በማህበራዊ ድህረ-ገፆች ላይ የሚሰራጭ የሀሰት ዜና ከጊዜ ወደጊዜ ተፅዕኖው በእጅጉ እያየለ መጥቷል፡፡ ዶናልድ ትራምፕን በትረ ስልጣን አስጨብጦ የተደመደመው የ2016ቱ የአሜሪካን ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ደግሞ የሃሰት ዜናን ተፅዕንኦ ለማመላከት የቅርብ ጊዜ ማሳያችን ነው፡፡በብዙዎች ዘንድ በሮቦቶች አማካኝነት የሚዘወሩ የሃሰት ዜና አሰራጭ ስርዓቶች ለዚህ ሁናቴ ተጠያቂ ሆነው ይቀርባሉ፤ ከአዲሱ ጥናት በስተቀር፡፡ የማሳቹሴትስ ኢንስቲቲዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ ተመራማሪው ሶሮሽ ቮሶዊ አማካኝነት የተጠናው ጥናት እናደሚያመላክተው ለዚህ ዋነኛ ተጠያቂ ሮቦታዊ ስርዓቶች ሳይሆኑ ሰዎች መሆናቸውን ነው፡፡
እነዚህ በሰዎች አማካኝነት የሚሰራጩት የሃሰት መረጃን ያዘሉ ዜናዎች የማህበራዊ ሚዲያ መረብ በሆነው ትዊተር ላይ ከእውነተኛ ዜናዎች ስድስት እጥፍ ባደገ ፍጥነት ለሰዎች ተደራሽ ይሆናሉ፡፡ ይህም ሮቦቶችን የሃሰት ዜናዎችን ወደ አርስተ ዜናነት በመለወጡ ሂደት ውስጥ ከደሙ ንፁህ ያደርጋቸዋል፡፡
የ2013ቱን የቦስተን ማራቶን ሽብር ጥቃትን አስመልክቶ ከተተረጠሩት ውስጥ በጊዜው የብራውን ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረውና ባልታወቀ ምክንያት የተሰወረው ተማሪ ከዋነኞቹ ተጠርጣሪዎች መሃል አንዱ ሆኖ ታይቶ ነበር፡፡ ይህም ባልዋለበት ወንጀል ግለሰቡ በብዙሃን ዘንድ ተጠያቂ እንዲሆን አድርጎታል፤ በሃሰት ዜና አማካኝነት፡፡
ታድያ ይህ ጥናት ክስተቱን እንደመነሻ አድርጎ ነበር የተጀመረው፡፡ ቀጥሎም የትዊተር ድህረ ገፅ ስራ ከጀመረበት 2006 አንስቶ ያሉትን ትዊቶ
ች በማሰባሰብና የዜና ይዘት ያላቸውን ለይቶ በማውጣት እንደ ፋክት ቼኪንግ ዶት ኦርግ ባሉ ስድስት የተለያዩ እውነታን አረጋጋጭ ድህረ ገፃዊ ተቋማት ላይ እንዲረጋገጡ ተደረገ፡፡
በ3 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች 4.5 ሚሊዮን ጊዜ ሪትዊት የተደረጉ 126,000 ዜናዎችን ወስደው እውነታዎቹን ከሃሰት በመለየት ስርጭታቸውን ሲመለከቱ እውነተኛዎቹ 1,000 ለሚደርሱ የድህረ-ገፁ ተጠቃሚዎች የሚደርሱት አልፎ አልፎ ሲሆን የሃሰት ዜናዎቹ ግን ከ10,000 የሚበልጡ ተጠቃሚዎች ጋር በቀላሉ ይደርሳሉ፡፡
ከነዚህም አብዛኛዎቹ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ዜናዎች ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ቀጥሎ ባደረጉት ጠለቅ ያለ ምርመራ እነዚህ የሀሰት ዜናዎች እውነትን ከሚናገሩት በላይ በትዊተር ላይ ያልቀረበ አዲስ ሀሳብን ሲያነሱ የሰዎችን የተለያዩ ስሜታዎ ምልሰቶችንም ያካትታሉ፡፡ ይህም ብዙ ሰዎች ጋር ለመድረሱ እንደምክንያት ተጠቅሷል፡፡
ምንጭ፡ Science Magazine