AfricaCheck የአፍሪካ የመጀመሪያው ዕውነታን ማረጋገጫ ድርጅት ሲሆን እ.ኤ.አ በ2012 የህዝባዊ ክርክርን ትክክለኛነት እና የፖለቲከኞችን ታማኝነት ለማረጋገጥ የተጀመረ ድርጅት ነው፡፡ አፍሪካ ቼክ ከወቅታዊ የኦንላይን መሣሪያዎች ፣ አንባቢዎች ፣ ህዝባዊ ምንጮች እና ባለሞያዎች የጋዜጠኝነት ልምዶችን እና ማስረጃዎችን በመሰብሰብ እና በመጠቀም በህዝባዊ ቦታዎች የሚነሱ ቅሬታዎችን እያጠና ዕውነታውን ከሐሰተኛ መረጃዎች ለይቶ ውጤቶችን የሚያሳትም ፖለቲካዊ ያልሆነ ገለልተኛ ድርጅት ነው፡፡ እንደ “The African Election Promise Tracker” ያሉ የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ለምርጫቸው የገቡትን ቃል መፈፀም አለመፈፀማቸውን የሚከታተል አስፈላጊ ዲጂታል መሣሪያዎች የሚገኙበት ቦታ ነው፡፡ https://africacheck.org/
- Media Monitoring Africa (MMA) ሰብዓዊ መብትን የሚደግፍ ሥነ-ምግባራዊ እና ፍትሃዊ ጋዜጠንነትን የሚያበረታታ ድርጅት ነው፡፡ እንደ KnowNews የመሳሰሉ ዳውንሎድየሚደረጉ መሣሪያዎች ያሉበት ለጋዜጠኞች በጣም ጠቃሚ የሆነ ዲጂታል መሣሪያ ነው፡፡ ታማኝ የሆነ መረጃን ማጋራት ከፈለጉ ይህ መሣሪያ የሚፈልጉት ቦታ የታመነ ወይም የማይታመን ዜና መያዝ አለመያዙን ሊያረጋግጥልዎ ይችላል፡፡ https://www.mediamonitoringafrica.org/
- The Amnesty YouTube Dataviewer ይህ መሣሪያ የ YouTube ቪዲዮችን አድራሻ በማስገባት ቪዲዮው የተጫነበትን ትክክለኛ ጊዜ እና ከቪዲዮው ጋር የተያያዙ ማንኛውንም ዓይነት ምስሎች እንዲያገኙ ያስችልዎታል፡፡ YouTube ላይ ለመለየት አስቸጋሪ የሆኑት ቪዲዮው የተጫነበት ጊዜ እና ተያያዥ ምሰሎች ማግኘት የ YouTube ቪዲዮዎችን በቀላሉ ለመለየት በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡ የቪዲዮው ገፅ ላይ የማይገኘው የተጫነበት ትክክለኛ ጊዜ ምንጩን ለማወቅ ወሳን ነው፡፡ ምስሎቹም ወሳኝነታቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ምክንያቱም ምስሎቹን ቀይረን የጎግልን ምስል መፈለጊያ ወይም TinEye ን በመጠቀም ሌላ ቦታዎች ላይ መገኘት አለመገኘታቸው ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል በCitizen Evidence Lab ገፁ ላይ ሌሎች ዕውነታን ማረጋገጫ መሣሪያዎ አሉት፡፡ https://citizenevidence.org/2014/07/01/youtube-dataviewer/
- Tineye Tineye ተለዋጭ ምስል መፈለጊያ ምስሉ የት እና መቼ እንደተነሳ እና ተንኮል አዘል ፕሮፓጋንዳዎችን ለማሰራጨት የተጠለፈ መሆን አለመሆኑን ለመለየት ትክክለኛ ምንጩን እንዲያውቁ ያስችልዎታል፡፡ በ Tineye google chrome and firefox መተግበሪያዎች አማካኝነት ምስሉ ከየት እንደመጣ እና እንዴት ለጥቅም እንደዋለ ማወቅ ይቻላል፡፡ https://chrome.google.com/webstore/detail/tineye-reverse-image-sear/haebnnbpedcbhciplfhjjkbafijpncjl?hl=en
- The Poynter Institute የ PoynterInstitute የተለያዩ ስልጠናዎችን እና የዌብሳይት ሴሚናሮችን የሚያቀርብ የአሜሪካ የጋዜጠኝነት ስልጠና ተቋም ነው፡፡ Digital Tools to Verify Everything Online የተባለው የዌብሳይት ሴሚናር ዕውነታን ማረጋገጫ የኦንላይን መረጃዎችን ለማጣራት አንዳንድ አስፈላጊ የሆኑ መሣሪያዎችን ፣ ጥቆማዎችን እና ዘዴዎችን ያጋራል፡፡. https://www.poynter.org/shop/webinar/fact-check/