ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ግለሰቦች የተለያዩ ጥቅሞች ለማግኘት ሲሉ የሃሰት አካውንት በመክፈት ድብቅ አጀንዳቸውን ሲያራምዱ ማስተዋል እየተለመደ መጥቷል፡፡ ይህ ደግሞ ከፍተኛ ተከታይ በሚኖራቸው የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆች ላይ እጅግ ጎልቶ ይታያል፡፡ ከእነዚህ ግዙፍ የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎች ተርታ የሚመደበው የፊስቡክ ኩባንያም በአጅጉ ከሚታማባቸው ጉዳዮች መካከል የሃሰተኛ አካውንት መብዛት ዋነኛውና ቀዳሚው ነው፡፡ ታዲያ ከሰሞኑ የተሰማው ዜና ፌስቡክ ለሃሰተኛ አካውንት መበራከት ትልቅ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን በማሳያነት እየቀረበ ይገኛል፡፡
በጉደዩ ላይ ተጠይቀው ምላሽ የሰጡት የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የኢንተለጀንስ ኮሚቴ የሆኑት እና በፊስቡክ ኩባንያ ውስጥ የማህበረሰብ ኔትዊርክ ዳይሬክተር በመሆን የሚያገለግሉት ሼሪሊ ሳንበርግ በማብራሪያቸው ላይ እንደገለፁት ኩባንያቸው ከስድስት ወራት ጀምሮ የሃሰተኛ አካውንቶችን ለይቶ ለማጥፋት የሚያስችለውን ከፍተኛ ዝግጅት ማከናወኑን ጠቅሰው አሁን ላይ በጠቅላላው ከ1.2 ቢሊዮን በላይ የሃሰተኛ አካውንቶች መሰረዛቸውን አስታውቀዋል፡፡ አንደሳቸው ገለፃ ከሆነ ኩባንየው ይህንን ስራ ለማከናወን የተለያዩ መንገዶችን የተጠቀመ ሲሆን በዋናነት በማንዋል እና አውቶሜትድ ቅኝቶች በመታገዝ የማሽን ለርኒነግ፣ የኮምፒውተር ቪዥን እና የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ አተገባበሮችን በቀዳሚነት መጠቀሙን ጠቅሰዋል፡፡


ፌስቡክ የሃሰት አካውንቶችን በቁጥጥሩ ውስጥ ለማስገባት በሚያደርገው ሂደት ሌሎችን ለመጉዳት የሚፈልጉ አካላት እንዴት የማህበራዊ ሚዲያ ስርዓቱን ለራሳቸው የሃሰተኛ ዜና ማሰራጫ እንደሚጠቀሙበት እና የህዝቡን አመለካከት ወደራሳቸው አፍራሽ አጀንዳ ለመጠምዘዝ እንደሚሞክሩ የተጠቀሰ ሲሆን ለዚህም ኩባንያው በደህንነት ዙሪያ የሚሰራቸውን ስራዎች አጠናክሮ እንዲቀጥል ከሚያስገድዱት ምክንያቶች ውስጥ በቀዳሚነት የሚጠቀስ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ ኩባንያው ቁጥራቸው እጅግ የበዛውን የሃሰት አካውንቶች ለማጥፋት እንዲረዳው ቀድሞ በደህንነት ዙሪያ ያሰማራውን የሰው ሃይል በእጥፍ በመጨመር 20,000 ማድረሱን እና ዘገባዎችን 50 በሚደርሱ የቋንቋ አይነቶች ለመገምገም መሞከሩ የተጠቀሰ ሲሆን በተጨማሪም ከላይ የተጠቀሱ ቴክኖሎጂዎች በስራው ሂደት ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደነበራቸው ተገልጿል፡፡
ምንጭ፡ itmagazine.com

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *