በፍቃዱ ኃይሉ ከመንግሥት አካላትም ይሁን የማኅበራዊ ድረ ገጽ ተሳዳቢዎች የሚነሱ ጥቃቶች እንዴት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀንን እውነትን ለኀያላን የመናገር አቅማቸውን እንዳዳከሙት ይናገራል፡፡

ሕዳር 2011 ኢትዮጵያ አንፃራዊ የጋዜጠኝነት ነፃነት እያየች በነበረበት ወቅት እና ከ1997 ወዲህ በአገሪቱ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሥራቸው ጋር በተያያዘ የታሰሩ ጋዜጠኞች በሌሉበት ጊዜ ስድስት ጋዜጠኞች በጋምቤላ ክልል አቦቦ ወረዳ ውስጥ ታፍነው ተወስደው ነበር፡፡ መታሰቢያ ካሳዬ – የሳምንታዊው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋዜጠኛ ከታፈኑት ጋዜጠኞ ውስጥ አንዷ ነበረች፡፡ ክስተቱን ስትናገር በእንባ ታጅባ ነው፡፡ “በጣም ያስፈራ ነበር” በማለት በቀላሉ ገልጻዋለች፡፡

ጋዜጠኞቹ የደንብ ልብስ በለበሱ የክልል የፀጥታ ኃይሎች ነበር ታፍነው ነበር የተወሰዱት፡፡ ጋዜጠኞቹ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ሠራተኞች እና ባለሀብቶች በአካባቢው አስተዳደር ላይ በነበራቸው ቅሬታ ዙሪያ ዘገባዎችን በመሰብሰብ የመስክ ሥራ ላይ ነበሩ፡፡ የታፈኑትም ባለሥልጣናቱን ስለቀረበባቸው ቅሬታ መልስ እንዲሰጡ ከጠየቁ በኋላ ነበር፡፡ ማስፈራሪያ ደርሷቸው፣ ተደብድበው፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮቻቸውን እና የቀረጿቸውን ሥራዎች ተቀምተው በመጨረሻም የሰበሰቧቸው መረጃዎች በሙሉ አንዲጠፉ ተደርጎባቸው ነበር፡፡ ከሰዓታት አፈና እና ማስፈራራት በኋላ ሲለቀቁ የሙያ መሣሪያዎቻቸውን ሁሉ ትተው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል፡፡

ይህንን አፈና ያዘዙት እና የፈፀሙት ባለሥልጣናት አንዳቸውም ቢሆኑ ተጠያቂ አልተደረጉም፡፡ ከዛም ባለፈ የነዋሪዎቹ ቅሬታዎችም ሪፖርት ሳይደረግ ቀርቷል፡፡

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ጥቃት ደረጃ መገናኛ ብዙኀኑ እንዳላቸው እውነትን ለኀያላን የመናገር አቅም ደካማ አይደለም፡፡ እንዲያውም የጥቃት ደረጃው ለመገናኛ ብዙኀኑ ድክመት ግብዓት ሆኗል፡፡ ጋዜጠኝነት በኢትዮጵያ ውስጥ ሁልጊዜም ቢሆን አስጊ እና ጋዜጠኞችን ወደ ሌሎች የሥራ ዘርፎች ለመቀላቀል የሚገፋፋ ወይም በሕዝብ ግንኙነት ቦታዎች እንዲገደቡ የሚያደርግ ሥራ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት እንደ ተርዬ ስክየርዳል እ.አ.አ.በ2016 ያወጣው የኢትዮጵያ ሪፖርት መሠረት “የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች አጭር ሙያዊ ልምድ – በአማካይ (ልምዳቸው ብቻ) 5.2 ዓመታት ነው።”

ከጥቅምት 1985ቱ የፕሬስ ነፃነት አዋጅ ጀምሮ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኞች ከመንግሥትም ሆነ መንግሥታዊ ካልሆኑ አካላት ጥቃቶችን ያስተናግዱ ነበር፡፡ አንዳንድ ጋዜጠኞች ሀገራቸውን ጥለው ሲሰደዱ የተወሰኑት ደግሞ ታስረው ነበር፡፡ ሌሎቹ ደግሞ በፍርሐት ተሸማቅቀው እንዲሁም አስደንጋጭ ተፅዕኖው  ብዙዎችን ራሳቸውን ሳንሱር እንዲያደርጉ አስገድዷቸዋል፡፡

የጥቃት ዓይነቶቹ ከማሥፈራራት፣ ስድቦች፣ የኢንተርኔት ዛቻ፣ ፆታዊ ጥቃት፣ የግድያ ዛቻዎች፣ ማሰቃየት ጀምሮ እስከ እስር ድረስ ይዘልቃሉ፡፡ ባለፉት 3 ዐሥርት ዓመታት መንግሥትን በከፍተኛ ሁኔታ በመተቸት የሚታወቀው እና ከ8 በላይ የኅትመት መገናኛ ብዙኀን ውጤቶች አርታኢ እና መሪ የነበረው እስክንድር ነጋ ከእነዚህ የጥቃት ዓይነቶች አብዛኞቹ ደርሰውበታል፡፡ እስክንድር የጥቃቶቹን ዓይነቶች በሁለት የተለያዩ ወቅቶች ይከፋፍላቸዋል፤ ቅድመ 2010 እና ድኅረ 2010 በማለት።፡ እንደ እስክንድር ገለጻ አዲሱ አመራር ሁሉንም የታሰሩ ጋዜጠኞች ለመፍታት እና ነጻ ምኅዳር ለመፍጠር ቃል ገብቶ ሥልጣን ላይ ከወጣ በኋላ “ዛቻዎቹን እንዴት መቋቋም እንደሚቻል መማር አስቸጋሪ የሆነበት አዲስ ሁኔታ ተፈጥሯል” ሲል ያስረዳል፡፡

“የተሳሳተ መልዕክት እንዳላስተላልፍ ስል ብቻ ለቃለ መጠይቅ ከመሄዴ በፊት ስለምለብሰው ልብስ የምጨነቅባቸው ጊዘያት አሉ፡፡ “ ስትል ትናገራለች፡፡

የህትመት ሥራው እ.ኤ.አ በ2016 በነበረው ቀውስ ስራው የቆመው የአዲስ ስታንዳርድ ዋና አርታዒ ፀዳለ ለማ በመንግስት በኩል ያለው ሁኔታ የተሻሻለ ሲሆን በማህበራዊ ትስስር ገፆች ያለው ትንኮሳ ግን የጋዜጠኞችን ደህንነት እያሰጋ መሆኑን ትናገራለች፡፡ “አንዳንድ ጊዜ የጋዜጠኞቻችንን ደህንነት አደጋ ውስጥ ላለመጣል ስንል እውነታ እንደታፈነ ቢገባንም የአንዳንድ ታሪኮችን ምርመራ እና ዘገባ ስራ

ግን እናቆማለን፡፡ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ጋዜጠኞች ወደ አንድ ቦታ ሄደው ስለተፈጠረ ነገር ሄደው ለመዘገብ እንዳይችሉ የሚያደርግ ትረካዎችን የመጠምዘዝ መርዛማ አካሄድ አላቸው፡፡ “ ስትል አክላለች፡፡

በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ዘጋቢ በመሆን የሚሰሩ የውጪ ሀገር ጋዜጠኞችም በተለይም ከዋና ከተማው ለዘገባ ወጥተው በሚጓዙበት ጊዜ ተለይተው በተደጋጋሚ አጫጭር እስሮች አጋጥሟቸዋል፡፡

እ.ኤ.አ ሰኔ 2011 ላይ ሁለት የስዊድን ጋዜጠኞች ማርቲን ሺብዬ እና ዮሃን ፒርሰን በኦጋዴን ሶማሌ ክልል የነበረውን የስዊድን የነዳጅ ማውጫ ድርጅት እንቅስቃሴዎች ሊመረምሩ በክልሉ ተገኝተው ነበር፡፡ ኬንያ ላይ በዘይት ማውጫው አካባቢ ይፈፀማል የሚባለውን በደል ከኢትዮጵያ ሶማሌ ስደተኞች ሰምተው ነበር፡፡ ከኢዮጵያ መንግስት ስለ አካባቢው ለጋዜጠኞች መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ ስለነበር በወቅቱ “አሸባሪ ድርጅት” ተብሎ የተሰየመው የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ሠራዊት አባላት ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ገቡ፡፡ በዚህም ምክንያት በክልላዊ መንግስቱ ጦር ዒላማ ውስጥ ገብተው በትከሻቸው እና በእጃቸው ላይ በጥይት ተመትተው ተይዘው ታሰሩ፡፡ በ “ፀረ- ሽብርተኝነት” ህጉም መሰረት ተከስሰው “ጥፋተኛ” ሆነስ ስለተገኙ የ11 ዓመት አስከፊ እስራት ተፈረደባቸው፡፡ በመጨረሻም ከ438 ቀናት የእስር ቆይታ በኋላ “በምህረት” ተለቀቁ፡፡ ይሁን እንጂ እ.ኤ.አ በ2018 መጨረሻ አካባቢ መንግስት ኦብነግን ከሽብርተኛ ዝርዝር ውስጥ አውጥቶታል፡፡

በአሁኑ እስክንድር ነጋ ድህረ 2018 ብሎ በሚጠራው ጊዜ መገናኛ ብዙሃንን የሚመለከቱ ህጎች እና ደንቦች እ.ኤ.አ ከሐምሌ 2018 ጀምሮ በክለሳ/ማሻሻያ ላይ ናቸው፡፡ የህጎች ማሻሻያ ጋዜጠኞች ሥራቸውን ለመሥራት አመቺ ከባቢን መፍጠር ይኖርበታል፡፡ ነገር ግን መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት የሚመጡ  የፕሬስ ነጻነት ፈተናዎችንም ማካተት አለበት፡፡ ማሻሻያዎቹ ጋዜጠኞች ስራዎቻቸውን ሲሰሩ ከሚደርስባቸው አደጋ እንዲጠበቁ የሚያደርግ ከሆነ ከዚህ በፊት ከነበረው ጨቋኝ ጊዜ የተሻለ አወንታዎ ለውጥ እንደሚኖረው እሙን ነው፡፡

በፍቃዱ ኃይሉ ተጫኔ ኢትዮጵያዊ ፀሃፊ፣ የመብት ተሟጋች እና ጦማሪ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በሚያዝያ 2014 በጦማር እንቅስቃሴአቸው ምክንያት ታስረው ከነበሩት የዞን 9 ጦማሪያን ውስጥ አንዱ ነው፡፡ የወላጆቻቸው ልጆች (Children of their Parents (2013) በሚል ርዕስ የፃፈው ልብ ወለድ እ.ኤ.አ 2012 ላይ የ በርት አዋርድ የአፍሪካ ፀሀፊ የሶስተኛ ደረጃ አሸናፊ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ ለበ2015 ከሌሎች የዞን 9 ጦማሪያን ጋር በመሆን የዓለም አቀፍ ፕሬስ ነፃነት አዋርድን ከጋዜጠኞች ጠባቂ ኮሚቴ ተቀብሏል፡፡

REFERENCES

1 CPJ, “Hundreds of journalists jailed globally becomes the new normal”, 13 December 2018

2 Metasebiya Kassaye, “አስገራሚው የጋዜጠኞች እገታ በጋምቤላ”, Addis Admass newspaper, 3 November 2018

3 Melat Mulugeta, “Mereja TV journalists at- tacked in Legetafo town”, https://mereja.com/index/267001, 25 February 2019

⁴ Martin Schibbye and Johan Persson, “438

Days”, Offside Press, 2015 (Henning Koch translation)

USEFUL REFERENCES

UGANDA: https://acme-ug.org/ and the link to the election coverage report is https://acme- ug.org/2016/06/22/acme-report-gives-media-a-mixed-report-card-for-coverage-of-2016-election/

ZIMBABWE: http://gmc.org.zw

MEDIA FREEDOM http://journodefender.org https://en.unesco.org/fightfakenews

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *