ሰላም ሙሴ እና ቤተልሔም ነጋሽ ሴቶች ፣ የተለያዩ የብሔር እና ቋንቋ ቡድኖች እንዲሁም አካል ጉዳተኞች በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ውስጥ እንዲወከሉ መከራከሪያዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡

ውክልና/መወከል ምን ማለት ነው?

ውክልና/መወከል ማለት

1) ቀድሞ የነበረን ነገር እንደገና ማቅረብ ሲሆን

2) ለአንድ እሳቤ ወይም ነገር ወክሎ መቆም (Richardson and Wearn-ing, 2016)

አስፈላጊነቱ ለምን?

ውክልና ያለው ወይም የነበረው ነገር ቀጥተኛ ነፀብራቅ ሳይሆኑ ነገር ግን ብዙ ጊዜ በባለታሪኩ እና በአድማጩ መካከል ያለውን የመልዕክት ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ የሚያበላሽ ፖለቲካ እና በተፅዕኖ ፈጣሪ እሳቤዎች ስር የሆነ ማለት ነው፡፡ ስለሆነም እንደ ጾታ ፣ ብሔር እና አካል ጉዳተኞች ያሉ የተለያዩ ማንነቶች በመገናኛ ብዙሃንና በጋዜጣዎች መወከላቸው ለተገፉ እና በበጎ መልኩ ላልተወከሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተስፈኛ እሴቶችን እና አወንታዊ ገፅታዎን ለማመቻቸት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን የተለያዩ ድምፆች የሚሰሙበት ዲሞክራሲያዊ ባህል እንዲኖር አስፈላጊ ናቸው፡፡

ሥርዓተ-ፆታ

ምህረት አስቻለው ፡ የቀድሞ ሪፖርተር ጋዜጣ አርታዒ እና የቢቢሲ የአፍሪካ ቀንድ ቢሮ የአማርኛ ፕሮግራሞች አዘጋጅ በፆታ ምክንያት መገለል ማለት ምን ማለት እንደሆነ በደንብ ታውቃለች፡፡ ምንም እንኳን በስራዋ በውሳኔ አሰጣጥ ላይ ብትሳተፍም ሴቶችን በተመለከተ ከተለመደው እሳቤ ወጣ ያሉ ዘገባዎችን መስራት ላይ ግን ሁልጊዜም ቢሆን ፈተና ያጋጥማታል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ይሔ ፈተና ጉዳዩን በደንብ ካለመረዳት ሲመጣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሴት ስለሆነች ብቻ እንደዚህ አይነት ሴታዊ አጀንዳዎችን ብቻ እንደምትመርጥ ያለው ያልተስተካከለ አመለካከት ነው፡፡

የሴቶችን ጉዳይ በመሸፈን ረገድ መገናኛ ብዙሃን የተወሰኑ መሻሻሎችን እያሳዩ እንደሆነ ብትቀበልም የሴቶች ውክልና ግን አሁንም ዝቅተኛ ነው ፤ የሴቶች ጉዳይም በቂ ሽፋን የለውም፡፡ የመገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች አልፎ አልፎ እና ወቅታዊ ከመሆናቸው ባሻገር ህብረተሰቡ ለሴቶች ያለውን ማህበራዊ አመለካከት ለመለወጥ ምንም ዓይነት ጥልቀት እንደሌላቸው ታምናለች፡፡ ምህረት “በመገናኛ ብዙሃን ውስጥ ሁልጊዜም ቢሆን የዜና እና ትንተና ባለሞያዎች ወንዶች ናቸው፡፡” ትላለች፡፡  ሌሎች ብዙ ሴቶች ጋዜጠኞች የምህረትን ዕይታዎች ይጋሩታል፡፡  በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፆታ ጥናት ማዕከል በእንጉዳይ አለማየሁ የተጠናቀረ ሴቶች እና መገናኛ ብዙሃን የሚል መጠይቅ ሴቶች በመገናኛ ብዙሃን ሥራዎች ላይ በተለይም በውሳኔ ሰጪነት ያላቸው ተሳትፎ አሁንም ዝቅተኛ መሆኑን በግኝቱ ውስት,ጥ አካትቷል፡፡ የኢትዮጵያ ጋዜጠኝነት አድማስ በ30 በመቶ የሴቶች የዜና ክፍል ተሳትፎ ብቻ በወንዶች ቁጥጥር ስር ነው፡፡  ይህም የኢትዮጵያን የዜና ክፍል አድማስ በዓለም ላይ ከሚገኙ የፆታ እኩልነት ከሌለባቸው መገናኛ ብዙሃን ውስጥ አንዱ ያደርገዋል፡፡ በዋና ዋና የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ድርጅቶች ውስጥ በቅጥርም ሆነ በሥራ እድገት ላይ ምንም አይነት አነስተኛ የሴቶች ተሳትፎ ኮታ የለም፡፡

ለምሳሌ በትልቁ እና ብሔራዊው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮረፖሬሽን (EBC) 5 ከፍተኛ የአመራር ቦታዎች ላይ አንዲት ሴት ብቻ ትገኛለች፡፡  በኢቢሲ በዳይሬክተርነት ደረጃ 3 ሶቴች ይገኛሉ (በሴቶች ፣ ጠቅላላ አገልግሎት እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክፍል ሃላፊ)፡፡ በኮርፖሬሽኑ ከሚገኙ 149 ከፍተኛ አርታዒያን እና አዘጋጆች ውስጥ 22ቱ ብቻ ሴቶች ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ 82% የሚሆኑት በዝቅተኛ የአመራር ደረጃ (የቡድን መሪነት) ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያ ፕሬስ ኤጀንሲ ደግሞ በከፍተኛ አመራርም ሆነ በዳይሬክተርነት ደረጃ ምንም አይነት ሴቶች አይገኙም፡፡ ሁለቱም ድርጅቶች በመገናኛ ብዙሃን ያለውን ፆታዊ እኩልነት በተመለከተ ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡

በሁለቱም ፡ በኢቢሲም ሆነ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ወንዶች ጠንካራ የሚባሉ ጉዳዮችን ማለትም ፖለቲካ ፣ ኢኮኖሚ እንዲሁም ሳይንስ እና ቴክኖሎጂን ሲሸፍኑ ሴቶች ግን ዝቅተኛ ግምት የሚሰጣቸውን የሴቶች ጉዳይ ፣ የህይወት ዘይቤ ፣ ባህል ፣ ጥበብ እና መዝናኛ ጉዳዮችን ይዘግባሉ፡፡

ጾታ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን የሚሰጠው ዕይታ በብዙ መንገዶች የተዛባ ነው፡፡ ከቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማዎች ፣ የመፅሔት ፕሮግራሞች ጀምሮ እስከ ማስታወቂያዎች እና ሙዚቃ ድረስ ተፅዕኖ ያላቸው መገናኛ ብዙሃን ሴቶችን እንደ መጥፎ ገፀባህሪይ ነው የሚስሏቸው፡፡ ወንዶች ጠንካራ መሪዎች ፣ ቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ፣ ውሳኔ ሰጪዎች እና ከችግር አውጪዎች ተደርገው ሲሳሉ በአንፃሩ ደግሞ ሴቶች ወደ ወንዶች መደሰቻነት ብቻ ወርደው ፣ ደካማ ተጎጂዎች እና የቤት ውስጥ ሥራ ሰሪዎች ተደርገው ይሳላሉ፡፡

በኤፍ ኤም ራዲዮዎችም ሆነ በሳተላይት ቴሌቪዥኖች ላይ የሚተላለፉ የመዝናኛ ፕሮግራሞች በጣም የከፉ ተጋፊዎች ናቸው፡፡ ሴቶች በማህበረሰቡ ውስጥ ያላቸው ደረጃ እየተሻሻለ ቢመጣም የቴሌቪዥን ድራማዎች ፣ አስቂኝ ተከታታይ ፊልሞች እንዲሁም የአማርኛ ፊልሞችን ጨምሮ ሴቶችን በአሉታዊ እና ክብር በሚነካ መልኩ መወከላቸውን ቀጥለዋል፡፡

በአብዛኛው የቴሌቪዥን ማስታወቂያዎች በኅብረተሰቡ ውስጥ የተገነቡ የሴቶችን ሚናዎች ማጠናከር ሴቶችን ልጆችን እና ባሎቻቸውን በመንከባከብ ሥራቸው ብቻ በባህላዊው መቼት ያቀርቧቸዋል፡፡ ሴቶች ብዙ ጊዜ በ ዳይፐር ፣ የህፃናት ምግብ ፣ ፓስታ ፣ ዘይት ፣ የፅዳት እና የማዕድ ቤት እቃዎች ላይ የሚሰሩ

ማስታወቂያዎች ላይ ሲታዩ (ጥቂቶች ይህንን ለመቀየር ይሞክራሉ) ወንዶች ገን በሱፍ ሽክ ብለው በባንክ ፣ የገንዘብ ነክ ሐዋላ አገልግሎት ፣ የህንፃ መሳሪያ ፣ ኢንሹራንስ ፣ ብዙ ጊዜ የሚያምር ሆቴል እና የግንባታ ቦታዎች ላይ የሚሰሩ ማስታወቂያዎች ላይ ይሳተፋሉ፡፡

በኤፍ ኤም ራዲዮ እና ሳተላይት ቴሌቪዥኖች ላይ ሙዚቃ 70% የዓየር ሰዓቱን ይሸፍናል፡፡ በ 2007 በፅዮን ዮሐንስ ‘ Gender Issues and Women’s Portrayal in Secular Amharic Songs Produced in Cassettes’ በሚል ርዕስ የተሰራው ጥናት የሴቶችን ባህሪይ በሙዚቃዎቻችን ላይ እንደ ተዓማኒ ፣ በራሳቸው መቆም የሚችሉ ፣ ባለ ርጋታ እና ምቹ ሳይሆን እንደ ጥገኛ ፣ የማይታመን ፣ ተገቢ ያልሆነ ፣ ብቃት የሌላቸው ፣ ጨካኝ ፣ ግድ የለሽ ፣ ትዕቢተኛ፣ ቀናተኛ እና ተሸናፊዎች ተደርገው ተስለዋል፡፡ 6.9 % ከሚሆኑት ሴቶች በቀር የእነዚህ ፕሮግራሞች አዘጋጆች ወንዶች ናቸው፡፡ ይህም የሴቶች ልምድ በወንዶች እየተገለፀ እንዳለ ያሳያል፡፡

በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሴቶች ፕሮግራም ላይ የሚሰሩ የኢኮኖሚ ፕሮግራሞም ፣ ጥናታዊ ፊልሞን ጨምሮ ሴቶችን ከእጅ ወደ አፍ በሆኑ ጥቃቅን ንግዶች ላይ ብቻ የተሰማሩ ተጠቂዎች አድርገው ይስሏቸዋል፡፡  በዜና እና ትንታኔ ዘገባዎች ላይ ግን ወንዶች ብቻ ናቸው የላቀ ባለሞያ ተደርገው የሚወሰዱት፡፡  የሴቶች በላቀ ባለሞያነት እና በተለያዩ ቦታዎ የሚኖራቸው ውክልና እነዚህን አሉታዊ የተዛቡ አመለካከቶች ለመንቀል እና ለኢትዮጵያ ማህበረሰብ የሚኖራቸውን ከፍተኛ እና የተለያየ አስተዋፅዖ ለማሳየት ይረዳል፡፡

መገናኛ ብዙሃን አስተያየቶችን ለመቀየር ፣ ተልማዳዊ እሳቤዎችን ፣ ፍርሃትን እና አጉል ኩራትን ለማስወገድ አይነተኛ መሳሪያዎች መሆን ይችላሉ፡፡ የሴቶችን የላቀ ተሳትፎ ማረጋገጥ በሥራ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ተሳትፎ ለማድረግ አቅም የላቸውም የሚለውን ተፅዕኖአዊ ተረክ ለመቀየር ይረዳል፡፡

ብሔር እና ቋንቋ

ቋንቋ የባህል ፣ ዕሴቶች እና ታሪክ መግለጫ መሣሪያ በመሆን በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ የማይናቅ ሚና እንደመጫወቱ የተለያዩ ቋንቋዎች ውክልና በመገናኛ ብዙሃን ውስጥ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ስለዚህ የአንዳንድ ቋንቋዎ በደንብ አለመወከል ወይም መጥፋት የአንድን ህብረተሰብ ማንነት የመግለፅ እና ባህሎቻቸውን ጠብቆ ለማቆየት ያላቸውን መብት አደጋ ላይ ይጥለዋል፡፡

የኢትዮጵያን ሁኔታ ስንመለከት የራሳቸው ልዩ ባህል ፣ ልማድ ፣ ቋንቋ እና ታሪክ ያላቸው ከ80 በላይ የሚሆኑ ብሔረሰቦች ሲኖሩ በመገናኛ ብዙሃን በተለይም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ላይ የሚታዩት ግን በጣም ጥቂት ቋንቋዎች ብቻ ናቸው፡፡ ነገር ግን ባለፉት ጥቂት አመታት በብሔራዊ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ላይ ተጨማሪ ቋንቋዎች ቦታ እንዲኖራቸው በማድረግ የተሻሉ እድገቶች ታይተዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የህዝብ/የመንግስት የሆኑ 9 የቴሌቪዥን እና 11 የራዲዮ ጣቢያዎች እንዲሁም 48 ማህበረሰባዊ ራዲዮ ጣቢያዎች በተለያዩ ሀገር በቀል ቋንቋዎች ፕሮግራሞቻቸውን ይሰራሉ፡፡

ይህም ለበለጠ የብሔር እና ቋንቋ ውክልና ተስፋ ሰጪ ጅማሬ መሆኑን ያመለክታል፡፡ ቢሆንም ግን የመገናኛ ብዙሃን ቤቶች የቋንቋ አገልግሎቶችን ማስፋት ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የዜና ምንጮች፣ ታሪኮች እና ሌሎች ይዘቶች እንዲኖሩ ንቁ ቅስቀሳ ማድረግ አለባቸው፡፡ ይህ የተለያዩ ቡድኖች ላይ ሚዛናዊ የሆነ ትረካን በመፍጠር ራስን የመግለጽን ፖለቲካዊ መብቶችን ለማረጋገጥ እንደ ማቀጣጠያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል፡፡

የቋንቋ ውክልና ብቻውን ሌሌች ፖለቲካዊ መብቶችን ባያስጠብቅም ለተለያዩ ብሔረሰባዊ ቡድች ውስጥ ራስን ወደ መግለጥ ነፃነት ይመራል፡፡ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ገፅታ የተለያዩ ብሔሮችን እና ቋንቋዎችን ውክልና ለማስጠበቅ የሚደረገውን ጥረት በመቀጠል ነገር ግን የጎሳዎች እና ቋንቋዎችን አሉታዊ ልማዳዊ አስተሳሰቦችን የሚያጭሩ እና በአጠቃላይ ብሔር ተኮር የሆኑ አሉታዊ ተፅእኖዎችን የሚያራምድ ንግግርን ማስወገድ አለባቸው፡፡ እንደ ጋዜጠኞች, የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እና ተደማጭነት ያላቸው ሰዎች ያሉ የመገናኛ ብዙሃን ዋና ተዋንያን ልዩነትን በማስተዋል የሁሉንም ብሔረሰባዊ መለያዎች እኩልነትን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡

አካል ጉዳተኝነት

በኢትዮያ መገናኛ ብዙሃን አካል ጉዳተኞች በበለጠ ሁኔታ የተገለሉ ፣ በበቂ ሁኔታ ያልተወከሉ እና በተሳሳተ ሁኔታ የተወከሉ ናቸው፡፡ ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን እና ተያያዥ ፕሮግራሞች ወይም ከመንግስት አሳታፊ የትምህርት ፖሊሲዎች ጋር በተገናኘ ብቻ ነው መገናኛ ብዙሃን በአካል ጉዳተኝነት ዙሪያ የሚዘግብባቸው አጋጣሚዎች፡፡

ተፈራ (2005) እንደሚለው በኢትዮጵያ ውስጥ የአካል ጉዳተኞች እንደ ደካማ ፣ ተስፋ የለሽ ፣ ጥገኛ እና ያልተማሩ እንዲሁም የልግስና ዒላማዎች የማድረግ አጠቃላይ ዝንባሌ እነዚህ የተዛቡ አመለካከቶች የአካል ጉዳተኞችን አቅም በማሳነስ በአጠቃላይ አሉታዊ አመለካከት እንዲኖር ምክንያት ሆነዋል፡፡ አሁን እየተሻሻለ ቢመጣም የአካል ጉዳተኝነት መንስዔ ምክንያት እርግማን እና መጥፎ ዕድል በቤተሰብ ላይ ሲመጣ ነው የመሉ ማህበራዊ እምነቶች ነበሩ፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 በዓለም ባንክ እና የዓለም ጤና ድርጅት በጣምራነት በታተመው የአካል ጉዳተኝነት የዓለም ሪፖረት በኢትዮጵያ ውስጥ ወደ 15 ሚሊዮን የሚጠጉ አካል ጉዳተኛ ሰዎች እንደነበሩ ግምቱን አስቀምጧል፡፡ ይህም በወቅቱ ከነበረው የሀገሪቱ ህዝብ ብዛት ውስጥ 17.6 % ይወክላል፡፡   ምንም እንኳን ይህ ቁጥር በቸልተኝነት የሚታይ ባይሆንም የአካ ጉዳተኝነት ጉዳዮች ግን በበቂ ሁኔታ በመገናኛ ብዙሃን አልተሸፈኑም፡፡ ለምሳሌ ያህል፡ በመዓዛ መንክር የማስተርስ የመመረቂያ ጽሁፍ “የኢትዮጵያ ብሔራዊ የመገናኛ ብዙሃን ለአካል ጉዳት ጉዳዮች የሰጡት ሽፋን” (እ.ኤ.አ 2008) ግኝት መሰረት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ኢትዮጵያ (በኤሌክትሮኒክ ሚዲያዎች መካከል ባለ ትልቅ ድርሻ እና ሽፋን) በአንድ ዓመት ውስጥ በተካሄደ የፕሮግራም ምርመራ ወቅት ከአካል ጉዳት ጋር ለተያያዙ ጉዳዮች እንደ ቅደም ተከተላቸው 1.3% እና ከ 0.51% የሽፋን ሰዓት ሰጥተዋል፡፡ ይኸው ጥናት እንደሚያመለክተው ሪፖርቶቹ በከፍተኛ ሁኔታ የተመሰረቱት አካል ጉዳተኛ ሰዎች በዕለት ተዕለት ኑሮአቸው በሚያጋጥሟቸው ፈታኝ ሁኔታዎች ይልቅ በስኬት (የመንግስት ፕሮግራሞች) እና ክስተቶች ላይ መሆኑን አትቷል፡፡ አካል ጉዳተኛ ሰዎች ህፃናትም ሆኑ አዋቂዎች የራሳቸውን ዕውነት ራሳቸውን ወክለው ሊናገሩ ይገባል፡፡ ነገር ግን በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ሪፖርቶች ላይ ጉዳዩ ከዚህ ይለያል፡፡

ወደፊት እንዴት?

ቀደም ባሉት ጊዜያት ተገልለው የነበሩ የህብረተሰብ አካላት ታሪኮቻቸውን በሚዛናዊ እና ሀዘኔታ ባልተሞላበት መንገድ የመናገር መብቶቻቸው ላይ ለኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን አካላት ስልጠና መሠጠት የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ የዜና ዘጋቢ ተቋሞችም የፆታዊ እና ብሔር ተኮር ዘገባዎቻቸው ስብጥራቸው በደንብ እንዲታይ ግድ ይላል፡፡

መገናኛ ብዙሃን በሴቶች ላይ ያላቸውን አሉታዊ ልማዳዊ እሳቤዎችን እና በበቂ ሁኔታ አጀለመወከል ለመዋጋት እና ሥርዓተ – ፆታዊ እኩልነትን ለማስፈን ጠንክረው ዘመቻ የሚከፍቱ እንደ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ሴቶች ማህበር ያሉ ማህበራትን ማጠናከር መገናኛ ብዙሃኑን የበለጠ ተጠያቂ ለማድረግ ያገለግላል፡፡ ሌላው መፍትሔ ደግሞ መገናኛ ብዙሃን የሚኖራቸውን ያልተገቡ ውክልናዎችን ለመቆጣጠር በህግ ስልጣን የሰተሰጠውን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን አቅም መገንባት ሊሆን ይችላል፡፡ በመገናኛ ብዙሃን ሥራዎች ውስጥ እና በአመራር ቦታዎች የሴቶች ቁጥር እንዲጨምር የሚስገድዱ ደንቦች እንዲረቀቁም መታገልም ያግዛል፡፡

ሰላም ሙሴ በአዲስ አበባ የምትገኝ በፆታ እና ሚዲያ ላይ ትኩረት ሰጥታ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽንስ አማካሪ ናት፡፡
ቤተልሔም ነጋሽ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽንስ አማካሪ ስትሆን አዲስ አበባ ውስጥ ለሚገኝ ጋዜጣ በፖለቲካዊ ግንኙነት እና ፆታዊ ጉዳዮች ላይ ትፅፋለች፡፡
selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *