱት ግጭት ተሳታፊ የነበሩ ግለሰቦች መያዛቸውን አብራርተዋል።
እንዲሁም በማህበራዊ ገጾች ግጭትን አነሳስተዋል ተብለው የተያዙ ግለሰቦች መኖራቸውንም ባለስልጣናቱ ገልጸዋል።
ምንጭ፦ሮይተርስ

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *