ሩዋንዳ ፕሮፓጋንዳ እውነትን ሲደፈጥጥ ምን ሊፈጠር እንደሚችል የምታሳይ አሳዛኝ ምሳሌ ናት፡፡ ከ 800000 በላይ ሩዋንዳውያን ህይወታቸውን እንዲያጡ ምክንያት ለሆነው የዘር ጭፍጨፋ መገናኛ ብዙሃን በማሰባሰብ እና በማቀነባበር የማይናቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ እ.ኤ.አ የ1994ቱን ጭካኔ የተሞላበት ክስተት ተከትሎ በተደረገው ጥናት እና ትንተና ይህ የመገናኛ ብዙሃን ሚና ተለይቶ ወጥቷል፡፡

እናም ፕሮፓጋንዳ በሚነዛበት ወቅት በተለይም ምርጫ እየቀረበበ በመጣበት ጊዜ እንዴት በተቻለ መጠን ትክክለኛ ዘገባን ማዘጋጀት እንችላለን?

ጥሩ ጋዜጠኞ እና ዘጋቢዎች ሁልጊዜም ቢሆን ስልጣን ከያዙ ሰዎች ገለልተኛ ናቸው፡፡ ለፖለቲከኞች መልዕክት ርባና የለሽ ማሰራጫ ወይም ድምፅ ማጉያ ሆነው አይገኙም፡፡ በተጨማሪም እንደ ፕሬዚዳንት ፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር ወይም ገዢ ፓርቲ ላሉ ባለስልጣናት ስንል ብቻም አይደለም ስለ ነጻነት የምናወራው፡፡

እናስታውስ፡ ስልጣን በእጃቸው ያለው እነሱም ተቃዋሚዎች ናቸው፡

፡ ሌሎች ተቃዋሚዎችም ቢችሉ ለመራጮቻቸው መልዕክቶቻቸውን ለማሰራጨት ልክ ገዢው ኃይል እንደሚያደርገው መገናኛ ብዙሃንን እና ጋዜጠኞችን መጠቀም ይችላሉ፡፡ የጋዜጠኞ ጠለቅ ያለ ፍተሻ እና ነፃነት በዓለም ላይ ከፍተኛ የፋይናንስ ፣ ባንኪንግእና ንግድ ቦታዎች ላይ የሚገኙትንም ይሸፍናል፡፡ ሁሉም ምንጮችጋዜጠኞችን እንዲያናግሩ ሊያነሳሱ ይገባል፡፡ ስለዚህ ሁልጊዜም ቢሆን የሚነገረንን ነገር ለምን እንደሚነገረን ራሳችንን መጠየቅ አለብን ፤ ምክንያቶቹንም መርምረን ምን እንደምናትም እና ምን ዓይነት ቅርፅ እንደሚኖረው በጥንቃቄ ልንወስን ይገባል፡፡

እነዚህን ድክመቶች ለማጥፋት እንዴት ልንሰራ እንደምንችል ትጠይቁ ይሆናል? እና ምርጫን በምንሸፍንበት ጊዜ ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ የትግበራ ስልቶችን እንዴት መተግበር እንችላለን? በራሳቸው ቀለም ነፃ እና ፍትሃዊ ምርጫዎች የጠንካራ ዴሞክራሲ ምሰሶዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ ጋዜጠኞች እንደመሆናችን ምርጫው

ነጻ እና ፍትሃዊ ስለመሆኑ ለማረጋገጥ ምን ምን ሚና መጫወት እንዳለብን እራሳችንን መጠየቅ ይገባናል፡፡ በወቅቱ በሚካሄደው ምርጫ ጥራት ያለው የጋዜጠኝነት ሥራ መስራት ለሚፈልግ ትልቅ ጋዜጠኛ ፣ ጠንካራ ዘገባን ይዞ ለመቅረብ፣ ከልማዳዊ እሳቤዎች እና የፖለቲከኞች መጠቀሚያ ከመሆን በደንብ እና በጥሩ ሁኔታ እንዲርቁ የሚያግዙ አንዳንድ ጠቃሚ ምክሮች እነሆ::

  1. ወደ ህዝቡ እንመለስ

ጥሩው ምክሬ የሚሆነው ከህዝቡ ጋር መስማማትን ወደ ህዝ መመለስ ነው፡፡ በዘገባችን ዜጎችን ፣ አካባቢያዊ ማህበረሰቦቻቸውን ፣ ችግሮቻቸውን እንሸፍን፡ ነገር ግን በተጨማሪም ለሚኖሩባት ሀገራቸው ያላቸውን ተስፋዎች እና ህልሞችም ጭምር፡፡ ስለዚህ ከተቀነባበረው የፖለቲከኞች ሽፋን እና መልዕክት መንገዶቻቸው መራቅ ያስፈልጋል፡፡ አንድ የዴንማርክ ራዲዮ ጣቢያ ፖለቲከኞች የማይጋበዙበት የተዘጋጀ የፖለቲካ ፕሮራምን ማዘጋጀት ልምዱ አድርጎታል፡፡ ይልቁንስ የመወያያ ጉዳዮቹ የሚነሱት ተጽዕኖ በሚያሳርፉባቸው እና በሚመለከታቸው ሰዎች መካከል ነው፡፡

አንድ ሆስፒታል የካንሰር ታማሚዎችን የማከም ችግር ካለበት ታማሚዎቹ ፣ ዘመዶቻቸው ፣ ዶክተሮቹ ፣ ነርሶቹ እና የጤና ባለሞያዎቹ ናቸው ችግሩ እንዴት መፈታት እንዳለበት የሚወያዩበት፡፡ ስለ ጉዳዩ እያደገ መምጣት ሳይሆን እንዴት መፈታት እንዳለበት ነው የሚገደው፡፡

ምናልባትም ተነሳሽነቱን ከአንባቢዎቻቸው ዕውቀት እና ግብኣቶችን በማሰባሰብ ስኬታማ ከሆነው ከደች ኦንላይን ሚዲያ De Corre- spondent ማግኘት ይቻላል፡፡ De Correspondent አንባዎቹን “ከፍተኛው የጋዜጠኝነት ያልተነካ ግብዓት” ብሎ ይጠራቸዋል፡፡ ስለዚህ ዓለምን በተሻለ ሁኔታ ለመግለፅ ትንሽ ፖለቲከኞች እና ብዙ ዜጎች ያስፈልጉናል፡፡

  1. ህዝቡን እናንቃ

ወደሰዎች ከተመለስን በኋላ አሁን ደግሞ ማንቃት ያስፈልጋል፡፡ ዘገባዎችን በአንድ አቅጣጫ ብቻ ከማየት ከአንባቢዎች ፣ ከአድማጮች እና ተመልካቾች ጋር ውይይት መጀመር ያስፈልጋል፡፡

የማ ህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ይህ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ በጣም ቀላል ሆኗል፡፡ ሰዎች መመለስ የሚፈልጉትን ጥያቄ እንጠይቅ፡ለምርጫ ድምፅ ከመስጠታቸው በፊት እንዲሁም መልስ በሚሰጡበት ጊዜ በህይወታቸው ብሎም በልባቸው ውስጥ በጣም ሰፊ ስፍራ ያለው ነገር ምንድን ነው? በአስተያየታቸው መሰረት

እርምጃ እየወሰድን እንደሆነ እንዲያውቁ እናድርግ፡፡ ሪፖርት አድርገንላቸው ሌሎች አዳዲስ ጥያቄዎችን እንጠይቅ፡፡ ከባድ አይደለም እንደ የአንድ ወገን ሪፖርት ሳይሆን ልክ እንደ ውይይት እንቁጠረው፡፡

በናይጄሪያ Trackaን አዘጋጅተዋል፡፡ Tracka ሰዎች በአካባቢያቸው ያሉ የካፒታል ፕሮጀክቶች ላይ እንዲሳተፉ እና እንዲተባበሩ ያስችላቸዋል፡፡ በጀት ያላቸውን ፕሮጀክቶች ሪፖርት የሚያደርጉ ንቁ ዜጎች ያሉበት መረብ ነው፡፡ ይህም የ Tracka ቡድን በ Tracka መተግበሪያ አማካኝነት ከዜጎች ያገኙትን መረጃ እና ማረጋገጫዎች በመንግሥት ውስጥ ለሚመለከታቸው አካላት በቀጥታ እንዲልክ ያስችለዋል፡፡ ዜጎች ቃል የተገባላቸው ፕሮጀክቶች ላይ ያለውን ሂደት እና ተጠያቂነት እንዲጠየቁም ያበቃቸዋል፡፡

  1. ከልማዳዊ አስተያየቶች እና ዋልታ ተኮር ዘገባ እንራቅ

በአሜሪካ ጋዜጠኝነት ላይ ትግሉ የአሜሪካን ዜጎች የሚፈልጓቸው ጉዳዮችን ትክክለኛው መንገድ ለመዘገብ ነው፡፡ በምትኩ, መገናኛ ብዙሃን ሁሉም ዶናልድ ትራምፕን በሚደግፉ እና በሚቃወሙ ትረካዎች በሚተረጎምበት እና በሚፈረጅበት በእሱ እንዲህ አለ – እሷ እንዲህ አለች ወሬ ወጥመድ ውስጥ ገብተዋል.፡፡ ተመሳሳይ አይነት ስህተትን የትም ብንሆን አንስራ፡፡ ነባራዊው ሁኔታ ሁለት ቡድኖች እርስ በእርስ የሚፋተጉበት ብቻ አይደለም፡፡ መጀመሪያ

ከሁለቱ ቡድኖች እይታ በመነሳት እንደማንዘግብ እርግጠኛ እንሁን፡ ፡ ከሆነም ከጥልፍልፉ እንውጣ ፣ ራሳችንን በመሃል ወይም ከዚህ ሁለት ቡድን ውጪ ማን እንዳለ እንጠይቅ ፣ በዚህ የጋዜጠኝነት ግርዶሽ ውስጥ ሳይታዩ ወይም ሳይዳሰሱ የሚታለፉት ሰዎች እና ድምፆች እነማን ናቸው?

እንፈልጋቸው፤ ለነሱ አስፈላጊው ነገር ምን እንደሆነም እንጠይቃቸው፡፡ ተስፋ የሚያደርጉት ምንድን ነው? እዛ ለመድረስ ምን ያስፈልጋቸዋል? እዛስ ለመድረስ እርምጃ ይወስዳሉ? እንዴት?

ኒው ዮርክ ታይምስ ዶናልድ ትራምፕ እ.ኤ.አ በ2016 በፕሬዚዳንትነት ከተመረጡ በኋላ ኢ-ዋልታ ተኮር የሆነ ሙከራን አድርጎ ነበር፡፡ ተከታታይ የሆኑ ቤተሰብ እና ጓደኛ የሆኑ ለሁለቱ ተቃራኒ ተመራጮት የመረጡ ሰዎች ቁጭ ብለው የሚያወሩበት “እኔ ክሊንተንን መርጫለሁ ፣

እናንተ ተራምፕን መርጣችኋል፤ እናውራበት” የሚሉ ፖድካስቶችን አዘጋጅተው ነበር፡፡ ከፕሮጀክቱ ውስጥ በጣም አበረታች እና አስደሳች የነበሩት የሚየቁት ጥያቄዎች ነበሩ፡፡ እስቲ ከጎን ያለውን ሰንጠረዥ እንመልከትና ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አዛምደን መጠቀም ከቻልን ለሪፖርታችን

እንዲመች አድርገን አስተካክለን እንውሰዳቸው፡፡ ያኔ ቁምነገር ያላቸውን ጥቆማዎች እና ሀሳቦችን ልናገኝበት የምንችንል ለሁለት ተቃራኒ ቡድኖች የመከራከሪያ መድረክ ማዘጋጀት እንችላለን፡፡ ዋጋ ያለው የጋዜጠኝነት ውጤትንም እናገኛለን፡፡

  1. የሰዎችን ልምድ እንጂ አስተያየት አንጠይቅ

በመጨረሻም ብልህ ጋዜጠኛ የሚጠቀመው ፣ ኢንተርኔት የማይፈልግ እና ለአጠቃቀም ቀላል የሆነ መሳሪያ ቢኖር፡ ሰዎችን አከራካሪ ስለሆነ የተጋጋለ ውይይት ስንጠይቃቸው ስለ ልምዶቻቸው እንጂ ስለ አስተያየታቸው አንጠይቅ፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች አስተያየታቸውን ሲጠየቁ መሰረት የሚያደርጉት አፈ ታሪኮችን ፣ እምነቶችን ፣ አሉባልታን እና ፖለቲካዊ ጥልፍልፎችን ነው፡፡ ውጤቱ ብዙ ጊዜ እውነታን የማያንፀባርቅ ሲሆን በማንኛውም ሀገራዊ ክርክሮች ላይ የሚኖርን የማስጠንቀቂያ ደወል የሚያሞግስ ነው፡፡ በምትኩ የሰዎችን ልምድ ስንጠይቅ ብዙ ጊዜ ነባራዊ ሁኔታን የሚያሳይ – ተዓማኒ እና እውነተኛ ውጤት እናገኛለን፡፡  ብዙም ባለ ጠባብ እይታ አይደለም እናም ለደማቅ የምርጫ ጋዜጠኝነት ሽፋን እንደ መነሻ ያገለግላል፡፡

ካትሪን ጊልደንስቴድ በጋዜጠኝነት ከ19 ዓመታት በላይ ሰርተዋል፡ ፡ እ.ኤ.አ ከ 2011 ጀምሮ በዜና ዘገባዎች ውስጥ አዳዲስ እና ገንቢ ዘዴዎችን በማካተት መርታለች፡፡

FIND MORE INFO HERE

https://medium.com/de-correspondent/rein-venting-the-rolodex-why-were-asking-our-60-000- members-what-they-know-9be6a857c340i

 http://www.tracka.ng/ https://www.facebook.com/trackanigeria/ https://ww.nytimes.com/2016/11/18/podcasts/how-could-you-19-questions-to-ask-loved-ones- who-voted-the-other-way.html

 https://www.mycountrytalks.org/

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *