ስሙ በክፉም ይነሳ በደግ ፌስቡክ የዓለማችን ቀዳሚው የማህበራዊ ትስስር መድረክ እና ለብዙዎችም ዋነኛ የዕለታዊ መረጃ ምንጭ መሆኑ አይካድም፡፡ ድረ-ገፁ ያለውን የተጠቃሚ ብዛት የተመለከቱ የመንግስት ሹመኞች፣ የንግድ ድጅቶች፣ የሃይማኖት ስብእናዎች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ ታላላቅ ሚዲያዎች፣ ጦማሪያን ወዘተ… ዕይታቸውን ያሰፍሩበታል ብሎም ምርቶቻቸውን ያስተዋውቁቀበታል፤ ይሸጡበታል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የፌስቡክ መጋረጃ ሲገለጥ የሚያሳየንን ዕውነታዎች ጀባ እንበልዎ፡፡

፩. የተጠቃሚዎች ቁጥር፡- ፌስቡክ በቀን ቢያንስ አንዴ የሚመለከቱት 1.52 ቢሊዮን ታማኝ ደንበኞች ሲኖሩት ይህን ሃቅ በወር ስንለካው ደግሞ 2.32 ቢሊዮን ይደርሳል፡፡

፪. ወደ አንድ ሶስተኛ የሚጠጋው የድረ ገፁ ተጠቃሚ ዕድሜ ከ24-34 ባሉት ውስጥ ብቻ ይገኛል

፫. እሮብ እና ዓርብ ከፍተኛውን የኔትዎርክ ፍሰት ይይባቸዋል

፬. 83 ሚሊዮን ሀሰተኛ ገፆችን (fake profiles) ይዟል

፭. በቀን በአማካይ 300 ሚሊዮን ፎቶዎች ይለቀቃሉ

፮. በአንድ ደቂቃ ውስጥ 510 ሺህ ኮመንቶች ይሰጣሉ

፯. 20 ደቂቃ፡ አንድ ሰው በአማካኝ አካውንቱን በከፈተ ቁጥር የሚያጠፋው ጊዜ

፰. ዕድሜያቸው ከ18-24 ከሆኑ ተጠቃሚዎች ውስጥ ግማሹ ከመኝታቸው በነቁበት ቅፅበት ወደ ፌስቡክ አካውንታቸው ያመራሉ

፱. 4.75 ቢሊዮን፡ በቀን ውስጥ የሚከወን የሼር መጠን

፲. በእያንዳንዷ ሴኮንድ አምስት አዳዲስ አካውንቶች ይከፈታሉ

ምንጭ፡ zephoria.com

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *