የተሳሳተ ዲጂታል መረጃ በሚታይበት ጊዜ የመናገር እና የዴሞክራሲን ነጻነት ለመጠበቅ የመገናኛ ብዙሃን እና የመረጃ መሰረተ ትምህርት አስፈላጊነት ላይ ትኩረት አድርገዋል “ምንም አይጠፋም ፣ ሁሉም ባለበት ይቆያል” የሚለው ፅሁፍ በፊዚክስ እና ኬምስትሪ ህጎች ላይ ካሉ ውይይቶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ አቶሞች መቼም ቢሆን ሊጠፉ አይችሉም፡፡ ባሉበት ይቆያሉ፡ ፡ ቅርፃቸውን ሊቀያይሩ ፣ ሊለወጡ ፣ ሊደበቁ ወይም ሊበታተኑ ቢችሉም ከመኖር ግን አይጠፉም፡፡ ይህም በዲጂታል አውድ ውስጥ እንዳለ ግንኙነት ማለት ነው፡፡ ይቆያል ፣ ይከፋፈላል ፣ ይባዛል፡፡ ሌላው አካላዊ መገለጫ ደግሞ በቁጥጥር ስር ያለ እንቅስቃሴ ወደ ለቁጥጥር አስቸጋሪ ኃይል የሚቀየርበት ግራ መጋባት እና ሁካታ ነው፡ ፡ ይህም የተፈጥሮ ሁኔታ ነው፡፡ ሁካታ ሁልጊዜ ያሸንፋል፡፡ በዲጂታል ዓለም ደሞ መለካት ወይም መቀመር በማይችሉ ዳታ እና ቀመሮች መሠረት ግራ መጋባት ከፍተኛውን ቦታ ይይዛል፡፡ ከተፈጠረበት እ.ኤ.አ 90ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ ኢንተርኔት ላይ ብዙ ነገር ተደርጓል፡፡ ግልጽ የሆነ ፣ ዴሞክራሲያዊ ፣ ግልጽ እና የተረጋጋ ድርጅት ለመፍጠር የመጀመሪያው ግስጋሴ በቀመር እና የተለያዩ ፍላጎቶች እርስዎን – የኢንተርኔት ተጠቃሚ – በአንድ የተወሰነ አቅጣጫ ወደ አንድ አተገባበር እንዲገቡ ማስቻል ነበር፡፡ ለንግድ ፣ ፖለቲካ ፣ ኃይማኖታዊ ወይም ዝም ብሎ የማይረባ ምክንያት፤ በተከፋፈለ የመገናኛ ብዙሃን አቅርቦት እና ግለሰባዊ አጠቃቀም በሰዎች እና በተቋማት መካከል ያለው ክፍተት ያድጋል፡፡ ህዝባዊነት በሁሉም የዓለም ማዕዘናት ላይ እንደ ገዳይ ቫይረስ እተሰራጨ ነው፡፡ እንደ ፍሪደም ሀውስ መረጃ የአለም ዴሞክራሲ በአሁኑ ጊዜ ረፍት ላይ ነው፡፡ አደገኛ ኃይሎች ደግሞ ፖለቲካዊ መብቶችን እና ሲቪል ነፃነቶችን እንዲከላከሉ የተቀመጡትን ተቋማት እየተገዳደሩ ይገኛሉ፡ ፡ ጋዜጠኝነት በህጋዊ ትንኮሳ እና በስሜታዊ ዘመቻዎች የተዳከመ ነው፡፡ በአጠቃላይ ሁሉም እንደ የቴክኖሎጂ እድገትና ዝቅተኛ ወጪዎች ውጤት – ወደ ዲጂታል አሳታሚ እና ፕሮዲዩሰርነት በመምጣት የተለመደውን ህትመት ቤቱት ወደማይታመን ተቋም ለውጠውታል፡፡ ይህም በጋዜጠኞች ላይ ጥላቻ እና ማስጠንቀቂያዎች እንዲደርሱባቸው መንገድ ከፍቷል፡፡ ሁላችንም ማግለል እና xenophobia እንዲያድጉ ምቹ ሁኔታን የፈጠረ በከፍተኛ ሁኔታ ዋልታ ተኮር የሆነ ማህበረሰብ ውስጥ ነው የምንኖረው፡፡ የትዊተር ማዕበል በህብረተሰቡ ውስጥ ያለውን ልዩነት ላይ የተመሰረተ ክርክር የተካበት ፣ አድማሳችንን አስፍተን ሁሉን አቀፍ ማድረግ ስንችል የራሳችንን ምስል ብቻ የምናይበት ፣ የራሳችንን ፎቶ ብቻ የምናነሳበት ጊዜ ነው፡፡ በዚህ አውድ የዴሞክራሲን ፣ ነፃ ማህበረሰብን እና ኃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን መሰረታዊ መርሆዎች ማስከበር አለብን፡፡ እንደ ሰውነታችን በተለያየ ይዘት እና ቅርፅ የሚኖሩ ጥላቻን ፣ ትንኮሳን ፣ የተሳሳተ መረጃን እና ፕሮፓጋንዳን ለመቆጣጠር አቅማችንን ማጠናከር ይኖርብናል፡፡ የተለመዱት ጠባቂዎች እና ኃላፊነት ያለባቸው አታሚዎች ሁሉም መረጃ በማህበራዊ ትስስር ገፆች በኩል ተጣርቶ በሚያልፍበት እና በሳይበር ሐሰተኛ ዜናዎች እንዲሁም ተንኮል አዘል ፕሮፓጋንዳ እየተዋጡ በሚመጡባቸው አንዳንድ ጊዜያት ጫናውን ተቋቁመን ማለፍ አለብን፡፡ አስተያየቶ እና ሃሳቦች ጥያቄ ሳይቀርብባቸው ሲቀሩ እና የተረጋገጡ እውነታዎች እና ሳይንስ ሳይታመኑ ሲቀሩ ፤ የተለመደው የአታሚዎች ንግድ ጉዳይ (የጋዜጣ ሽያጭ) ሲሞት ፣ የመገናኛ ብዙሃን አዘጋጆች የክፍያ ጣሪያዎችን ሲያስተዋውቁ “በቤት ውስጥ የተዘጋጁ” ዜናዎችን እና በስሜት ቁጥጥር ስር የወደቁ መረጃዎችን ዲጂታል መረቦች እንዲጋሩት ቦታ ይከፍታል፡፡ ዘመናዊ ትስስር መሰረቱን ያደረገው በአነስተኛ ፅሁፍ እና በብዙ ምስሎች በመደገፍ ነው፡፡ በሁሉም ቦታ ፣ በማስታወቂያዎች ፣ በተንቀሳቃሽ ስልክ ግንኙነቶች ፣ ዜናዎች ፣ የማህበራዊ ትስስር ሁነቶች ፣ ዩቲዩብ እና ሬዲት ን ጨምሮ 24/7 መረጃዎችን ከምስሎች ጋር በማዛመድ እንፈጥራለን፡፡ ነገር ግን አሳሳቹ ነገር – ምስሉ እንደ አንድ ክስተት በቀላሉ አእምሮአችንን እና የማሰብ ችሎታችን የሚኖሩበት የአንጎል ክፍል በቀላሉ ያልፈዋል፡፡ በቀጥታ ስሜትን ዒላማው ያደርጋል፡፡ ውጤታማ ነው፡፡ ልክ “አንድ ፎቶ ከሺ ቃላት በላይ ይናገራል “ እንደሚለው የዱሮ አባባል፡፡ በቅርቡ ከተካሄደው የአሜሪካን ምርጫ እና የእንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት መውጣት ክስተት የምንማረው አንድ ነገር ቢኖር የምርጫን ውጤት በትክክል ለመገመት እየከበደ መምጣቱን ነው፡ ፡ ከዚህ በኋላ አንድ መራጭ ምርጫውን እንዴት እንደተረዳውና ማንን ሊመርጥ እንደሚችል መረዳት ከባድ ነው፡፡ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ እየተሳተፍን መሆናችንን ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህን ነገር በእርግጠኝነት አለማወቃችን የሚደንቅ ነው፡፡ በዚህ የዲጂታል ዘመን እንዴት እርስ በርስ ተፅዕኖ  እንደምናሳድር ለመረዳት በአዲስ አመክንዮ ማስረዳት ይቻላል፡፡ ከዚህ በፊት ፖለቲከኞችን ፣ አስተማሪዎችን ፣ ወላጆችን እና ሌሎችን በመሳሰሉ ባህላዊ ባለስልጣናት ተፅዕኖ ስር በይበልጥ እንገኝ ነበር፡ ፡ አሁን ግን መረጃዎችን ፣ ኃሳቦችን እና አስተያየቶችን በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በሚያጋሩ ሌላ አይነት ተፅዕኖ አሳራፊዎች ስር እንገኛለን፡፡ ስለዚህ መረጃን ከበፊቱ በበለጠ እናገኛለን ማለት በደንብ ተረድተነዋል ማለት አይደለም፡፡ የምንኖረው በቴክኖሎጂ እና በይዘት ፈጠራ እና በችርቻሮ እና በስርጭት ስር ባለ የእሴት ሰንሰለት ውስጥ የሚገኙትን ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን እና የመገናኛ ብዙሃን ዘርፉን የበለጠ ኃይለኛ የሆኑ አለምአቀፋዊ ተዋናዮች በሚቆጣጠሩበት የዲጂታል ዓለም ውስጥ ነው፡፡ የሁሉም ስራዎች ባለቤት ናቸው፡ ፡ በተመሳሳይም በአለም ላይ ያሉ መንግስታት የ”ሀሰተኛ ዜና” ን ሽፋን በመጠቀም ተቃውሞ ለማፈን ፣ በኢንተርኔት ላይ ያለውን እምነት እንዲሁም የዴሞክራሲን መሠረት በማጣመም የዜጎቻቸው የመረጃ አጠቃቀምን ቁጥጥር እያጠበቁ ነው፡፡

ዲጂታልነት በብዙ መልኩ ህዝባዊ ቦታን ዴሞክራሲያዊ አድርጓል፤ ነገር ግን ሁሉም ሰው ኃሳብን በነፃነት የመግለጽ መሰረታዊ መርሆችን አደጋ ላይ ሳይጥል ህዝባዊ ውይይቶች ላይ መሳተፍ አለበት፡፡

ሰዎች ስለ መገናኛ ብዙሃን ያላቸው ዕውቀት ከፍተኛ መሆን አለበት እንዲሁም ዴሞክራሲ ዘላቂነት እንዲኖረው የመረጃ ምንጮችን በአፅንዖት ማወቅ አለባቸው፡፡ ነገር ግን ፕሮፓጋንዳን እና ሐሰተኛ ዜናና መረጃን ለመከላከል ቀላል የሚባል መፍትሔ የለም፡፡ በተጨማሪም ባሉት ተቋማት እና ጋዜጠኞ ላይ ተዓማኒነት እንዳይኖር የመራውን የማህበረሰባችንን ነባር አወቃቀር ችግሮችም መዋጋት አለብን፡፡ ዛሬ – መረጃ በማንኛውም ጊዜ እና በየትኛውም ቦታ ባለበት ጊዜ የወረስናቸውን አድሎአዊነት እና ጭፍን ኩራት ጥያቄ ውስጥ የማይከቱ እና ውድቅ የማያደርጉ ሌሎች እይታዎች ፣ እውነታዎች እና ልምዶች ሳይጋለጡ በራሳችን ትንሽ የዲጂታል አለም ውስጥ ቆልፎ የሚያስቀምጠንን የመገናኛ ብዙሃን አይነት መፍጠር በጣም ቀላል ነው፡፡ የመረጃ መጠን በድንገት በሚያሻቅብበት በዚህ ጊዜ ዘላቂ ለመሆን ያለው ብቸኛ መንገድ ይህ ሊሆንም ይችላል፡፡ ወደ ማግለል እና ልዩነትን ወደማስፋት የምናዘግምበት መንገድም ሊሆን ይችላል፡፡ የመገናኛ ብዙሃን እና የመረጃ እውቀት ተጠቃሚ ስንሆን ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በዲጂታሉ አውድ አዘጋጅ ፣ አሳታሚ እና አከፋፋይ ስንሆን ሊኖረን የሚገባ እጅግ አስፈላጊ ችሎታ ነው፡፡ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከስልክ መልዕክት (SMS) ወደ ስናፕቻት (Snapchat) እና ኢንስታግራም (Instagram) ክ ብሎጎች (bloggs) ወደ ቪዲዮ ብሎጎች (vloggs) ተሸጋግረናል፡፡ የምስል መልዕክቶችን 24/7 እንለውጣለን፡፡ ወቅታዊ የምንጭ ትችት ምንነትን ፅሁፎችን እና ምንጮችን ጥያቄ ውስጥ በማስገባት ፣ በማወዳደር እና በመተንተን ፋንታ አዲሱን ክስተት ማለትም የፍለጋ ምቹነትን ፣ ቀመርን እና ሀገር በቀል ማስታወቂያን በደንብ ተረድተን መተዋወቅ ይኖርብናል፡፡ በተጨማሪም የምንጮች ትችት ትርጓሜን የማራዘም እና የትረካን ፣ የምልክት ገለፃን እንዲሁም የድራማተርጂ እና የምስላዊ ዓረፍተነገር (dramaturgy and rhetoric. )የኃይል እና ጥቅም የመረዳት ከፍተኛ ፍላጎት አለ፡፡ ሁሉም ቦታ ታሪኮች አሉን፡

በእያንዳንዱ ሴኮንድ አንድ ሰው ለማስታወቂያ ፣ ፖለቲካዊ ወይም ሐይማኖታዊ ጉዳዮች ስለሆነ ነገር ሊያሳምነን ይፈልጋል፡ ፡ ድግግሞሹን ለማየት መቻል አስፈላጊ ነው፡፡ ይህም ሰዎች ፡ ወጣቶችም ሆኑ ትልልቆች ላይ መረጃን በወሳኝ ሁኔታ እንዲመለከቱ እናም አንዳንድ ጊዜ በተለመደውም ሆነ በዲጂታል መገናኛ ብዙሃን የሚያጋጥሙንን በጥንቃቄ ተቀርፀው የሚመጡ መልዕክቶችን እንዲኖራቸው የመፈለግን ትልቅ ፍላጎትን ያሳርፋል፡፡ ለምሳሌ ያህል የሀይለኛ እና ጽንፈኛ ፕሮፓጋንዳን በተመለከተ፡ ትስስሩ ከየትኛውም አቅጣጫ ወይም መካከል ይምጣ ፡ የወንጀል ማህበራት፣ ቀኝ ፅንፈኛ ፣ ግራ ፅንፈኛ ወይም እንደ በኃይማኖታዊ ርዕዮተ ዓለም የታመቁ – ቢያንስ አራት ዘይቤያዊ አካባቢዎች ውስጥ ከታች የተጠቀሱትን የሚያካትቱ ተለዋዋጭ ነገሮች አሉ፡፡

  • ከፍተኛ ተቃራኒዎች
  • ግልፅ ራስን የመከላከያ አባባል
  • የዓለም በሴራዊ ማዕቀፍ ትረካዎች ውስጥ መብራራት
  • እናም ከውይይት እና ውሳኔ አሰጣጥ መፍትሔዎች ጋር የተጣመሩ ሐሳባዊነት እና ቀጥተኛ እርምጃዎች አሉ፡፡ ይህ ወሳኝ ባህሪይ በሚያሳዝን ሁኔታ የሚልከውን አካል ለምሳሌ የራሳቸውን የዓለም ምስል ለማረጋገጥ ከራሳቸውን ዓውደ-ፅሁፋዊ አስተሳሰብ በመነሳት ከዋናው የመገናኛ ብዙሃን የተሰበሰበን ቁሳቁስ ከመላክ አያስቆማቸውም፡፡ ነገር ግን እነዚህን መሰረታዊ አቀራረቦች እና ዘዴዎች በመረዳት እውነታዎትን ለማዛባት ከሚሞክሩት ውሸቶች እራስን ለመከላከል ይችላሉ፡፡

 ኢቫ ቶርስለንድ በዲጂታላይዜሽን እና ታማኝነት ጉዳዮች ላየ የሚያተኩሩ 4 መፃህፍት ደራሲ ናቸው፡፡ በቅርቡ በስዊድን መንግስት የተሰጣቸውን የስድስት ዓመት የስዊድን ሚዲያ ካውንስል ጠቅላላ ኃላፊነት ሥራ አጠናቀዋል፡፡ የቀድሞ የስዊድን አይ እና ቴሌኮም ኢንዱስተሪዎች የህዝብ ግንኙነት ኤክስፐርት ነበሩ እንዲሁም የስዊድን ኢነዱስትሪ እና ቴክኒካል ልማት ብሔራዊ ቦርድ የቀድሞ የክፍል ሐላፊ ነበሩ፡፡

 

selegna

By selegna

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *