ሳይበር ቡሊንግ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ ወይም ሳይበር ስፔስ ውስጥ በዋናነት ታዳጊዎች ላይ የሚደርስ ጥቃት ሲሆን፤ እነዚህም ጥቃቶች በተደጋጋሚና ሆን ተብሎ በሌሎች እኩያ ታዳጊዎች የሚፈጸም ነው፤ ለምሳሌ ስም ማጥፋት፣ ያለፍላጎት በቅጽል ስም የመጥራት፣ ማዋረድ፣ ማንቋሸሽ እና ሌሎች አግባብ ያልሆኑ ባህሪያት ወይም ድርጊቶች ናቸው፡፡

ሳይበር ቡሊንግ የምንለው በታዳጊዎች ላይ በሳይበር አለም ላይ ማለትም በፌስቡክ፣ በትዊተር፣ በኢሜል፣ በሞባየል ሜሴጅ፣ ወዘተ ሚዲያዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ሲሆኑ በታዳጊዎች ላይ የስነ ልቦና፣ ማህበራዊ እና ጤና እንዲሁም ህይወት ስጋት እንደሆነ በአለም ላይ በተለያዩ ሀገሮች የተከሰቱ ክስተቶች ያሳናል፡፡

ይህ ጥቃት ከባህላዊው ቡሊንግ የሚለየው በሳምንት 7 ቀናት እንዲሁም በቀን 24 ሰአት የሚፈጸሙ መሆናቸው እና በቦታ የተገደቡ ያለመሆናቸው ነዉ፡፡ የሳይበር ቡሊንግን ለመከላከል የሚያስችሉ የመፍትሄ ሀሳቦች ቤተሰብ ታዳጊዎች ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲጠቀሙ ንቃተ ህሊናቸውን ማሳደግ ቤተሰብ ከታዳጊ ልጆቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት የጓደኝነት ስሜት ያለው እንዲሆን በተቻላቸው መጠን በማድረግ የመረጃ ልውውጡን ማጠናከርና ጥሩ የማማከር እንዲሁም አቅጣጫ የማስያዝ ስራ መስራት፡፡

ቤተሰቦች የልጆቻቸውን ኦንላየን እንቅስቃሴ መቆጣጠር፣ ት/ቤቶች ሳይበር ቡሊንግን አንዱ የትኩረት ከባቢ በማድረግ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ማድረግ፣በት/ቤቶች ግልጽ የሆነ መመሪያዎችን በዚህ ችግር ዙርያ በማውጣት እንዲሁም ችግሩ ሲከሰት ሪፖርት የሚደረግበት መንገድ ማመቻቸት፣ታዳጊዎች ይህ ክስተት/ጥቃት ሲደርስባቸው ለሚመለከተው አካል ወይም ወላጆቻ ሪፖርት የማድረግ ልምድ ማዳበር ፣ ታዳጊዎች የሶሻል ሚዲያ አካውንቶቻቸውን ቅንብር ማስተካከል፡ ማለትም የሚለጥፉት ስዕል፣ የሚጽፉት ጽሁፍ፣ ወዘተ ማን ይየው ወይም ማን ይመልከተው የሚለውን ቅንብር ውስጥ በመግባት ማስተካከል፡፡ ሁኔታው አስቸጋሪ እየሆነ ሲመጣ ያንን ግለሰብ ከጓደኝነት ብሎክ (Block) ማድረግ ወይም ማስወጣት፡፡

ምንጭ – አሳቴኮኮመደኤ

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *