እንኳን በደህና ወደ ድረገፃችን መጡ! ይህ ድረ ገፅ መነሻውን እና መድረሻውን በሠላም ላይ ብቻ አድርጎ የተዘጋጀው ፕሮግራም ይፋዊ ድረ ገፅ ነው፡፡

በአገራችን በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ምክንያቶች የንፁህ ዜጎች ሕይወት በአሰቃቂ (በአሳዛኝ) ሁኔታ እያለፈ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በእነዚህ አሳዛኝ ጥቃቶች በርካቶች ህይወታቸው አልፎ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ከቤት ከቄያቸው ተፈናቅለው፤ ሌሎች በርካቶችም ለከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ተዳርገዋል፡፡ እንዲህ ያለውን አሳዛኝ ክስተት ለመግታት ደግሞ ሁሉም ወገን የድርሻውን መወጣት ይኖርበታል፡፡ በተለይ ደግሞ ወጣቱ አንድም ግጭቶች ከመቀስቀሳቸው በፊት በመከላከሉ ረገድ በሌላም በኩል ግጭቶች ከተከሰቱ በኋላም ግጭቶችን ለማብረድ የላቀ ሚና ያለው መሆኑ ይታወቃል፡፡

 

እኛም በዚህ ረገድ የተለያዩ በሠላም ላይ ያተኮሩ የሬዲዮ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ማሕበራዊ ሚዲያን ለጥል እና ለመለያት ሳይሆን ለመቀራረብ እና ለአንድነት የሚውልበትን መንገድ በማመቻቸት የድርሻችንን ለመወጣት ተዘጋጅተናል፡፡ በመሆኑም በዚህ ድረገፅ ላይ የሚገኙት ማናቸውም መረጃዎችም መነሻ እና መድረሻቸውን ሠላምን ያደረጉ ናቸው፡፡

በአገራችን ዘላቂ ሰላም ማስፈን የሚቻለው ሁላችንም የድርሻችንን መወጣት ስንችል ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም በሰላም ተከባብሮ በመኖር፣ የዜግነት ግዴታን ስለመወጣት፣ በበጎ ፍቃደኝነት አገልግሎት ስለመሳተፍ እና መሰል ማናቸውም ተመሳሳይ በጎ ነገሮች የተመለከቱን ሐሳቦች ታደርሱን ዘንድ እየጠየቅን በፌስቡክ፣ በቴሌግራምም ሆነ በዩቲዩብ ቻናላችን ቤተሰብ ትሆኑን ዘንድ በዚሁ አጋጣሚ እንጋብዛለን፡፡

የእኛን ድረገፅ በመጎብኘት አንዳች ቁምነገርን እንደሚገበዩ እና በርካታ ጠቃሚ መረጃዎችን ለግሎ ማድረግ እንደሚቻልዎ እርግጠኛ ነን፡፡
መልካም ቆይታ!

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *