በኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት (ኢሴማቅ) አስተባባሪነት ረቡዕ ኅዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም. የሚጀመረው ዘመቻ እስከ ታኅሳስ 1 ቀን 2013 የሚቆይ ነው፡፡ የዓለም አቀፍ የነጭ ሪቫን ቀን፣ የዓለም አቀፍ የኤድስ ቀን፣ የዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን፣ ዓለም አቀፍ የጥቃት ሰለባዎች ቀን፣ የዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከላካዮች ቀንና የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ቀንን መሠረት አድርጎ ፆታዊ ጥቃትን የሚቃወም ንቅናቄ የሚደረግበት እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

ፆታዊ ጥቃትን በመቃወም ላይ ትኩረት ባደረጉት 16 የንቅናቄ ቀናት የሚመለከታቸውን አካላት በማሰባሰብና ልምዶችን በመለዋወጥ የተገኙ ውጤቶችና ያጋጠሙ ችግሮች የሚታዩበት፣ ከዚያም ውሳኔ ሰጪው መንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላት ለጉዳዩ የበለጠ ትኩረት እንዲሰጡ የሚጠየቅበትና ድምፃቸው የበለጠ እንዲሰማ የሚሠሩበት ወቅት እንደሚሆን ኢሴማቅ ንቅናቄውን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ፆታዊ ጥቃትን የሚቃወም የ16 ቀናት ንቅናቄ ተጀመረ

ዘመቻ በፆታዊ ጥቃት – ኢትዮጵያ ቡድን ወቅታዊውን የኢትዮጵያ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ፣ ‹‹ሰላም ለሴቶች ከጓዳ እስከ አገር!›› በሚል መሪ ቃል የሚያካሂደው ንቅናቄ፣ በኢትዮጵያ ተደጋጋሚ የሚፈጸሙ ፆታዊ ጥቃቶች ላይ ልዩ ትኩረት ያደርጋል ተብሏል፡፡

መሪ ቃሉ የተመረጠው በኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት የሚቀሰቀሰውን አለመግባባትና ግጭት ተከትሎ፣ ሴቶችና ወጣት ሴቶች በአመዛኙ የችግሩ ገፈት ቀማሽ መሆናቸውን ታሳቢ በማድረግ መሆኑን ኢሴማቅ ገልጿል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ የኢትዮጵያ ካባቢዎች እየተከሰተ ያለውን አለመረጋጋት ተከትሎ ዜጎች ከመኖሪያ ቀየአቸው በብዛት ሲፈናቀሉ፣ በዕድሜ ለጋ የሆኑ ሴት ሕፃናት ሳይቀሩ ለፆታዊ ጥቃቶች ተጋላጭ  ሊሆኑ እንደሚችሉም በመግለጫው ተመልክቷል፡፡

በ16 የንቅናቄ ቀናት በፆታዊ ጥቃት ምክንያት ከሚከሰቱ ማኅበራዊና ኢኮኖሚዊ ጉዳቶች በተጨማሪ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረጉ ጥሪዎችም ይቀርባሉ ተብሏል፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ግጭት በሚከሰትባቸው ሥፍራዎች መንግሥት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላትና ኅብረተሰቡ በአካባቢያቸው ለሚገኙ ሴቶች ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጡ ማሳሰብን ይጨምራል፡፡

ዓለምን እያስጨነቀ ያለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከጤና ቀውስነቱ በተጨማሪ፣ በኅብረተሰቡ ላይ የሚያሳድረው መጠነ ሰፊ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጫናም ሴቶችና ሕፃናት ላይ በአመዛኙ ጉዳት አድርሷል ያለው መግለጫው፣ የዘንድሮ የዓለም አቀፍ ፆታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ዘመቻ ክብረ በዓል በአንድነት የመቆም ምልክት  የሆነውን ብርቱካናማ ቀለም በማስቀደም ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለማስቀረት የሚከናወኑ ሥራዎችን በገንዘብ መደገፍ፣ መከላከል፣ ተገቢ ምላሽ መስጠትና ተያያዥ መረጃ መሰብሰብን ያማከለ ነው፡፡

ዘመቻ በፆታዊ ጥቃት – ኢትዮጵያ ቡድን ፆታዊ ጥቃት እንዲቆም፣ አገራዊ አጀንዳ አድርጎ ለመሥራት በ1998 ዓ.ም. የተቋቋመ መሆኑ ተገልጿል፡

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *