ኢሰመኮ “የጋዜጠኞቹ መታሰር አሳስቦኛል” ብሏል

ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ የአዲስ ስታንዳርድ እና የኦ ኤም ኤን 6 ጋዜጠኞች የታሰሩ ሲሆን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የጋዜጠኞቹ እስር በእጅጉ አሳስቦኛል ብሏል።
የፌደራል መንግስት ከህወሓት ጋር ግጭት ውስጥ መግባቱን ተከትሎ የታሰሩት ጋዜጠኞች የተጠረጠሩበትና ያሉበት ሁኔታም ግልፅ አይደለም ተብሏል።
በሳምንቱ ወደ እስር ቤት የተጋዙት ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ይሰሩ የነበሩት ጋዜጠኛ ሀፍቱ ገ/እግዚአብሔር፣ አብርሃ ሃጎስ፣ ፀጋዬ ሀዱሽ እንዲሁም የአዲስ ስታንዳርድ መጽሔት ዋና አዘጋጅ መድህኔ እቁበ ሚካኤል፣ የአውሎ ሚዲያ አዘጋጅ በቃሉ አላምረው እና የኦ ኤም ኤን ጋዜጠኛ ኡዲ ሙሣ መሆናቸው ታውቋል።
የአዲስ ስታንዳርድ ዋና አዘጋጅ መድህኔ እቁበ ሚካኤል ባሳለፍነው ሰኞ ከቢሮው ተወስዶ ታስሮ ፍ/ቤት ቀርቦ የ14 ቀን ቀጠሮ ተጠይቆበት የነበረ ሲሆን ከፍ/ቤት መልስ ከፖሊስ ጣቢያ በመታወቂያ ዋስ ቢወጣም በሌላ ቀን ተመልሶ እንደታሰረ ለማወቅ ተችሏል። አለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች CPJ በበኩሉ ጋዜጠኞቹ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ ጠይቋል።

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *