የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ – ኢሰመጉ በትግራይ ክልልና አዋሳኝ ቦታዎች ያለው እንቅስቃሴ የሰላማዊ ሕዝብን የሕይወትና አካላዊ ደህንነት ብሎም የሲቪል ንብረቶችን ደህንነት አደጋ ላይ የማይጥል እንዲሆን እና ሁሉም ወገኖች ግጭት አባባሽ ከሆኑ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪል ማኅበራት፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እና መላው ኢትዮጵያውያን ግጭቱ ተባብሶ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት በመንቀሳቀስ ልዩነቶች በውይይት እንዲፈቱ በሁሉም ወገኖች ላይ ግፊት እና ጫና እንዲያደርጉ ኢሰመጉ ይጠይቃል፡፡ መንግሥትም በየጊዜው በሚፈጠሩ ነገሮች ዙሪያ ተከታታይ መረጃዎችን ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ኢሰመጉ ይጠይቃል፡፡
ሁሉም የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እና ብዙኃን መገናኛ ድርጅቶች ሕዝብን ለግጭት የሚያነሳሱ እና ለሰብዓዊ መብቶች ጥሰት የሚዳርጉ የሐሰት ዜናዎችን፣ የተሳሳቱ፣ የተዛቡ እና የተበከሉ መረጃዎችን ከመናገር እና ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ ኢሰመጉ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *