ክሪስቶፈር ጄ ሃይኪ ሚድያው የተጋፈጣቸውን የኢኮኖሚ ተግዳሮቶች ከውስጥ በተነሱ ስትራቴጂዎች እና የቢዝነስ ሞዴል ፈጠራዎችን በማቅረብ መፍትሔ ያስቀምጣሉ።

ከቅርብ ግዜ ወዲህ በ አፍሪካ እና በደቡቡ የዓለም ክፍላት የሚወጡ ርዕሰ አንቀጾች የመደበኛ ሚድያዎች ቢዝነስ የገጠመውን ፈተና እና አዳዲስ አካሄዶች በዚህ ላይ ያገኙትን ድል አስነብበዋል።

የአዳዲስ አካሄዶች ስኬት በተደጋጋሚ የሚታይ ባለመሆኑ የሚድያ ተቋማት ቀጣይነታቸውን ለማረጋገጥ እነዚህን ስኬቶች ለመረዳትና

ለሃገራቸውበሚስማማ መልኩ ለመተርጎም እየተገደዱ ነው። እንዴት የሚድያው ቢዝነስ አሁን ባለበት ሁኔታ ለአንዳንዶች በጣም ምቹ ለሌሎች ደግሞ ፈተና ሊሆን ቻለ? መልሱም ያለው የዲጂታል ግንኙነት አብዮትን ተከትሎ የቢዝነስ ንድፎች/ሞዴሎች/ የሚጫወቱት ሚና ውስጥ ነው።

የቢዝነስ ንድፍ

የቢዝነስ ንድፍ ማለት አንድ ተቋም ለደንበኞቹ ዋጋ ያለው ነገር የሚያቀርብበት መንገድ ነው። ለሚድያ ደግሞ ደንበኞቹ ታዳሚዎች እና አስተዋዋቂዎች ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ተቋሙ ዋጋ ያለውን ነገር የሚያደርስበትን መንገድ እና ከዚህ ጋር የተያያዙ የገንዘብ ወጪ እና ገቢን ይጨምራል። የቢዝነስ ሞዴሉ ውስጥ ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ ሌሎችም ጉዳዮች ያሉ ሲሆን ይህም የተቋሙን አጋሮች፣ ቁልፍ እንቅስቃሴዎች፣ ግብዓቶች፣ የወጪ ገቢ አደረጃጀት፣ የዋጋ ዕቅድ፣ የደንበኞች ግንኙነት፣ የተመቹ ሁኔታዎች፣ የደንበኛ አይነቶች እና የገቢ ምንጮችን ያጠቃልላል። የቢዝነስ ንድፉን መረዳት ዋጋ ያለው ነገር በመፍጠር እና ዋጋ ያለው ነገር  የሚደርስበትን መንገድ በመወሰን የሚድያ ተቋሙን የገንዘብ ስኬት ለማረጋገጥ ይጠቅማል።  ከእነዚህ ጉዳዮች በግባቡ ካልተሰናሰሉ የቢዝነስ ንድፉ የማይመች ሊሆን ይችላል።

ዛሬ ላይ መጠነ ሰፊ የሆኑ አካባቢያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተጽዕኖዎች መጀመሪያውንም በጭንቅ ውስጥ ያለውን የአፍሪካን እና የደቡባዊው የዓለምን ሚድያ ግፊት እያደረጉበት ይገኛል።

ዝርዝሩ ብዙ የሆነ የኢኮነሚ ተጽዕኖም ለዚህ ግፊት አስተዋጽዕ አለው። በ እ.ኤ.አ 2018 በደቡብ አፍሪካ በተደረገ ጥናትና ዘገባ ፕሮፌሰር ሄሪ ዱግሞር የዜና ሚድያ ላይ ሃገሪቷ ያላት አቋም ተለዋዋጭ እንደሆነ ጠቁመዋል። የህትመት ስርጭትን መዳከም፣ የታዳሚዎች ወደሌላ የሚድያ አማራጭ መኮብለል እንዲሁም ለጥናታዊ ጋዜጠኝነት የሚያስፈልገውን የግብዓት መመናመን ተከትሎ የሚድያ ተቋማት የሚያቀርቡትን ይዘት በገንዘብ የሚተምኑበት አቅም ፈተና ውስጥ ወድቋል። ከዚህም ከፍ ያሉ ተጽዕኖዎች በሚድያ ተቋማቱ የአስተዳደር ችግር፣ ውጤታም ባልሆነ የስራ አፈጻጸም እና የገንዘብ ምንጭ በማጣት ፈተናውን ያባብሱታል። ምንም እንኳን እያንዳንዱ የአፍሪካ ሃገራት ያለው ገበያ እንደየ ሃገሩ እየተለያየ ቢሆንም ተመሳሳይ ለውጦች ግን በሁሉም የአህጉሪቷ ክፍሎች መከሰታቸው አልቀረም።

መፍትሔ

ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡት ሃሳቦች የውስጥ ስትራቴጂ እና የቢዝነስ ንድፍ ጽንሰ ሃሳቦችን በመጠቀም እነዚህን ተግዳሮቶች መወጣት ላይ ትኩረት ያደረጉ ናቸው። ሃሳቦቹም የቀረቡት ስኬት ያስመዘገቡ የሚድያ ተቋማትን በተመለከተ ከተሰሩ ጥናቶች ጋር በማያያዝ ነው። ከእነሱ ውጪ ወዳሉ አካላት የሚመለከቱ የአፍሪካ ገለልተኛ የሚድያ ተቋማት ምቹ ያልሆኑ ሁኔታዎች የሚገጥሟቸው ቢሆንም አንዳንድ የሚድያ ተቋማት ግን ግዙፍ ተግባራትን መፈጸም ችለዋል ይህንንም ማድረግ የቻሉት በውስጥ አሰራራቸው ነው።

በአነስተኛና መካከለኛ ደረጃ ላሉት ከተቋሙ ውጪ ያሉ ነገሮች በመሻሻላቸው የሚያገኙት የቢዝነስ ስኬት በጣም ውስን ነው። ተዘግተው የነበሩ የሚድያ ገበያዎች በሚከፈቱበትና ለውጥ/ ሪፎርም በሚያካሂዱበት ግዜ እንኳን ቢሆን በጥሩ መልክ ከተዘጋጀ የቢዝነስ ንድፍ ጋር የተቆራኘ ጠንካራ የውስጥ አስተዳደር የሌላቸው የሚድያ ተቋማት ከፍተኛ ደረጃ መድረስ አይችሉም። ለዚህም መጀመሪያውኑ ለቦታው ብቁ ሃላፊ መሸም ነው መፍትሔው።

ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡት ሃሳቦችም ቀጣይነትን ያረጋገጡና የቢዝነስ ንድፋቸውን እንዲሁም አሰራራችውን ያጋሩ የሚድያ ተቋማትን ተሞክሮ ይፈትሻሉ።

የስራ ሞዴሎች አራት አስፈላጊ ግብዓቶች:

  • የገቢ ምንጮች፡ የመገናኛ ብዙሃን ከሥራ ገቢ የሚያመነጩባቸው የተለያዩ መንገዶች
  • የወጪ መዋቅር: የመገናኛ ብዙሃን በሥራ ጊዜ የሚያወጧቸው ወጪዎች
  • ቁልፍ ግብዓቶች: የስራ ሞዴልን በተሳካ ሁኔታ ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልጉ ጠቃሚ ግብዓቶች
  • ቁልፍ ተግባራት: ሐሳባዊ ዕሴቶችን ለመተግበር የሚያስፈልጉ በጣም ጠቃሚ ተግባራት

1.ከህዝብ የሚሰበሰብ እና አባልነት፡

በገንዘብ ረገድ ስኬታማ መሆን የቻሉ መጠነ ሰፊ የምርመራ ዘገባ የሚያዘጋጁ የዜና ሚድያ ምሳሌዎች ግን አልጠፉም።በገቢ ማሰባሰቢያ በተገኘ 1ሚሊየን ፓውንድ እ.ኤ.አ 2013 የተመሰረተው አምስተርዳም የሚገኘው ደ ኮረስፖንደንት (ዲሲ) የአባልነት ክፍያዎችን ብቻ በማስከፈል በርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ዘገባ የሚቀርብበት ከማስታወቂያ የጸዳ መድረክ መፍጠር ችሏል።

በማስታወቂያ የሚገኝ ነዋይን ከማሳደድ ይልቅ ይህ ተቋም በመፈለግ ላይ ያለው ከተለመደው የየዕለቱ የዜና መንገድ አዲስ አካሂድን በመፍጠር አባላቱ በዙሪያቸው ያለውን የዓለም ሁኔታ በተሻለ መንገድ የሚረዱበትን ሁኔታ ነው። ለተደራሽ ታዳሚዎች አዳዲስ ሰበር ዜናዎችን እና ትኩረት የሚስቡ ዜናዎችን ከመጋት ይልቅ ዲሲ ከዚህበተቃራኒ ድጎማዎችን በማድረግ ብዙም ሽፋን የማይሰጣቸው ነገር ግን አንባቢዎቹን የሚያስደስቱ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የምርመራ ዘገባ ይሰራል። ዲሲ የቢዝነስ ሞዴሉን የነደፈው በመተማመን ላይ ሲሆን የንድፉም ዙሪያ ገባ ይህንን መተማመን ከግምት በማስገባት የተሰራ ነው። አንባቢዎችን እንደ ባለሞያ የመረጃ ምንጭነት ከማነሳሳት ጀምሮ የገንዘብ አቋሙን ሙሉ ለሙሉ ግልጽ አድርጎ እስከማሳየት ይህን ተዓማኒነት በየአንዳንዷ ነጥብ ላይ አስቀምጧል። የተቋሙ የአባልነት አሰራርም የዚህ መተማመን መሰረት በመሆኑ ወደ 4.5 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር የሚጠጋ ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢን ማስገኘት የቻሉ 60,000 አባላትን እንዳፈሩለት ተቋሙ ይናገራል።

በማዘጋጀት ወቅት ድርሻ እንዲኖራቸው በማድረግ፣ የታተሙ ጉዳዮች ላይ የሚኖሩ ውይይቶች ላይ እንዲወያዩ በማድረግ እንዲሁም ተቋሙን እንዲለግሱ በማድረግ አባላቱን በተለያየ መንገድ ያሳትፋል።ተቋሙ በኢንተርኔት ከደንበኞቹ ጋር መስተጋብር የሚፈጥርበት መንገድም ወሳኝ ሃብቱ ነው። ከተጠቃሚዎች ጋር መስተጋብር መፍጠር የሚያስችሉ ቁልፍ የሆኑ ሞያዊ ክህሎቶች ከቋሚ ክትትል (ሞኒተሪንግ) እና ቴክኒካዊ ድጋፍ ጋር በጣም አስፈላጊ ነገሮች ናቸው።

2.በማሌዥያ የይዘት ባዶነትን መሙላት: BFM Business Radio

በተለያዩ የገበያ ውድድሮች እንደታየው በማደግ/በመለወጥ ላይ ላሉ ጣቢያዎች ራሱ የራድዮ ቢዝነስ ንድፍ እንዲያድጉ የሚያስችል ነው። የሃገር ውስጥ ራድዮ ጥሩ ቢዝነስ ሊሆን ይችላል በዛ ላይ የመነሻና ማንቀሳቀሻ ወጪው አነስተኛ ነው፣ ብዙ ቦታ አያስፈልገውም፣ በአነስተኛ ገንዘብ ብዙ ሰዎች ጋር ለመድረስ የሚያስችል ነው በተለይም ደግሞ የዲጅታል ሚድያው ተጽዕኖ ባልደረሰባቸው ቦታዎች።የራድዮ ጣብያ ስኬት ማዕከሉን የሚያደርገው ከቁሳዊ ሃብት ይልቅ በሚቀጥራቸው ባለተሰጥዖ ባለሞያዎች፣ የማስታወቂያ ሽያጮችን በማዘጋጀት፣ አላስፈላጊ ወጪዎችን በመቀነስ እንዲሁም ኦሪጅናል በመሆን ነው።

ይህ እንዳለ ሆነ በተለያዩ በማደግ ላይ ባሉ ሃገሮች የሚገኙ የሃገር ውስጥ ራድዮዎች ብዙውን ግዜ ገደብ ወይም ቁጥጥር አለባቸው። ሶማሊላንድ የሚገኝ የግል ራድዮ በርዋንዳ የዘር ፍጭት በነበረው ሚና የተነሳ ታግዷል። ማይናማርን በመሳሰሉ ሃገራት መንግስት በዘርፉ ላይ የሚያደርገውን ቁጥጥር ቀጥሏል። እንዲህም ሆኖ መስራት በተቻለበት ሁኔታ ሁሉ በሚድያው ምህዳር ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ምንድነው አንድ ራድዮ ጣቢያን ስኬታማ የሚያደርገው? ማሌይዢያ የሚገኘው ቢ ኤፍ ኤምየተሰኘ የቢዝነስ ራድዮ ጣብያ የበላይ ሃላፊ የሆኑት ማሌክ አሊ እንደሚመልሱት ከሆነ በአንድ ገበያ ውስጥ የጎደለውን ይዘት የመለየት እና የመሙላት ጉዳይ (ኮንቴንት ቫከም) ነው።

የይዘት ባዶነት (ኮንቴንት ቫከም) የሚፈጠረው ገበያው ላይ ዝግጁ ሆኖ የቀረበ ይዘት ሳይኖር ሲቀር፣ ወይም በአንድ በተወሰነ ግዜ ወይንም በሚድያ ዘርፉ ላይ ለማግኘት የማይቻል ሲሆን ነው። ለምሳሌ በማሌይዢያ የንግድ ልውውጥ በጦፈበት ወቅት እንኳን የቢዝነስ ወሬዎችና ውይይቶች እንዲሁም ከቢዝነስ ጋር የተገናኙ ትምህርታዊ ይዘቶችን ለማግኘት አይቻልም ነበር።  በኩዋላ ለምፐር በንግድ ፈጠራ እና ቢዝነስ የተካኑ ኮምፒውተሮቹን በመጠቀም ቢዝነስ ተኮሩ የራድዮ ጣብያ ይህን የይዘት ባዶነት መሙላት የሚችልበት ከፍተኛ አቅም ነበረው። ቢ ኤፍ ኤምም ይህንን ዕድል ተጠቅሞበታል።

የራድዮ ገበያ እድገት ደረጃዎች

የይዘት ባዶነትን (ኮንቴንት ቫከም)ን በምናጠናበት ግዜ ገበያው ያለበትን የዕድገት ደረጃ መገንዘብ በጣም ጠቃሚ ነው። አሊ እንደለየው ከሆነ ሶስት ደረጃዎች አሉ እነሱም ያልተስተካከሉ፣ ዲሞግራፊን መሰረት በማድረግ የተስተካከሉ እና ፍላጎትን መሰረት በማድረግ የተስተካከሉ ናቸው። ቢ ኤፍ ኤም እ.ኤ.አ 2008 የ ማሌይዢያን ገበያ ሲቀላቀል ገበያው ሶስተኛው ደረጃ ላይ ነበር።

ኳላ ለምፐር ካልተስተካከለ ዲሞግራፊን መሰረት በማድረግ ወደተስተካከለ የራድዮ ከተማ የተሸጋገረችው እ.ኤ.አ 1995 ነበር። እነዚህ ደረጃዎች ቀጥሎ በቀረበው አስረጅ ምስል የተገለጹ ሲሆን ይህም የራድዮ ቢዝነስ ፈጠራዎች ምን አይነት ራድዮ ጣቢያዎችን መጀመር ወይንም ማሻሻል እንዳለባቸው ለመረዳት ይጠቅማል።

ራድዮ በቂ ባልሆነበት ሁኔታ እንደ አብዛኛዎቹ የመደበኛ ሚድያ አገልግሎቶች ሁሉ የታዳሚዎችን መከፋፈል እና ለዲጂታል ነገሮች ላይ የሚወጣው ወጪ በመጨመሩ ከራድዮ የሚገኙት ገቢዎችም ለመረዳት የሚያዳግቱ እየሆኑ መጥተዋል።እነዚህን ኪሳራዎች ለመቋቋምና የዕድገት አቅምን ለማሳደግ የሚድያ ተቋማት የተለያዩ ገቢዎችን ማስገኘት ወደሚችሉበት ደረጃ የሚያሸጋግራቸውን ንድፍ ለመፈለግ ተገድደዋል።ይህም በኢንተርኔት ላይም ከዛ ውጪም የሚካሄዱትን ገቢ የሚያስገቡ ስርጭቶችን ይጨምራል።

ማማ ኤፍ ኤም- ኡጋንዳ ውስጥ በኡጋንዳ የመገናኛ ብዙሃን ሴቶች ማህበር አማካኝነት እ.ኤ.አ በ2001 ተመስርቷል:: በፍላጎት ላይ የተቀረፀ ጣቢያ ሲሆን የይዘት አትኩሮቱንም በአካባቢው ባሉ ስኬታማ ሴቶች ላይ አድርጓል፡፡

ሁሙሩዛ ራዲዮ: የዛምቢያ ራዲዮ ሲሆን እ.ኤ.አ በ2015 ነበር የተመሰረተው፡፡ በስነ-ህዝብ ቅርፅ የተዋቀረ ወጣቶች ላይ የሚተኩር ራዲዮ ነው፡፡ ይዘቱም አብዛኛውን ጊዜ ወጣት ሰዎች ላይ ያነጣጥራል፡፡ በወጣቶች ጉዳይ ፣ ሐይማኖት ፣ ባህል ፣ መዝናኛ ፣ ትምህርት ፣ ጤና ፣ ቴክሎጂ እና ሙዚቃ ላይ ያሉ አሳታፊ ፕሮግራሞቹን አየር ላይ ያውላል፡፡

ክዊዘራ ራዲዮ ፡ በሰሜን ምዕራብ ታንዛኒያ እ.ኤ. አ በ1995 የተቋቋመ፡፡ ሰሜን ምስራቅ ታንዛኒያ ፣ የሩዋንዳን፣ ቡሩንዲ እና ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብክን ምስራቃዊ ክፍል የሚሸፍን ነው፡፡ ጣቢያው ሰዎችን ስለ ብዙ አጀንዳዎች መረጃ ሊያቀብል የተቋቋመ ነው፡፡ ዛሬ ላይ ጣቢያው ዜናዎችን እና የህብረተሰቡን አጠቃላይ ፍላጎቶች ጉዳይ ይሸፍናል፡፡

ከኢንተርኔት ውጪ የሚገኙ ገቢዎችንም ለማሳደግ ቢ ኤፍ ኤም ዝግጅቶችን የማስተዋወቅ ስራ መስራት የጀመረው ከዓመታት በፊት ነበር። አሁን ላይ ከአጠቃላይ ገቢው 10 በመቶ የሚሆነውን የሚያገኘው ከዚህ ዝግጅቶችን ከሚያስተዋውቅበት አሰራሩ ነው። ይህ ዕድገት ከገቢም በበለጠ ሶስት አይነት ጥቅም አለው የመጀመሪያው ዝግጅቱን ከሚያዘጋጁት ተቋማት ጋር የንግድ ስሙን ከፍ በማድረግእና ስፖንሰሮችን ስለሚያስገኝ ቢ ኤፍ ኤም ጥቅም እንዲጋራ ማስቻሉ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ቢ ኤፍ ኤም ጣቢያውን  ተጠቅሞ በአነስተኛ ወጪ ዝግጅቱን አየር ላይ ማዋል መቻሉ ነው። እንዲሁም በሶስተኛነት ዝግጅቱ የተሳካ በሆነ ቁጥር የ ቢ ኤፍ ኤምን ብራንድ/የንግድ ስም ገጽታ ስለሚያጠናክር አዳዲስ አድማጮችን ለራድዮ ጣብያው ጎብኚዎችን ደግሞ ለገጸ ድሩ ለማግኘት ይረዳዋል።

  1. በ ኤዲቶሪያል ረገድ የተሳካለት ዝግጅት ለስፖንሰርሺፕ፦ ዲ ቪ ቢ ቲቪ

የራሳቸውን ይዘት ለሚቀርጹ የራድዮና ቴሌቪዥን አዘጋጆች የፕሮግራም ስፖንሰርሺፕ ትልቁ ገቢ ማግኛቸው ነው። በመሆኑም ትክክለኛው ፕሮግራም/ዝግጅት በትክክለኛ ምክንያት ከተገቢው ስፖንሰር ጋር ከተጣመሩ የኤዲቶሪያል ግልጽነት የተጠበቀይሆናል።  ዴሞክራቲክ ቮይስ ኦፍ በርማ ወይም ዲ ቪ ቢ በመባል የሚታወቀው የማይንማር የግል ቴሌቪዥን ጣብያ ከንግድ ከሚያገኘው አጠቃላይ ገቢ 70 በመቶውን ከ ስፖንሰርሺፕ የሚያገኝ ሲሆን ይህም ተቋሙ በለጋሾች ላይ ከመንጠልጠል እራሱን ወደሚችልበት ቁመና እንዲቀየር አግዞታል።

ለምሳሌ እ.ኤ.አ 2017 ዲ ቪ ቢ ‘ሞደርን ፋርም’ በሚል ርዕስ በጀመረው ትምህርታዊ ፕሮግራም በንግድ ተቋማት ሙሉ በሙሉ የስፖንሰር ድጋፍ ያገኘው የመጀመሪያው ክፍል እንኳን አየር ላይ ሳይውል ነበር። የፕሮግራሙ ይዘትም ማዳበሪያን፣ የመስኖ ዘዴዎችን እና የተሰበሰበ ዘር ከፍ ያለ ዋጋ የሚያወጣበትን አይነት ርዕሶች የያዘ ነበር። ዝግጅቱን ስፖንሰር ማድረግ የሚችሉ አካላት ሲታሰቡ ዲ ቪ ቢ የመዳበሪያ አምራች ኩባንያዎችን ኢላማው ውስጥ የሚያስገባ ይመስል ነበር። ነግር ግን ይህ እንዴት ተደርጎ ይተገበራል? እያንዳንዱ ክፍል ሲያልቅ የስፖንሰሩን ማዳበሪያ ተጠቀሙ እያለ ሊመክር ነው? ዲ ቪ ቢ ከግምት ማስገባት የነበረበት በእንደዚህ አይነት አቀራረብ ላይ አንድ የንግድ ስም/ ብራንድ የሚኖረውን ተጽዕኖ ነበር እና ማዳበሪያ መጠቀም ከግዜ ብዛት የሚያመጣውን ችግር፣ የውሃ ብክለትን ሊያስከትል መቻሉን ወይም እንስሳትና ሰዎች ላይ ሊፈጠር የሚችለውን የተቃረነ ተጽዕኖ ሊያስብበት ተገድዶ ነበር። ከይዘቱ አንጻር የማዳበርያ ኩባንያ ፕሮግራሙን ቢደግፈው በፍጹም የሚያስኬድ ሃሳብ ይመስላል ነገር ግን ከታዳሚው አንጻር ይህ አካሄድ የዝግጅቱን ኤዲቶሪያል ሃቀኝነት ወይም ተቀባይነት ጥያቄ ውስጥ የሚከተው ይሆን ነበር። በምትኩም የሽያጭ ቡድኑ የፕሮግራሙን ማህበራዊ ተልዕኮ እና ታዳሚው የሚሰጠውን ዋጋ የመሸጫ ነጥብ በማድረግ ሌሎች አይነት ስፖንሰሮችን ፈለገ። “አርሶ አደሮች ነገሮችን እንዴት በተሻለ መንገድ መስራት እንደሚችሉ በማስተማር ቤተሰቦቻቸውን በተሻለ መንገድ እንዲደግፉ ማስቻል” የሚለው ሃሳብ የዝግጅቱ ቋሚ ጭብጥ ሆነ። የንግድ ተቋማትም ይዘቱ ውስጥ ተጽዕኖ ሳያሳድሩ ዶላሮቻቸውን ዝግጅቱ ላይ ለማፍሰስ ተነሳሱ። የፕሮግራሙ ተልዕኮም የሽያጭ ቡድኑ ምን አይነት ስፖንሰር መፈለግ እንዳለበት አመላካች በመሆኑ የማይክሮፋይናንስ ተቋማት፣ የስፖርት መጠጦች እና የሶላር መብራቶች ጋር ሄደ።

የሶማሊላንድ ምሳሌ

ስፖንሰርሺፕ ፕሮፖዛልን ለማቅረብ ፣ ለማስተካከል እና ለማስተዳደር ደህና አርትዖታዊ የአቀራረብ ሂደት መመስረት አስፈላጊ ነው፡፡ በሶማሊላንድ አንድ የቴሌቪዥን አሰራጪ በአካባቢያዊ ቸርቻሪዎች ዘንድ ጥሩ ገበያን ስለማግኘት የሚሰራን ሳምንታዊ ፕሮግራም ስለማዘጋጀት ሲያስብ ስለ እነዚህ ነገሮች በጥንቃቄ አስቧል፡፡ ዋነኛው ፅንሰ-ሀሳብ በምሽት በከተማ ዙሪያ እየዞሩ የሚጫወቱ ፣ የሚቀልዱ ፣ እና በዋጋ ላይ የሚከራከሩ  ወጣት ፣ ጎበዝ ፕሮግራም አስተናጋጆችን አሳትፏል፡፡ ሆኖም ግን የሚታወቁት ስፖንሰሮች ከተወሰኑ ተጠያቂነቶች ጋር መምጣት ጀመሩ፡፡

በእርግጥም አንዳንዱ ሱቆች ሥራዎቻቸውን የሚያሳትፉ ክፍሎችን ስፖንሰር ለማድረግ ፈቃደኛ ይሆናሉ፡፡ የአርትዖት አደጋ ሊሆን የሚችለው የፕሮግራሙ ይዘት ወገንተኛ መሆኑን እና ምናልባትም ትክክለኛ መረጃ ላለመሆኑ በተለይም ሥራው በተሻለው አቅሙ አገልግሎት እንደማይሰጥ የሚኖር ግምት ነው፡፡ ይህም የፕሮግራሙን ተልዕኮ ፣ የአድማጭ ተመልካቹን ህጋዊነት እና አርትዖታዊ ታማኝነትን ያዳክመዋል፡፡

ይልቁንም የሽያጭ ቡድኑ ሌሎች ተስፋ ያላቸውን ስፖንሰሮችን ፡ በምሽት ለመዝናናት ለሚወጡ ወጣቶች ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የታክሲ መተግበሪያዎች እና የመዝናናቱ ክፍል የሚሆኑ ምግብ ቤቶችን ለይቶ አስቀምጧል፡፡

አንዴ ስፖንሰሮች ከተለዩ በኋላ ፈጠራ በተሞላበት መንገድ ስፖንሰሮቹን ፕሮግራሞቹ ውስጥ ማካተት ወሳኝ ነበር ይህም ስክሪፕቶቹን ለመጻፍ አንዳች ብዕር ማንሳት ሳያስፈልጋቸው የሚስብ እይታ ውስጥ እንዲገቡ አስችሏል።

የገቢ ምንጭ / ፋይናንሲንግ

የፕሮግራም ስፖንሰርሺፕ ለማግኘት የተለያዩ አካሄዶች ያሉ ቢሆንም ለአዘጋጁም ለስፖንሰር አድራጊው አካልም ጥሩ የሚሆነው ግን አንድ ሙሉ ሲዝን የሚተላለፉ ክፍሎችን መወሰን ነው።

ይህም የሚሆነው ለምሳሌ በሳምንት አንድ ክፍል እየተላለፈ ለስድስት ወራት የሚቆይ በጥቅሉ 24 ክፍሎች ያሉት። ለአዘጋጆቹ ይህ ወጪያቸውን የሚታወቅ ያደርግላቸዋል። ለስፖንሰር አድራጊዎቹ ደግሞ የሽያጭና የፕሮዳክሽን ቡድኖቻቸው ምርታቸው የሚተዋወቅበትን ቦታ፣ የንግድ ስማቸው በበለጠ እይታ ውስጥ የሚገባበትን እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ነገሮች በፕሮግራሙ የመካተታቸውን ነገር በመለየት ለስፖንሰር አድራጊው የሚኖረውን ዋጋ ጥንቅቅ አድርገው እንዲያቀርቡ ያስችላል። ሙሉ ሲዝን ስፖንሰር ማድረግ የቴሌቭዥን ጣብያው ስፖንሰሩን ከፕሮግራሙ ጋር አድርጎ ሲዝኑ ሲጀምር እና ሲያልቅ እየመላለሰ ለማስተዋወቅ ያስችለዋል። እንዲሁም ስፖንሰርነቱ በ ዩቲዩብና መሰል ዲጂታል መንገዶች ሲዝኑ ከማለቁም ቀደም ብሎ በተደጋጋሚ ለማሳየት ያስችላል።

ኦቨር ዘ ቶፕ እና አይ ፒ ቲቪ ስርጭቶች በአፍሪካ

የሞባይል ስርጭት እና የኢንተርኔት መሰረተ ልማቶች በአፍሪካ እየተስፋፉ እንደመምጣታቸው ኦቨር ዘ ቶፕ (ኦ ቲ ቲ) ወይም ኢንተርኔት ፕሮቶኮል ቲቪ (አይ ፒ ቲቪ) የቢዝነስ ንድፎች አዋጭ መንገዶች እየሆኑ እየመጡ ናቸው።  የ አይ ፒ ቲቪ አገልግሎቶች ከ የሳተላይት ወይም የገመድ (ኬብል) አገልግሎት ይልቅ ስርጭቶች በኢንተርኔት የሚደርሱባቸው ናቸው። ተጠቃሚዎችንም እንደነ ኔትፍሊክስ ያሉ አገልግሎቶችን ለመጠቀም በመምረጥ ወይም ሰብስክራይብ በማድረግ የቀጥታ ስርጭቶችን ወይም የመረጡትን ፕሮግራም በፈለጉት ግዜ እንዲመለከቱ ያስችላይል።  እ.ኤ.አ ከ2010 እስከ 2017 ከሰሃራ በታች ባሉ ሃገራት የሚገኙ የ ኦ ቲ ቲ ስርጭት ተጠቃሚ ቤተሰቦች ብዛት የ21.8 በመቶ ጥምር አማካይ እድገት ሲያሳይ የመደበና ቴሌቪዥን ተጠቃሚ ቤተሰቦች ብዛት ግን የ 3.6 በመቶ ጥምር አማካይ እድገት ብቻ ነበረው።  የብሮድካስት ፈቃድ ለማውጣት የሚያግዱ ፖሊሲዎች በበዙባቸው አንዳንድ ሃገራት የቴሌቪዥን ቢዝነሱን መቀላቀል ለሚፈልጉ ኦ ቲ ቲ የተሻለ አማራጭ የሚሆንበት ግዜም አለ።  በሌሎች ሁኔታዎች ደግሞ ኦ ቲ ቲ እና አይ ፒ ቲ ቪ አሁን ላሉ ማሰራጫዎች አዲስ የቢዝነስ ማስፋፍያ አቅጣጫ ሊሆን ይችላል። በሁለቱም ሁኔታዎች ቢሆን ግን የተንቀሳቃሽ ምስል / ቪድዮ ይዘት እና የዝግጅቱ የፕሮዳክሽንአቅም ለአንድ የሚድያ ተቋም ዋጋ የማይገኝላቸው የመወዳደሪያ ነጥቦች ናቸው።

እነዚህ አካሄዶች እየተጠናከሩ ሲሄዱ ፕሮግራሞች  ገንዘብ የማግኛ መንገዶችን ያማከሉ እየሆኑ ይሄዳሉ። እንደ ጅማሮው ግን እኚህ አዳዲስ የ አፍሪካ ኦ ቲ ቲ ተቋማት ቢዝነሳቸው ቀጣይነት እንዲኖረው የሚያደርጉት በቀጥታ ከማስታወቂያ የሚገኙ ገቢዎችን በሚያረጋግጡ ስምምነቶች ነው። ይህም ማለት እንደ ዲ ቢ ቪላይ የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው በፕሮግራም ስፖንሰሮች የማስታወቂያ ገቢን መፍጠር የሚያስችል አካሄድ መንደፍ ::

  1. ዋናውን እንደገና መገንባት ፣ አዲስ ሞዴል መፍጠር፡ ዴዘርት ኒውስ

ብዙ የአፍሪካ ጋዜጣ አሳታሚዎች በሌሎች የዓለም ክፍሎች ከሚሠሩ አቻዎቻቸው ጋር በተመሳሳይ የእርስ በርስ ግጭት ያጋጥማቸዋል፡፡ ትርፍ እያሽቆለቆለ ነው ፣ ከፍተኛ ገንዘብ አመንጪዎች ፈተና ገጥሟቸዋል ፣ አድማጭ ተመልካቾች ደግሞ ወደ አዲስ መድረኮች እየፈለሱ ባለበት ጊዜ አታሚዎች በዲጂታል ስራዎ ላይ ፈሰስ ማድረግ አለባቸው፡፡ የትርፍ ግቦች ህልውናን በማስጠበቅ ግቦች ብቻ ሊተኩ ይችላሉ፡፡ ታዳሚዎች ወደ ኦንላይን በሚፈልሱበት ጊዜ የዜና ድረ ገፅን መጨመር ተፈጥሮአዊ እድገት ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን በቂ ነውን? የዲጂታል ሳንቲሞች የህትመት ብሮችን ይቀይራሉን? ብዙ ድርጅቶች በቂ አይደለም ወይም አይቀይሩም የሚሉ መልሶችን ነው ያገኙት፡፡ ወደ አዲስ መድረክ የሚደረግ ስልታዊ ሽግግር የጋዜጦችን መረጃ ምንጮች፣ እንቅስቃሴዎች ፣ እሴት ፈጠራ ፣ የወጪ መዋቅር እና የገቢ ምንጮችን እንደ አዲስ መፍጠርን ይጠይቃል፡፡

የሁለትዮሽ ለውጥ

እ.ኤ.አ በ2010 ደዘርት ኒውስ Deseret News (Salt Lake City, Utah, USA) ወደ ከፍተኛ ስኬት ያለው የህትመት እና የዲጂታል ቢዝነስ እየተቀየረ ነበር፡፡ ለውጡ በእርግጥም “የሁለትዮሽ ለውጥ” ነበር፡፡ ምን ማለት ነው? እንደ ሃርቫርድ የቢዝነስ ትምህርት ቤት ፕረፌሰር ክላርክ ጊልበርት ገለፃ የቢዝነስ ሞዴሎችን በተሳካ ሁኔታ ለማሻሻል ሁለት አይነት የለውጥ አይነቶች አሉ፡፡

ለውጥ 1፡ ዋናው ቢዝነስ በማስተካከል እና አሁን ያለውን የቢዝነስ ሞዴል ከተዘበራረቀው የገበያ ሁኔታ ጋር ያለማምደዋል

ለውጥ 2፡ ለወደፊቱ ተቀዳሚ የገቢ ማመንጫዎች የሚሆኑ አዲስ የፈጠራ ዘዴዎችን ለመፍጠር የተለየ የራሱን ድርጅት ይፈጥራል፡፡

ሁለቱንም ለውጦች የተሳኩ ለማድረግ ሌላ ሶስተኛ ነገር ያስፈልጋል፡፡ ከሁለቱ ድርጅቶች ጋር የሚያገናኝ አወቃቀር እና ሂደትን መገንባት እና የጠንካራ ጎኖችን እንዲሁም የሀብት እና አቅም መጋራት ያመቻቻል፡፡ ይህንን ነው ጊልበርት “የችሎታዎች ልውውጥ” ብሎ የሚጠራው፡፡ የችሎታዎች ልውውት ሁለት የተለያዩ ድርጅቶች

በአንድነት እንዲኖሩ ከማረጋገጥም ባለፈ የዱሮውን የቆየ ድርጅት በተለመዱ ተፎካካሪዎቹ ላይ አብላጫነት የሚሰጠው ሲሆን አዲሱን ያልተረጋጋ ቢዝነስ ደግሞ በሌሎች በጥንካሬ አነስ ያሉ ጀማሪዎች ላይ የበላይነት እንዲኖረው ያደርጋል፡፡

ማጠቃለያና የወደፊት ርምጃ

የምርመራ እና የረጅም ጊዜ ጋዜጠንነት እያንሰራራ ይገኛል፡፡ እንዲያውም እየጨመረ ለሚሄደው የአባልነት እና የደመወዝ ስራ ሞዴሎች ምርጡ ቅርፅ ሊሆን ይችላል፡፡ ማስጠንቀቂያው ተዓማኒነት ነው፡፡ እንደ የመገናኛ ብዙሃን ባለቤትነት ወይም ሥራ አስኪያጅነት ተዓማኒነትን መገንባት የአመራሩ ኃላፊነት ሲሆን በጥብቅ የመደበኛ/ የደረጃ አሰራር ሁኔታዎች እና በአርትዖት ፖሊሲዎች ሊደገፍ ይገባዋል፡፡ ተዓማኒነት የመገናኛ ብዙሃን በሚሳተፉባቸው ስራዎች ሁሉ በተለይም የአባልነት ሥራ ሞዴል ለመፍጠር ለሚፈልጉት የእንቅስቃሴአቸው ሁሉ ማዕከል ነው፡፡

የሬዲዮ ሥራ – በተለይም የባህላዊ ሬዲዮ ስርጭቶች በአፍሪካ እና በሌሎች የዓለም ክፍሎች አስፈላጊነታቸው እንደቀጠለ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ተጠቃሚዎች በተከፋፈሉ እና በተለያዩ ቁጥር የተለያዩ ዘላቂ የገቢ ሞዴሎች አስፈላጊ ናቸው፡፡ ከነዚህም መካከል አንዳንዶቹ የብሔራዊ አስተዋዋቂዎችን ለመሳብ ስፋት ላለው ታዳሚ በኦንላይን ማሰራጨትን ፣ ዕለታዊ ልዩ ፕሮግራሞችን ለኦንላይን ስርጭት እና ለገንዘብ ማግኛ ቪዲዮ መቅረፅን ፣ ለስራ – ተጠቃሚ ምዝገባ ክፍያ ወይም የከስራ- ለስራ የፈቃድ ጥምረቶችን ፣ እንዲሁም ወደ ዝግጅት ማዘጋጀት ማደግን ያካትታሉ፡፡

በሁለቱም ፣ በተለመደውም ሆነ በኦንላይን ስርጭት (በIPTV or OTT) በፕሮግራም ስፖንሰርሺፕ አማካኝነት የማስታወቂያ ገንዘብ የማግኘት ትልቅ ዕድል አለ፡፡ በአርትዖት ፅኑ ጥብቅነት ይህን ማድረግ ቀጥተኛና የአጭር ጊዜ መንገድ አይደለም፡፡ ነገር ግን ለአሰራጮች እና ለስፖንሰር አድራጊዎች ትልቅ ድል ይሆንላቸዋል፡፡ ከሁሉም የተሻለው መንገድ ይዘትን እና የስፖንሰርሺፕ አቀራረብን በጋራ ለማዳበር ቀጥታ ሽያጭ ፣ የፕሮግራም ስፖንሰሮችን እና አስተዳደርን ያካትታል፡፡ ይህም ትክክለኛ ስፖንሰሮች ተልዕኮን መሰረት ባደረገ አቀራረብ ዒላማ መደረጋቸውን ያረጋግጣል፡፡

የሚስብ እና ተፈጥሮአዊ የፕሮግራም ተደራሽነትን ለስፖንሰሮች ይፈጥራል ፤ ጥሩ የአርትዖት ፖሊሲዎችም ፀድቀዋል፡፡  ይህን አይነት በትብብር የሚሰሩ የሥራ ሂደቶችን ማዘጋጀት ቁልፍ ነው፡፡

ወደ ዲጂታል-መር ድርጅት ወይም ሌላ ዓይነት የሚረብሹ የመገናኛ ዘዴዎች መቀየር ከአዲስ የሥራ ክፍል ወይም መምሪያ በላይ ይወስዳል፡፡ አዲስ ስራን ለመጀመር ሌላ የተለየ ድርጅት ያስፈልገዋል፡፡ በተጨማሪም የቀድሞውን የመገናኛ ብዙሃን ሥራ ወደ አዲስነት ቀይሮ ለመገንባት ትኩረት ያስፈልገዋል፡፡ይህ የሁለትዮሽ ሽግግር ዘላቂነትን ለማረጋገጥ የተሻለው አቀራረብ ነው፡፡ ሆኖም ግን ይህንን በትክክል ለማሳካት አስቸጋሪ ውሳኔዎችን ፣ ጠንካራ አመራር እና በሁለቱ ድርጅቶች መካከል የጋራ ጥቅምን ለማጎልበት አዳዲስ ሂደቶችን ያቀርባል፡፡ በመጨረሻም ከተሳካ ሁለቱ ድርጅቶች የመገናኛ ብዙሃ የስራ ሞዴሎቻቸውን እንደ አዲስ አድሰው ለወደፊት ዕድገት ያመቻቹታል፡፡

“ከማሽከርከር በፊት ትክክለኛ ሰዎችን በአውቶቡስ ውስጥ ማስገባት እና ትክክለኛ ቦታቸውን መስጠት ወሳኝ ነው” ጂም ኮሊንስ

በላይኛው አባባል “አውቶቡሱ” የተባሉት የመገናኛ ብዙሃን ቤቶች ሲሆኑ “አሽከርካሪዎቹ” ደግሞ የአመራር ቡድኑ ነው፡፡ ጠንካራ አመራርን መገንባት የመገናኛ ብዙሃን ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ የውስጥ ስልቶችን ማዘጋጀት እና የሥራ ሞዴሎችን እንደ አዲስ ማዋቀር ቀላል ስራ አይደለም፡፡ የሥራ ለውጥ ማሻሻያን በምናስብበት ጊዜ ባለቤቶች በመጀመሪያ የአስተዳደር ባለሙያዎችን እና ጠንካራ የቴክኒካዊ ዕውቀት ያላቸው ባለሞያዎችን መቅጠር አለባቸው፡፡ “ምን መደረግ አለበት” የሚለውን ለመወሰን ከፍተኛ መሪዎችን እንዲሁም “እንዴት ይተግበር” የሚለው ውሳኔ ላይ እንዲያግዙ መካከለና ስራ አስኪያጆችን መቅጠር ቁልፍ ነው፡፡

የአሰራር ልህቀት የስልት አስፈላጊ ክፍል ነው፡፡ ለመገናኛ ብዙሃን 24/7  የዜና ማእከላት ውስጥ ስራ ላይ ማሳለፍ እና ዕለታዊ የስራ ክንዋኔ መስፈ ርቶችን ማሟላት ዘወትር አፈፃፀምን በከፍተኛ ደረጃ ለማስኬድ ፈተናዎችን ይፈጥራሉ፡፡ እነዚህም ዘገባን ፣ ኤዲቲንግን ፣ ፕሮዳክሽን ፣ ስርጭት ፣ ሽያጭ እና ቁጥራቸው እየጨመረ ያለ ቴክኖሎጂ ተኮር ሥራዎችን ያካትታል፡፡ ለእያንዳንዱ ክንዋኔ ውጤታማነት እያንዳንዱን ሥራ በየቀኑ ለማስተዳደር በተገቢው ደረጃ ያሉ ሰዎችን ፣ ሂደቶችና ፖሊሲዎችን በቦታው ማስቀመጥ አስፈላጊ ነው አስፈላጊ ናቸው፡፡ በተጨማሪም ተገቢ መስፈርቶች አሠራሮችን ለመለካት እና ለመለየት ቁልፍ ናቸው፡፡ አፈፃፀም ላይ የሚደረጉ ማሻሻያዎች ፈጣን እና አጭር እድሜ ያላቸውን ውጤቶች ያስገኛሉ፡፡ በብዙ አጋጣሚዎች የመገናኛ ብዙሃን ፈጠራን በተቀላጠፈ ሁኔታ ማከናወን የሚችሉበት እና ፈጣንና ዘላቂነት ያለው ዘመናዊ አሰራርን ለመከታተል የሚያስችሉ ፈጣን መንገዶች ሊኖራቸው ይችላል፡፡

REFERENCES

i Osterwalder, 2010, Business Model Generation: A Handbook for Visionaries, Game Changers, and Challengers

ii Dugmore, 2018, Paying the Piper: The sustain-

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *